Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Samitech
Cloudbridge
Traininginstitute
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.23K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 245

2022-05-20 15:22:55
የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ አስረከበ።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ በመሸንቲ ሳይት ተደራጅተው ለቆዩ 196 ማኅበራት የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ አስረክቧል።

በመሸንቲ ሳይት 3 ሺህ 806 አባላትን ያቀፉ 185 ማኅበራት፣ 261 አባላትን ያቀፉ 11 የአርሶ አደር ልጆች ማኅበራት በድምሩ 196 ማኅበራት፣ 4 ሺህ 67 አባላት የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታ ተረክበዋል።

የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ሀላፊ ኃይለእየሱስ ፀጋዬ አዲስ ከተማን የመመስረት ተግባር እየተሠራ በመሆኑ ውኃ፣ መብራት፣ መንገድና ሌሎች የመሠረተ ልማት ግንባታዎች እንደሚከናወኑ ተናግረዋል። መንግሥት ለሚያከናውናቸው ሥራዎች ሁሉ ማኅበራትም የበኩላቸውን ድጋፍ እዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ለማኅበራት ቦታ መስጠት ብቻ ሳይሆን ከተማ አሥተዳደሩ አስፈላጊውን ማሽነሪና ሌሎች ድጋፎችን እንደሚያደርግ ኀላፊው ቃል ገብተዋል። በተለይ ለግንባታ አስቸጋሪ አካባቢ የገጠማቸው ማኅበራት ከተማ አሥተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በዘንዘልማ ሳይት ተደራጅተው የመኖሪያ ቤት መሥሪያ ቦታን ለሚጠባበቁ ማኅበራት በበጀት ዓመቱ ምላሽ ለመስጠት እየሠራ መሆኑን ሀላፊው ተናግረዋል።

ለመኖሪያ ቤት መሥሪያ ግንባታ ቦታቸውን የሚለቁ አርሶ አደሮች ልጆቻቸው በማኅበር በመደራጀት ቦታ እንዲሰጣቸው መደረጉን አቶ ኃይለእየሱስ ተናግረዋል ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

@tikvahethmagazine
24.0K views12:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 15:20:41
5 ሺህ ሄክታር ስፋት ያለው የአባያ ሃይቅ ክፍል በእምቦጭ ተወሯል ተባለ

የደቡብ ክልል የአከባቢና ደን ባለስልጣን የብዘሃ ህይወት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ አቶ መላኩ ባፋ ፥ እምቦጭ አረም የአባያ ሀይቅን በስፋት እያጠቃ መሆኑን ገልፀው፥ አረሙን ለማጥፋት የሚያስችሉ ስራዎችና ሙከራዎች በሰው ጉልበትና በመሳሰሉት ለመግታት ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም ብለዋል፡፡

በዚህም በሀይቁ ላይ ያለውን ብዘሃ ሕይወት በማይጎዳ መልኩ አረሙን የማጥፋት ዘመቻ ለማካሄድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አረሙ በፍጥነት ካልተወገደ ከሀይቁ በሚገኝ ገቢ የሚተዳደሩትን በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ገቢ በማሳጣት ሊጎዳ እንደሚችል ተገልጿል።

የእንቦጩ መስፋፋት ከኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ተባብሮ ለመስራት እንዲያስችል ከስምጥ ሸላቆ ተፋሰስ ባለስልጣን ጋር በጥምረት ለመስራት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ሃይቁ በውስጡ ከ54 በላይ ብዘሃ ሕይወትን የያዘው የአባያ ሀይቅ በዓመት ከ4 ሺህ ቶን በላይ ዓሳ የማምረት አቅም ያለውና ዓዞን ጨምሮ በነጭ ሣር ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ያሉ የዱር እንስሳትም የህልውናቸው መሰረት መሆኑ ከደ.ሬ.ቴ.ድ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahethmagazine
19.4K viewsedited  12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 15:20:31
የት ለመማር ወሰኑ?

በ Software Engineering እና በ Information Technology and Systems በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርቶን ለመማር ወደ #ቢትስኮሌጅ ቢመጡ አብዝተው ያተርፋሉ።

በ4 ዓመት ውስጥ በዲግሪ ብቻ ሳይሆን ብቁ ሰራተኛ ሆነው ጭምር ይመረቃሉ።

ጥራታቸውን የጠበቁና የመማር ማስተማር ሂደቱን የሚያግዙ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መምህራን፣ በዘመናዊ መልክ የተደራጁ መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተመፃህፍት፣ የኮምፒዩተር ላብራቶሪዎች እና እጅግ ዘመናዊ የአይቲ መሠረተ ልማት #በቢትስኮሌጅ የተሟሉ ናቸው።

