Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Silver
Platinum
Golden
Choleraupdate
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.37K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 248

2022-05-15 16:28:16
አንዲት እናት እያዋለደች ባለበት ሰዓት በባሏ በጩቤ ተወግታ የተገደለችው የጤና ባለሞያ

በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በዳዳ ሳታላይት ጤና ጣቢያ አዋላጅ ነርስ የነበረችው ሲ/ር ሲ/ር አማረች ዋዳ በምትሰራበት ቦታ በባሏ በጩቤ ተወግታ ህይወቷ አልፏል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ግንቦት 5 ዕለት ከጧቱ 3:00 ሰዓት ላይ አንዲት እናት እያዋለደች እንዳለ ሲሆን ገዳይ በጩቤ 5 ቦታ በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉን ፖሊስ አስታውቋል።

ከወረዳው ኮሚውኒኬሽን ቢሮ በተገኘው መረጃ መሰረት ሲ/ር አማረች ከገዳይ ባሏ ሁለት ልጆች የወለደች ሲሆን የአንድ ወንድና የአንድ ሴት እናት ነበረች።

ገዳይ በሰዓቱ በህግ ቁጥጥር ውሎ ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን መረጃው ተጣርቶ የህግ እርምጃ ሲወሰድ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

@tikvahethmagazine
25.9K viewsedited  13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 16:07:46
የጎጃም ባህል ማዕከል ግንባታ አፈጻጸም 41 በመቶ መድረሱን የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ገለጸ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ ላይ በመገንባት የሚገኘው የጎጃም ባህል ማዕከል ግንባታ አፈጻጸም 41 በመቶ መድረሱን የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ገልጿል።

የባህል ማዕከሉ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ሙዚየም፣ ቤተ መፅሀፍትና ሌሎች ቢሮዎችን ያካተተ መሆኑንና ከተማዋን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ጠቀሜታ እንዳለው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌው ተናግረዋል።

በአማራ ህንፃ ስራዎች ተቋራጭነት እየተገነባ የሚገኘው ይህ የባህል ማዕከል የግንባታ ጥራቱን በጠበቀና በተገቢው የውል ስምምነት ጊዜ ለማጠናቀቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የድርጅቱ የጎጃም በህል ማዕከል አሰሪ መሀንዲስ አቶ ሰለሞን ቸኮል ተናግረዋል።

መረጃው የክልሉ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine
24.0K viewsedited  13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 16:01:08
#Arerti

በሰሜን ሸዋ ዞን አረርቲ ከተማ አሥተዳደር በ15 ሄክታር መሬት ላይ 70 መኖሪያ ቤቶች ለመገንባት የማስጀመሪያ መርኃግብር ተካሂዷል። ግንባታውን በሱፍቃድ ሪልስቴት የሚያከናውነው ሲሆን በከተማዋ ያለውን የመኖሪያ ቤት ችግር ከማቃለል ባለፈ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሏል። (አሚኮ)

@tikvahethmagazine
20.3K viewsedited  13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 16:00:39
#PowerOutage

በአዲስ አበባ ከተማ ለመካከለኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ተሸካሚ መስመሮች የማሻሻያ ስራ ለመስራት ለጥንቃቄ ሲባል ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 11፡00 ድረስ በለቡ፣ በጆሞ አንድ በከፊል፣ በኮዩ ፈጨ ውሃ፣ በአርሴማ ቤተ ክርስቲያን፣ በባሌስትራ እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

@tikvahethmagazine
18.4K viewsedited  13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 16:00:23
የሊንኮቹን ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+Zhm6yWqPh7U0N2E0
17.0K views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 16:00:08
የተሟላ የውሃ ስራ መፍትሔ - Complete Solar pumping solution

የአንድ ገበሬ ወይም የሰፋፊ እርሻ ባለቤት ከሆኑ፣ መንግስታዊ የውሃ እና የመስኖ ቢሮዎች ከሆናችሁ፣ እንዲሁም መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ የውሃ ፕሮጀችቶች ለምትቀርፁ ሁሉ ተመራጭ ስለሆንን ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት በስልክ ቁጥሮቻችን አሁኑኑ ያግኙን።

