Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.56K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 246

2022-05-23 18:37:29
'የአፍሪካ ተምች' በጅማ ዞን መከሰቱ ተገልጿል።

'የአፍሪካ ተምች' በጅማ ዞን በሸቤ ሰምቦ ወረዳ መከሰቱን የጅማ እፅዋት ክሊኒክ ማዕከል አስታውቋል፡፡ የማዕከሉ ሀላፊ አቶ ቦና ሂርጳ ፥ ተምቹ በወረዳው በሚገኙ አራት ቀበሌዎች መከሰቱን መግለጻቸውን ፋብኮ ዘግቧል።

በዚህም በ400 ሄክታር መሬት ላይ በሚገኝ የበቆሎ፣ጤፍ፣ማሽላ፣ ዳጉሳ እና የግጦሽ ሳር ላይ ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት፡፡

አሁን ላይ ተባዮችና የዕፅዋት በሽታዎች እየተስፋፉ በመሆኑ አርሶ አደሩ ማሳውን በመፈተሽ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው አሳስበዋል ሲል ዘገባው አመላክቷል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
20.9K viewsedited  15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 16:29:07
#ጥቆማ

አዋሽ ባንክ ታታሪዎቹ የተሰኘ የስራ ፈጠራ ውድድር በቅርቡ እንደሚጀምር አስታውቋል። የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው የውድድሩ ተሳታፊዎች የሙያዊ ክህሎት ስልጠና እንዲሁም በየደረጃው የገንዘብ ሽልማት ከማግኘታቸውም በተጨማሪ ከ1ኛ እሰከ 5ኛ የሚወጡ የመጨረሻዎቹ የውደድሩ አሸናፊዎችም ከብር 200 ሺህ እስከ አንድ ሚሊዮን የገንዘብ ሽልማትና የፈጠራ ሀሳባቸውን ተግባራዊ የሚያደርጉበት እስከ ብር አምስት ሚሊዮን የሚደርስ ከዋስትና ነፃ የብድር አገልግሎት ይመቻችላቸዋል ብሏል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
24.3K viewsedited  13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 16:23:45
የኢትዮጵያ ቡና በአልጄሪያ ገበያ ስለሚቀርብበት ሁኔታ ምክክር ተካሄደ

በአልጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው የኢትዮጵያ ቡና በአልጄሪያ ገበያ ስለሚቀርብበት ሁኔታ በሀገሪቱ እውቅ ከሆነው የቡና አቅራቢ ፌኔክ ኮፊ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ነቢያት በውይያታቸው የኢትዮጵያ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቀጥታ ወደ አልጄሪያ ገበያ ስለሚቀርብበት ሁኔታ መምከራቸውን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ወራት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ውጭ ከተላከ ቡና አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳገኘች መገለጹ ይታወሳል። (ENA)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
20.5K viewsedited  13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 16:22:47
የቤቶች መረጃ አስተዳደር ስርዓት በኦሮሚያ ዘጠኝ ከተሞች ሊተገበር ነው ተባለ።

ከቤቶች መረጃ አያያዝና አስተዳደር ጋር በተያያዘ የሚስተዋለውን ሰፊ ክፍተት ለመሙላት ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው የታመነበት የቤቶች መረጃ አስተዳደር ሶፍትዌር ትግበራ በኦሮሚያ ዘጠኝ ከተሞች ዛሬ በይፋ ተጀምሯል ተብሏል።

በክልሉ ከ122ሺህ በላይ የሚገኙ የቀበሌ ቤቶችን ለመመዝገብ፣ ጥገናና እድሳት ለማድረግ፣የኪራይ ውልን ለማከናወን፣ በተከራዮች የሚነሱ የተለያዩ ጉዳዮችንና ቅሬታዎችን ለመከታተልና መፍትሔ በወቅቱ ለመስጠት የመረጃ ስርዓቱ እጅግ ጠቃሚ ነው ተብሏል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
18.4K viewsedited  13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 16:15:58
በሐረርና ጅግጅጋ አካባቢ የተተከሉት ትራንስፎርመሮች በቅርቡ ሥራ ይጀምራሉ ተባለ።

የሐረርና የጅግጅጋ ከተሞችና አካባቢያቸውን ችግር እንዲፈቱ የተተከሉት ፓወር ትራንስፎርመሮች ተከላ እና የፍተሻ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለሙከራ ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ ጋሻው እንድሪያስ እንዳስታወቁት÷ በሐረር ቁጥር 3 ማከፋፈያ ጣቢያ ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፔር የፓወር ትራንስፎርመር ተከላ ሥራ እና ፍተሻው በመጠናቀቁ ኃይል መስጠት የሚችልበት የሙከራ ሥራ የሚሰራበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡

አዲሱ የፓወር ትራንስፎርመር መሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ በሐረር፣ በአወዳይ፣ በኮምቦልቻ ከተሞችና የገጠር መንደሮች በማከፋፈያ ጣቢያው በሚስተዋለው ከአቅም በላይ ጭነት ምክንያት ያጋጥም የነበረውን የኃይል እጥረት ሙሉ በሙሉ ይቀርፋል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም እስከ ሐሮማያ ከተማ እንደ አስፈላጊነቱ መመገብ የሚችል አቅም የተፈጠረለት ሲሆን÷ አዲሱ ትራንስፎርመር ከነባሩ ትራንስፎርመር አቅም ጋር ሲነጻጸር በ5 እጥፍ የሚበልጥ አቅም እንዳለው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በጅግጅጋ ማከፋፈያ ጣቢያ የፓወር ትራንስፎርመር ተከላ ሥራ እየተከናወነ ሲሆን÷ አፈጻጸሙም ከሐረር ቁጥር 3 ማከፋፈያ ጣቢያ ጋር ተቀራራቢ በሆነ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሪጅኑ የሰብስቴሽን ኦፕሬሽንና ጥገና ሥራ አስኪያጅ አቶ ከድር አብደላ ገልጸዋል።