ለማመልከት እና ለበለጠ መረጃ፦

ድረ ገጽ www.bitscollege.edu.et

0982 363636 / 0978028655

#BITSCollege
18.4K views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 15:20:22
ኢትኤል ዲዛይን ❖ Ethel Design

ለመኖርያ ቤት ለቢሮ ለንግድ ቦታዎ ውብ እና ማራኪ የሆኑ ዲዛይኖችን በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ካለው የፊኒሺንግ ስራ ጋር ሰርተን እናስረክቦታለን። ይደውሉልን።

የምንሰጣቸው አገልግሎት
የዲዛይን እና የፊኒሺንግ ስራ
የእንጨት ፓርቲሽኖችን መስራት
አጠቃላይ የእንጨት ስራ
ብራንዲንግ

Contact us @etheldesign1
0939902740
0919361804

Telegram: t.me/etheldesign
19.6K views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 22:19:53 የጉማ ሽልማት ፦

የህይወት ዘመን ተሸላሚ
ፕሮፌሰር ሳሌም መኩሪያ

በምርጥ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ምርጥ ድርሰት
እረኛዬ (ቅድስት ይልማ፣ አዜብ ወርቁ፣ ቤዛ ሀይሉ)

ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ምርጥ ተዋናይ
" በእግር እሳት" ብርሀኑ ድጋፌ

ምርጥ የቴሌቪዥን ተከታይ ድራማ ዳይሬክተር
አብርሐም ገዛኸኝ በ "እግር እሳት "

በምርጥ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ እረኛዬ

በምርጥ ሴት ተዋናይት
ሳያት ደምሴ አሸናፊ " እረኛዬ "

ዘንድሮ በጉማ ሽልማት ለመጀመሪያ ጊዜ መሰጠት የጀመረውን "የሄርሜላ ሽልማት" የመጀመሪያዋ ተሸላሚ ዓለም ፀሐይ በቀለ ።

የአመቱን ምርጥ ኤዲተር
ዳንኤል ግርማ " ምን አለሽ "ፊልም

በምርጥ ረዳት ተዋናይ አሽናፊ
ሽመልስ አበራ

የአመቱ ምርጥ ሴት ተዋናይት
አምለሰት ሙጬ "ምን አለሽ" ፊልም

የአመቱ ምርጥ ተዋናይ
እንግዳሰው ሀብቴ

የአመቱ ምርጥ ፊልም
"ማንያዘዋል"

ኑር አክመል በ "ማንያዘዋል"ፊልም የአመቱ ምርጥ ዳይሬክተር

ምንጭ፦ ያሬድ ሹመቴ

@tikvahethmagazine
31.7K viewsedited  19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 18:09:03
በአዲስ አበባ የሚገኙ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የማጽዳትና የመጠገን ሥራ እየተሰራ ነው ተባለ።

በአዲስ አበባ የጎርፍ አደጋ ሥጋት ያለባቸው ሥፍራዎች የሚገኙ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የማጽዳትና የመጠገን ሥራ እየተሰራ መሆኑን የመዲናዋ የመንገዶች ባለሥልጣን አስታውቋል።

ከመንገድ ግንባታና ጥገና በተጨማሪ ተቋሙ ጽዳትና ጥገና ለሚያስፈልጋቸው ከ400 ኪሎ ሜትር በላይ ‘የፍሳሽ መስመር ጽዳትና ጥገና መደረጉን የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እያሱ ሰለሞን ገልጸዋል።

መጪው የክረምት ወቅት ከባድ ዝናብ እንደሚኖር የሚቲዎሮሎጅ ትንበያ እንደሚያመለክት ኃላፊው ገልጸው ይህንንም ተከትሎ የአደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን በለያቸው ሥፍራዎች የሚገኙ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የማጽዳትና የመጠገን ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ ኅብረተሰቡ ለጽዳት ተብሎ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ክዳኖች በሚከፈቱበት ወቅት ደረቅ ቆሻሻዎችን በማስወገድ መስመሮች እንዲዘጉ በማድረግ ችግሩን ማባባሱን ገልጸዋል። እስካሁን 42 ቦታዎች ላይ ጥገናና ጽዳት እየተደረገ በመሆኑ ኅብረተሰቡ እነዚህን ቦታዎች ህገ-ወጥ ተግባራት ከሚፈጽሙ ሰዎች እንዲከላከል ጠይቀዋል።

@tikvahethmagazine
33.6K viewsedited  15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 17:31:46
የቡናና ሻይ ህንፃ የፍሳሽ ማስወገጃ ስራ ላይ በተሰማሩ ሰራተኞች ላይ አፈር ተደርምሶ ጉዳት ደረሰ

ሜክሲክኮ አካባቢ በሚገኘው የቡናና ሻይ ህንፃ የፍሳሽ ማስወገጃ ለመቀየር እየሰሩ በነበሩ የቀን ሰራተኞች ላይ በተሰማሩ ሰራተኞች ላይ አፈር ተደርምሶ ጉዳት ደርሷል።

