Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.28K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 233

2022-05-31 19:42:39
የተምች ወረርሽኝ በሰብሎች ላይ መከሰቱን የቡርጂ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ገለፀ።

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በሁሉም ቀበሌያት ፀረ ሰብል የሆነው የ #ተምች ተባይ ወረርሽን መከሰቱ ተገልጿል። የቡርጂ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽብሩ ኦቴ እንደ ወረዳ በአዋር ክላስተር አካባቢ በሚያዝያ ወር ተከሰቶ 200 ሊትር መድኃኒት ተረጭቶ የነበረ ቢሆንም በድጋሚ በወረዳው ሁሉም ቀበሌያት በመከሰቱ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል ይላሉ።

በአጠቃላይ ሰብሉ የተሸፈነው በ39000 ሄክታር አከባቢ በመሆኑና የተምች ስርጭት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ በመድኃኒት ቶሎ ካልተቆጣጠርን ሰብሎችን እንደሚጎዳና ህብረተሰቡን ለከፋ ችግር እንደሚያዳርግም ኃላፊው ተናግረዋል።

የክልሉ መንግሥትም ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የሚገልፁት ኃላፊው 1400 ሊትር መድኃኒት ከክልል እስከ ነገ እንደሚገባምና ለቀጣይም የተምች ተባይ የመራባት አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ የመድኃኒት እጥረት እንዳይከሰት የክልሉ መንግሥት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው እስካሁን ምንም የደረሳቸው መድኃኒት እንደሌለ ገልፀው የክልሉ መንግሥትም ሆነ የወረዳው መንግሥት ጊዜ ሳይሰጥ የተምች የመሰራጨት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ቶሎ መድኃኒት እንዲያቀርቡም አበክረው ጠይቀዋል ሲል የዘገበው የቡርጂ ልዩ ወረዳ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
25.1K viewsedited  16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 17:15:56
ባለፉት ዘጠኝ ወራት 444 ሐሰተኛ ማስረጃዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ተደርጓል።

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በዘጠኝ ወራት ውስጥ 303 መታወቂያ፣ 12 የጋብቻ ማስረጃ ፣ 111 ያላገባ ማስረጃ.፣ 8 የውክልና ሰነድ፣ እና ሌሎች ሰነዶችን ጨምሮ በአጠቃላይ በተቋሙ 444 ሐሰተኛ ማስረጃዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማድረጉን ገልጿል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
24.5K viewsedited  14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 23:44:06 #የዛሬ_2 (ግንቦት 22/2014)

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የአውሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ የመጣው ልዩነት ሙሉ በሙሉ ወደ #ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሰኑን ገልጿል።

ባለፉት ሁለት ቀናት ከጎረቤት ኤርትራ ሠራዊት ጋር አዲስ ውጊያ መካሄዱን የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀዋል። ቃል አቀባዩ ባለፈው ቅዳሜ እና እሑድ የኤርትራ ሠራዊት #በሽራሮ ጥቃት ከፍቶ ነበር ሲሉ ተናግረዋል። በኤርትራ መንግስት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ይህን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በሰጡት ቃል ተካሄደ ስለተባለው ውጊያ መረጃው እንደሌላቸው ገልጸው፣ ነገር ግን የኤርትራ ኃይሎች ጥቃት ሊፈጽሙ የሚችሉበት ሁኔታ የለም ብለዋል።

በጌዴኦ ዞን በገደብ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች የራሳቸውን ቋንቋ በመጠቀም ስለ ሀገራቸው እንዲያዉቁ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ተተርጉሞ እየተጠቀሙ መሆኑ ተገልጿል።

የፍትህ ሚኒስቴር ባለፉት አራት ዓመታት በባንኮች ላይ የ 1.8 ቢሊየን ብር #ምዝበራ መድረሱን አስታውቋል። ከዚህም ውስጥ 50 ነጥብ 7 በመቶ የደረሰው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ነው የተባለ ሲሆን በመቀጠል ከፍተኛ ምዝበራ ያጋጠማቸው አቢሲኒያ ባንክ (328.9 ሚሊየን ብር)፣ ኦሮሚያ ባንክ (161.8 ሚሊየን ብር) እና ወጋገን ባንክ (155.6 ሚሊየን ብር) ናቸው።