አቶ ከድር አክለውም÷ ሪጅኑ ከሑርሶ እስከ ሐረር ድረስ ባለው የ132 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር ላይ አስራ ሁለት የ132ኪሎ ቮልት 400/800/1 አምፐር ከረንት ትራንስፎርመሮችን በመትከል የምስራቅ ኢትዮጵያን የግሪድ ሲስተም የሚያስተካክል ሥራ ሰርቷል ብለዋል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
17.7K viewsedited  13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 16:15:49
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+Zhm6yWqPh7U0N2E0
16.3K views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 16:15:36
ARE YOU LOOKING FOR LOGISTICS RELATED SHORT TERM
TRAINING PROGRAMS?

Our Association, Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA) has a good news!!!
We arranged continuous short term training programs on various topics of Logistics.

INTERESTED TO KNOW MORE?
Please call us at +251 903 182525 or +251 115 589045
OR
Visit our telegram channel
https://t.me/EFFSAAOfficial
18.1K views13:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 11:49:09
#ጥቆማ

'አዩቴ ኢትዮጵያ ቻሌንጅ (AYuTe Ethiopia Challenge)' የተሰኘና በኢትዮጵያ ግብርናን ለማሻሻል የሚረዳ የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው ዕድሜያቸው ከ18-29 የሆኑ ኢትዮጵያንን የሚያሳትፍ ውድድር ይፋ ሆኗል።

ውድድሩ፥ በኢትዮጵያ ያሉ አነስተኛ አርሶ አደሮችን ተግዳሮቶች መቅረፍ ምርትን ምርታማነትን፣ ገቢን፣ የፋይናንስ አቅርቦትንና የመቋቋም አቅም ያላቸውን የግብርና ቴክኖሎጂ ሀሳቦችን አወዳድሮ ለመሸለም ያለመ ነው።

የማመልከቻ ጊዜው ከግንቦት 13 ቀን 2014 ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ከአንድ እስከ ሶስት ለሚወጡ አሸናፊዎች 20 ሺ ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቷል።

ለማመልከት : https://ayute-ethiopia.et/apply-here/

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.4K viewsedited  08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 11:02:11
የአፈር አሲዳመነት አምራች በሚባሉት ክልሎች ላይ በስፋት መከሰቱ ተጠቆመ።

የአፈር አሲዳመነት አምራች በሚባሉት ክልሎች ላይ በስፋት መከሰቱ በምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር ነገር ነው።

የግብርና ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያመለክተው፦

በኦሮሚያ ክልል በ14 ወረዳዎች 1.7 ሚሊዬን ሄ/ር መሬት፤

በአማራ ክልል ለእርሻ አገልግሎት ከሚውለው 4.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት 1.2 ሚሊዬን የሚሆነው፤

በደቡብ ክልል ከሚታረሰው የእርሻ መሬት 44 በመቶ የሚሆነው እንዲሁም፤

በሲዳማ ክልል አጠቃላይ ካለው የመሬት ስፋት 95 ሺህ ሄ/ር የሚሆነው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነው ተብሏል፡፡

አሁን ላይ በመንግስት በኩል ያለው የኖራ አቀርቦት በቂ ባለመሆኑ መንግስት ኖራ በብዛት አንዲመረት የግል ባለሀብቶችን ወደ ዘርፉ በሚኒስቴሩ በአማራጭ መፍትሔነት ተይዟል።

በተጠማሪም ኖራ የሚገኝባቸው ቦታዎች ላይ የፀጥታ ችግር እንዳይኖር የማድረግ እንዲሁም አሲዳማነት የሚታይባቸው ቦታዎችን በጥናት በመለየትና ኖራ የሚመረትባቸው ቦታዎች አንዲቃራረቡ በማድረግ ለትራንሰፖርት የሚወጣውን ከፍተኛ ወጭም መቀነስ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
21.9K viewsedited  08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 10:59:25
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በባህላዊ ፍርድ ቤቶች ከሁለት ሺህ በላይ የክስ መዝገቦች እልባት አግኝተዋል።

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ በሶስት ወራት ውስጥ ከሁለት ሺህ በላይ የክስ መዝገቦች በባህላዊ ፍርድ ቤቶች እልባት እንዲያገኙ ተደርጓል ተብሏል። ይህንን የተመለከተ ውይይትም በጭሮ ከተማ ተካሂዷል።

የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ቡካር ከዲሮ በዞኑ በሶስት ወራት ውስጥ ከቀረቡት 2 ሺህ 954 መዝገቦች 2 ሺህ 230 ጉዳዮች በባህላዊ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

በመደበኛ ፍርድ ቤቶች የቀረቡ ጉዳዮች በባለ ጉዳዮቹ ፈቃደኝነት ላይ በመመስረት ጉዳዩ በባህላዊ ፍርድ ቤት የሚታይ ሲሆን በገጠራማ አካባቢ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የስራ ጊዜያቸውንና ለመጓጓዣ የሚያወጡትን ወጪ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶላቸዋል ብለዋል።

ጨፌ ኦሮሚያ በሐምሌ ወር 2013 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብስባ በኦሮሚያ ክልል ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች በተጨማሪ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች እንዲቋቋሙ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 240/2013 ማጽደቁ የሚታወስ ነው። (ENA)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
19.6K viewsedited  07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