በዚህም በአምስት ሰራተኞች ላይ ቀላል ጉዳት ሲደርስ የአፈሩ የተደረመሰበትን አንድ ሰራተኛ የማውጣት ስራ እየተከናወነ እንደሆነ ይገኛል ሲል #ኢብኮ ዘግቧል።

የኮንስትራክሽን ደህንነት አጠባበቅ ችግር ለአደጋው መንስኤ እንደሆነ ሰራተኞቹ የተናገሩ ሲሆን የህንፃውን የፍሳሽ ማስወገጃ ኮንትራት ወሰዶ እያከናወነ የሚገኘው የደበበ ክንፈ ህንፃ ስራ ተቋራጭ ኢንጂነሮች በበኩላቸው አደጋው በአጋጣሚ የደረሰ እንደሆነ ገልፀዋል።

@tikvahethmagazine
29.9K viewsedited  14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 17:31:22
#CrohnsandColitisEthiopia #TikvahEthiopia

በኢትዮጵያ ስለ አንጀት ቁስለት ህመም እንዲሁም ተያያዥ የጤና ጉዳዮች ላይ የሚሰራው በክሮንስ እና ኮላይተስ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር አንጀት ቁስለትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን ለማድረስ ተስማምተዋል።

ክሮንስ እና ኮላይተስ ኢትዮጵያ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በጉዳዩ ላይ የተለያዩ መረጃዎችንና ውይይቶችን በ Tikvah Magazine ቻናል ላይ ይዞላችሁ ይቀርባል። ለሚኖሯችሁ ጥያቄዎች የባለሞያ ምላሾችንም ያደርሳል።

ዘወትር ዕሮብ በክሮንስ እና ኮላይተስ ኢትዮጵያ ተዘጋጅተው የሚቀርቡ መረጃዎችን መከታተልና ጥያቄዎችንና ተሞክሮዎችን ማድረስ እንዲሁም ጠቃሚ መረጃዎችን ከድርጅቱ ድረገጽ ( http://ibdeth.org ) ላይ ማግኘት ይችላሉ።

@tikvahethmagazine @ibdeth
28.2K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 17:30:53
#ልባምሕይወት

ልባም ሕይወት የአዕምሮና ራስን የማሳደግ ስልጠና 6ኛ ዙር ኦንላይን ምዝገባ ተጠናቆ ስልጠና ሊጀመር ነው።

ሆኖም ቀሪ ባሉት የተወሰኑ ቦታዎች ሰልጣኞችን መቀበል እንፈልጋለን። ስልጠናው ከግንቦት 23 እስከ ሰኔ 25 ይሰጣል።

ለአምስት ሳምንታት፣ በሳምንት ሦስት ቀናት፣ ምሽት ከ3:00 - 5:00 ሰዓት በሚሰጠው የአዕምሮና ራስን የማሳደግ ስልጠና በመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ወይም ቴሌግራም ቁጥር +251974046870 ይደውሉ ወይም ስምዎን ቴክስት ያድርጉ




https://t.me/libamhiwot
24.5K views14:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 15:53:53
ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የአለም ዋንጫን እንዲመሩ ከተሾሙ ዳኞች ውስጥ አለመካትቱ ታውቋል።

በኳታር አዘጋጅነት በ 2022 ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ፊፋ 36 ዋና ዳኞችን 69 ረዳት ዳኞችን እና 24 የቫር ዳኞችን ውድድሩን እንዲመሩ መሾሙን አስታውቋል።

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ፊፋ የአለም ዋንጫን እንዲመሩ ከሾማቸው ዳኞች ስም መካከል #አለመካትቱ ታውቋል።

ፊፋ ለመጀመሪያ ጊዜ በኳታር አዘጋጅነት በሚካሄደው የአለም ዋንጫን ላይ ሶስት ዋና ሴት ዳኞችን እና ሶስት ረዳት ሴት ዳኞችን ውድድሩን እንዲመሩ መምረጡ ተገልጿል ።

የአለም ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲመሩ ከተመረጡ ሶስት ሴት ዳኞች መካከል አንዷ ሩዋንዷዊቷ ሳሊማ ሙካንሳንጋ መሆኗ ተዘግቧል።

አፍሪካን ወክለው የአለም ዋንጫን እንዲመሩ የተመረጡ ስድስት ዋና ዳኞች ሳሊማ ሙካንሳንጋ ፣ ጃኒ ሲካዝዌ ፣ ባካሪ ጋሳማ ፣ ቪክቶር ጎሜዝ ፣ ማጉዬቴ ኒዳዬ እና ሙስጣፋ ጎርባል መሆናቸው ተነግሯል።

Via @tikvahethsport

@tikvahethmagazine
25.8K viewsedited  12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