በጥሬ ዕቃ ምክንያት ላለፉት 3 ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው አዲስ የተሽከርካሪ ሠሌዳ የመስጠት አገልግሎት #ከ1ሣምንት በኋላ መሥጠት ይጀመራል ተብሏል። አሁን ላይ ግን የውጭ ምንዛሬ ተፈቅዶ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ከጀርመን ሀገር ለማስመጣት ዝግጅት ተጠናቋል ነው የተባለው።

እስካሁን በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች መያዙ የታወቀው #መንኪፖክስ ወይም የዝንጀሮ ፈንጣጣ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ይደርሳል ብለው እንደማይጠብቁ የዓለም የጤና ድርጅት ከፍተኛዋ የበሽታው ኤክስፐርት ተናግረዋል። ዶክተር ሮዛሙንድ ሉዊስ በሰጡት ማብራሪያ ድርጅታቸው መንኪፖክስ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም በአየር በትንፋሽ ይተላለፍ እንደሆን በተጨማሪም የህመም ምልክት የሌላቸው ሰዎች በሽታውን ያስተላልፋሉ ወይ የሚሉትን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎችን ይዞ እየመረመረ መሆኑን አመልክተዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል12 ወረዳዎች በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ ሰሞኑን በሩዝ ምርት ላይ የተከሰተው #ተምች አስጊ መሆኑ ተነግሯል። የዘርፉ ባለሞያዎች አሁን ላይ በሩዝ ሰብል ላይ የተከሰተው ተምች ''የአፍሪካ ፎል አርሚ ዎርም'' እንደሆነና ክስተቱ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ትልቅ ርብርብ እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
3.9K viewsedited  20:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 23:26:38 #የዛሬ_1 (ግንቦት 22/2014)

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፤ " ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት " ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ በሚገኘው በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የምርምራ ጊዜውን የፈቀደው የተከሳሽ ጠበቃ ያቀረቡትን መከራከሪያ እና የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ነው።

የ "ፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ " የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አህመድ ዛሬ ረፋዱን ከቢሾፍቱ ከተማ ከሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ የተለቀቀች ሲሆን ጋዜጠኛዋ ከእስር ከተለቀቀች በኋላ በስልክ እንዳነጋገሯት የገለጹት የቴሌቪዥን ጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ፖሊስ " ስንፈልግሽ ትመጫለሽ " በሚል መፈታቷን እንደነገረቻቸው አስታውቀዋል።

ባሳለፍነው ቅዳሜ በፀጥታ ሃይሎች የተያዘችው መዓዛ መሃመድ ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርባለች። ፖሊስ በመዓዛ መሃመድ ላይ " ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት " የሚል ክስ አቅርቦባታል። የጋዜጠኛዋ ጠበቆች ጋዜጠኛዋ ሰራች የተባለው ወንጀል ተፈፅሞ ቢሆን እንኳን ጉዳዩ ሊታይ የሚገባው በመገናኛ ብዙሀን አዋጅ ነው ፤ በእስር እንድትቆይ ህጉ አይፈቅድም ሲሉ ተከራክረዋል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር አዳምጦ የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል።

የመብቶች ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና 7 የተለያዩ ማህበራት በጋራ ባወጡት አጭር መግለጫ በጋዜጠኞች ላይ የዘፈቀደ እስር እየተፈፀመ መሆኑን በመግለፅ ድርጊቱን እንደሚቃወሙ ገልፀዋል።

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 22/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ተመልክቷል። የመርማሪ ቡድኑ ምርመራዬን ስላልጨረስኩ የተለያዩ ማስረጃዎችን ከባንክ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከኢንሳ እና ከሌሎች ተቋማት የምንሰበስባቸው መረጃዎች ስላሉ የ14 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል። ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱን ስላመነበት የምርመራ ቡድኑ ከጠየቀው የ14 ቀን ውስጥ 4 ቀን ቀንሶ 10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለሰኔ 2/2014 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
5.0K viewsedited  20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 21:50:20
ሰሞኑን በሩዝ ምርት ላይ የተከሰተው ተምች አስጊ መሆኑ ተጠቆመ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከባለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ የተከሰተው የተምች ወረርሽኝ በበቆሎና በሩዝ ማሳዎቻቸው ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

በተለይ በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በሩዝ ሰብል ላይ ተምች መከሰቱ ተገልጿል። በወረዳው የተሰተው ተምች በሩዝ ሰብል ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው የተጠቆመው።

የክልሉ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ የተምች ወረርሽኙ በክልሉ 12 ወረዳዎች ውስጥ በ1 ሺህ 219 ሄክታር መሬት ላይ መከሰቱን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። በአሁኑወቅት ወረርሽኙ በክልሉ 4 ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 12 ወረዳዎች ውስጥ በ 1 ሺህ 219 ሄክታር መሬት ላይ መታየቱን ነው የገለጹት።

በተመሳሳይ በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ ኮይና ከርከን በተባሉ ሁለት ቀበሌዎች ተምች መከሰቱ ሪፖርት ተደርጓል። ተምቹ በ4000 ሄክታር መሬት የሩዝ ማሳ ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ተብሏል።

በዲማ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት የሰብል ልማት ስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጫኔ ገመቹ እንደገለፁት ከዚህ በፊት የአሜሪካን ተምች ተብሎ የሚጠራ በበቆሎ ላይ ተከስቶ እንደነበር ገልፀው አሁን የተከሰተው ተምች በዋናነት ሩዝን የሚያጠቃ ከዚህ በፊት ያልተከሰተ መሆኑን ተናግረዋል።

የዘርፉ ባለሞያዎች አሁን ላይ በሩዝ ሰብል ላይ የተከሰተው ተምች ''የአፍሪካ ፎል አርሚ ዎርም'' እንደሆነና ክስተቱ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ትልቅ ርብርብ እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
12.9K viewsedited  18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 19:04:42
የከተማ መሬት ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ምዘናና ስልጠና በሶስት ዩኒቨርስቲዎች ተጀመረ።

የከተማ መሬት ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ምዘናና ስልጠና በባህርዳር፣ በአምቦና ወላይታ ዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኖል።

በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በአጠቃላይ 5000 የዘርፉ አመራርና ባለሙያዎችን 16 የዘርፉ የሙያ አይነቶችና አራት የሙያ ስትሪሞችን መሰረት በማድረግ ምዘናውና ሥልጠናው ይከናወናል ተብሏል።

በዚህ በጀት ዓመትም 1000 የሚሆኑ አመራሮችና ባለሙያዎች በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠናዉን በመውሰድ እንዲመዘኑ የሚያደርገው መርሃ ግብር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በመገኘት የስልጠና ማስጀመሪያውን በንግግር የከፈቱት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ሰልጣኞች የከተማ ነዋሪዎች የሚንገላቱባቸውንና የሚማረሩባቸውን የመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች በዕውቀትና በዘመነ አሰራር አንዲሁም በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲከውኑ ሰልጣኖች አደራ የተጣለባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በከተሞች ገቢ ማሻሻያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት በሀገራችን ባሉ አምስት ዩኒቨርስቲዎች የሚካሄደው የስልጠናና የብቃት ምዘና ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጉን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
19.1K viewsedited  16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 18:53:25
የምልክት ቋንቋ በደቡብ አፍሪካ 12ኛ ብሔራዊ ቋንቋ ሆኗል።

ደቡብ አፍሪካ የምልክት ቋንቋን 12ኛ ብሔራዊ ቋንቋ አድርጋ ተቀብላለች። ይህ ቋንቋ በመሰረታዊ የትምህርት ሥርዓት ውስጥም በአማራጭነት ይካተታል ተብሏል።

በቅርቡ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) የምልክት ቋንቋን 5ተኛ የሀገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ አድርጋ አጽድቃለች። በተመሳሳይ አፍሪካዊቷ ሀገር ማላዊም የምልክት ቋንቋን ብሔራዊ ቋንቋዋ አድርጋለች።

