Get Mystery Box with random crypto!

የተምች ወረርሽኝ በሰብሎች ላይ መከሰቱን የቡርጂ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ገለፀ። በደቡብ ክልል | TIKVAH-MAGAZINE

የተምች ወረርሽኝ በሰብሎች ላይ መከሰቱን የቡርጂ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ገለፀ።

በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ በሁሉም ቀበሌያት ፀረ ሰብል የሆነው የ #ተምች ተባይ ወረርሽን መከሰቱ ተገልጿል። የቡርጂ ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽብሩ ኦቴ እንደ ወረዳ በአዋር ክላስተር አካባቢ በሚያዝያ ወር ተከሰቶ 200 ሊትር መድኃኒት ተረጭቶ የነበረ ቢሆንም በድጋሚ በወረዳው ሁሉም ቀበሌያት በመከሰቱ ጉዳዩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል ይላሉ።

በአጠቃላይ ሰብሉ የተሸፈነው በ39000 ሄክታር አከባቢ በመሆኑና የተምች ስርጭት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ በመድኃኒት ቶሎ ካልተቆጣጠርን ሰብሎችን እንደሚጎዳና ህብረተሰቡን ለከፋ ችግር እንደሚያዳርግም ኃላፊው ተናግረዋል።

የክልሉ መንግሥትም ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የሚገልፁት ኃላፊው 1400 ሊትር መድኃኒት ከክልል እስከ ነገ እንደሚገባምና ለቀጣይም የተምች ተባይ የመራባት አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ የመድኃኒት እጥረት እንዳይከሰት የክልሉ መንግሥት ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው እስካሁን ምንም የደረሳቸው መድኃኒት እንደሌለ ገልፀው የክልሉ መንግሥትም ሆነ የወረዳው መንግሥት ጊዜ ሳይሰጥ የተምች የመሰራጨት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ቶሎ መድኃኒት እንዲያቀርቡም አበክረው ጠይቀዋል ሲል የዘገበው የቡርጂ ልዩ ወረዳ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot