Get Mystery Box with random crypto!

በ10 ከተሞች በሊዝ ጨረታ መሬት ለመውሰድ ካሸነፉት መካከል 71 በመቶ የሚሆኑት ስራ አለመጀመራቸው | TIKVAH-MAGAZINE

በ10 ከተሞች በሊዝ ጨረታ መሬት ለመውሰድ ካሸነፉት መካከል 71 በመቶ የሚሆኑት ስራ አለመጀመራቸውን ጥናት አመለከተ

በኢትዮጵያ 10 ከተሞች በሊዝ ጨረታ መሬት ለመውሰድ አሸናፊ ከሆኑት 636 ተጫራቾች መካከል 71 በመቶ የሚሆኑት ስራ አለጀመራቸውን ጥናት አመለከተ።

በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ አሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ባህርዳር፣ ሐረር፣ ሀዋሳ፣ ጂግጅጋ እና ሰመራ ከተሞች በሊዝ ጨረታ መሬት በወሰዱ ግለሰቦችና በመሬት ተቋማት ላይ ጥናቱ መካሄዱ ተነግሯል።

በ2014 ዓ.ም ጥናቱ በተካሄደበት ወቅት መሬት ለመውሰድ ተጫርተው በሊዝ አሸናፊ የሆኑ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ ደረጃ የያዙ 636 ተጫራጮች ሲካተቱ የግንባታ ግብዓት እጥረት፣ የፋይናንስ አቅርቦት ችግር፣ የመሰረተ ልማት አለመሟላት ምክንያት ወደ ስራ አለመግባታችውን መሬት የወሰዱ ግለሰቦችና ተቋማት አስረድተዋል።

በሊዝ መሬት ወስደው ወደ ልማት ባልገቡ አካላት ላይ የሚመለከተው ተቋም በሚያከናውነው የክትትልና ቁጥጥር መላላት በ95 በመቶ በሚጠጉት ላይ እርምጃ #አለመወሰዱንም ጥናቱ አሳይቷል ሲል ኢዜእ ዘግቧል።

@TikvahethMagazine