NB: በኢትዮጵያ እስከ 2.5 ሚሊዮን የሚገመቱ መስማት የተሳናቸው ሰዎች ይገኛሉ።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
16.9K viewsedited  15:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 17:39:36
በግንባታ ላይ ባለው ከባህር ዳር- ወልዲያ - ኮምቦልቻ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ስርቆት ተፈጸመ።

ከባህር ዳር-ወልዲያ -ኮምቦልቻ በግንባታ ላይ ባለ 400 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ስርቆት መፈጸሙን ፖሊስ አስታወቀ።

ድርጊቱ የተፈጸመው በአምባሰል ወረዳ 05 ቀበሌ ልዩ ስሙ አባ ይመሬ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን 3 ሺህ ዶላር ግምት ያለው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት ተፈጽሟል ነው የተባለው።

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በተፈፀመው የስርቆት ወንጀልም የኤክትሪክ ማስተላለፊያ ምሰሶ ብሎኖች በዘራፊዎች ተፈተው መወሰዳቸው ነው ከወረዳው የተገኘው መረጃ የሚያሳየው።

የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታውን እያከናወነ ያለው ታታ ፕሮጀክት የተባለ የህንድ ድርጅት ሲሆን ስርቆቱን የፈፀሙ ተጠርጣሪዎችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግም ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን በወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር መስፍን ይመር ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
18.7K viewsedited  14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 17:16:06
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በጌዴኡፋ ቋንቋ ተተርጉሞ በገደብ ከተማ ባሉ ት/ቤቶች እየተዘመረ ነው።

በጌዴኦ ዞን በገደብ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች የራሳቸውን ቋንቋ በመጠቀም ስለ ሀገራቸው እንዲያዉቁ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ተተርጉሞ እየተጠቀሙ መሆኑ ተገልጿል።

የገደብ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የጌዴኡፋ ቋንቋ መምህርት የሆኑት መሠረት ከበደ በትምህርት ቤታችን ብሔራዊ መዝሙሩ በጌዴኡፋ ቋንቋ መተርጎሙ ተማሪዎች የመዝሙሩን ትርጉም በቀላሉ ለመረዳት አስችሏቸዋል ብለዋል።

ትውልዱ የራሱን ባህላዊ እሴቶችን እና ቋንቋውን እንዲያሳድጉ እና እንድያበለፀግ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በትኩረት መሠራት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል የዘገበው የገደብ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
18.8K viewsedited  14:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 12:22:42
የድምጽ ብክለትን ለመከላከል አዲስ ህግ ሊወጣ ነው ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን ከመጠን በላይ የድምጽ ብክለት ለመከላከል አዲስ ህግ ሊወጣ መሆኑ ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡ ከዚህ በፊት በመዲናዋ የድምጽ ብክለት የሚከለክል ህግ ቢኖርም ተግባራዊ ማድረግ ላይ ክፍተቶች እንደነበሩ ነው የተነገረው፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እንደተናገሩት፣ ከተማዋ በድምጽ የብጥብጥ እና የረብሻ ከተማ ከሆነች ሰነባብታለች ሲሉ ተናግረዋል ሲል ዘገባው አክሏል፡፡

በየመንገዱ በህገ-ወጥ መንገድ ከፍተኛ ድምጽ በመጠቀም፣ የንግድ ስራ የሚሰሩ ሰዎች የዜጎችን እና የከተማዋን ሰላም እየነሱ እንደሚገኙም ነው ሥራ አስኪያጁ የገለጹት፡፡

በዓለማችን ካሉ ከተሞች አዲስ አበባ ከፍተኛ የድምጽ ብክለት ከሚያስተናግዱ ከተሞች መካከል ከቀዳሚዎቹ ዉስጥ እንደምትጠቀስ፥ ለዚህም ከተማ አስተዳደሩ ውጤታማ እና ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የድምጽ ብክልት የሚከለክል ህግ እያዘጋጀ መሆኑን መግለጻቸውን ዘገባው አንስቷል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.6K viewsedited  09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