Solution matters!
+251970710024 / +251970710017

@SinopiaImpex
17.9K views13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 13:42:44
ሕንድ የስንዴ ምርት ከሀገሯ ዉጪ እንዳይሸጥ እገዳ ጣለች።

ሕንድ በሀገሯ የምግብ እጥረት እንዳይከሰት በሚል የስንዴ ምርት ከሀገሯ ዉጪ እንዳይሸጥ እገዳ ጥላለች። የአውሮፓ ሀገራት በበኩላቸው የሕንድን ውሳኔ የኮነኑ ሲሆን ውሳኔው በዓለም የስንዴ ገበያ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ሲሉ አክለዋል።

ሕንድ በስንዴ ሽያጭ ላይ እገዳ መጣሏ በተለይም በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የስንዴ አቅርቦት የተቋረጠባቸው የአፍሪካ እና እስያ ሀገራት ሕንድን እንደ አማራጭ ለመጠቀም አስበው ነበር።

የሕንድን ውሳኔ ከተቃወሙ የአውሮፓ ሀገራት መካከል ጀርመን አንዷ ስትሆን ድርጊቱ ዓለም ወደ ከፋ የምግብ ቀውስ እንደሚያመራ በግብርና ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃለች። (AlAin)

@tikvahethmagazine
6.9K viewsedited  10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 13:32:29
የወልድያ ከተማ አስተዳደር የ"መቀመጭት ተራራን" "አቡነ ኤርምስ ተራራ" ብሎ ሰይሟል።

''ከአምስት ወራት በላይ በዘለቁት አስከፊ ጊዜያት የሁሉም ቤተ እምነት ሰብሳቢ፤ ከእምነት ይልቅ ሰብኣዊነትን ባስቀደሙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞ ብሔረስብ አስተዳደር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በወገቡ ታላቅ ምስጢር ያዘለውን የ"መቀመጭት" ተራራን "አቡነ ኤርምያስ ተራራ" ተብሎ መሰየሙን አብስሯል፡፡'' ሲል ነው ከተማ አስተዳደሩ ያስታወቀው።

@tikvahethmagazine
7.8K viewsedited  10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 13:30:41
በደንዲ ሀይቅ ላይ ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም ሎጂ ሊገነባ ነው።

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው በደንዲ ሀይቅ ላይ ዘመናዊ ኢኮ-ቱሪዝም ሎጂ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ። የወንጪና የደንዲ ሐይቅ የልማት ፕሮጀክቶችን የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታም እየተከናወነ ነው።

የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የጣልያኑ "ዊ ቢውልድ" ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ፔትሮ ሳሊኒ እና የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

የምዕራብ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዲዳ ጉታ በፕሮጀክቱ የደንዲ ሐይቅንና አካባቢውን የልማትና የቱሪዝም ማዕከል በማድረግ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት ይከናወናሉ ብለዋል።

የደንዲ ሐይቅ ልማት ፕሮጀክት ግንባታው የሚያከናውነው ሳሊኒ ኢምፕረጂሎ ኩባንያ ነው።

የወንጪ-ደንዲ ሐይቅ ኢኮ ቱሪዝም ልማት ፕሮጀክት በ"ገበታ ለሐገር" መርሐ ግብር ከሚከናወነው ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ሲሆን የወንጪ ደንዲ የተቀናጀ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት የግንባታ ስራው በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መጀመሩ ይታወሳል። (EPA)

@tikvahethmagazine
7.4K viewsedited  10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 13:30:32
Sejoy Blood pressure

0911284606
    ሀኪሞን በእጆ , ጤናዎትን በየግዜዉ ሳይጨነቁ በፈለጉበት ቦታ ና ግዜ ይወቁ
የደም መጠን ሚለካ 
የልብ ምት መጠንን ሚለካ
ሰለደም ግፊት አጠቃላይ መረጃ ሚሰጥ
ዋጋ- 1900  birr
Bole medanialem
6.1K views10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