Get Mystery Box with random crypto!

5 ሺህ ሄክታር ስፋት ያለው የአባያ ሃይቅ ክፍል በእምቦጭ ተወሯል ተባለ የደቡብ ክልል የአከባቢና | TIKVAH-MAGAZINE

5 ሺህ ሄክታር ስፋት ያለው የአባያ ሃይቅ ክፍል በእምቦጭ ተወሯል ተባለ

የደቡብ ክልል የአከባቢና ደን ባለስልጣን የብዘሃ ህይወት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ኃላፊ አቶ መላኩ ባፋ ፥ እምቦጭ አረም የአባያ ሀይቅን በስፋት እያጠቃ መሆኑን ገልፀው፥ አረሙን ለማጥፋት የሚያስችሉ ስራዎችና ሙከራዎች በሰው ጉልበትና በመሳሰሉት ለመግታት ጥረት ቢደረግም ሊሳካ አልቻለም ብለዋል፡፡

በዚህም በሀይቁ ላይ ያለውን ብዘሃ ሕይወት በማይጎዳ መልኩ አረሙን የማጥፋት ዘመቻ ለማካሄድ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አረሙ በፍጥነት ካልተወገደ ከሀይቁ በሚገኝ ገቢ የሚተዳደሩትን በርካታ የሕብረተሰብ ክፍሎችን ገቢ በማሳጣት ሊጎዳ እንደሚችል ተገልጿል።

የእንቦጩ መስፋፋት ከኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ተባብሮ ለመስራት እንዲያስችል ከስምጥ ሸላቆ ተፋሰስ ባለስልጣን ጋር በጥምረት ለመስራት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ሃይቁ በውስጡ ከ54 በላይ ብዘሃ ሕይወትን የያዘው የአባያ ሀይቅ በዓመት ከ4 ሺህ ቶን በላይ ዓሳ የማምረት አቅም ያለውና ዓዞን ጨምሮ በነጭ ሣር ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ያሉ የዱር እንስሳትም የህልውናቸው መሰረት መሆኑ ከደ.ሬ.ቴ.ድ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

@tikvahethmagazine