Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Digitalmarketing
Cloudbridge
Traininginstitute
Safaricomethiopia
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.61K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 250

2022-05-19 11:24:11
ዛሬ ዓለም አቀፍ ደረጃ የአንጀት ቁስለት ህመም ቀን ተከብሮ ይውላል።

ዛሬ ዓለም አቀፍ የአንጀት ቁስለት ህመም ቀን "የአንጀት ቁስለት ህመም የእድሜ ገደብ የለውም" በሚል መሪ ቃል በመላው አለም ስለ አንጀት ቁስለት በማስተማር እና ከዚህ ቀደም ባሉ መረጃዎች መሰረት ህመሙ በሁሉም የእድሜ ክልሎች ውስጥ ሊከሰት እንደሚችል ሆኖም ተጨማሪ ምርምሮች በዘርፉ እንደሚያስፈልጉ መረጃን በመስጠት ይከበራል፡፡

የአንጀት ቁስለት ህመም ቀን እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር በግንቦት 19 ቀን 2010 በአንጀት ህመም ታካሚዎች የተጀመረ ሲሆን፤ የዘንድሮው የአንጀት ቁስለት ህመም ቀን በአንጀት ህመም ታካሚዎች በሚመሩ ድርጅቶች በ50 ሀገራት ከአውሮፓ ክሮንስ እና ኮላይተስ ማህበር ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ይከበራል፡፡

በኢትዮጵያ የአንጀት ቁስለት ህመም ቀን የሚከበረው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን ይህም በክሮንስ እና ኮላይተስ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት አስተባባሪነት የተለያዩ ግንዛቤዎችን በመስጠት ይከበራል።

በፈረንጆቹ ጥቅምት 21 2019 መቀመጫውን በኒወርክ እና ቤጂንግ ባደረገው በላንሴት የህክምና ተቋም የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው ከ1990 እስከ 2017 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የአንጀት ቁስለት ህመም ታካሚዎች ቁጥር ከ3.7 ሚሊዮን ወደ 6.8 ሚሊዮን አሻቅቧል፡፡ ይህም የ85.1% ጭማሬ አሳይቷል።

በሃገራችን የአንጀት ቁስለት ህመም ታማሚዎች ቁጥርም እየጨመረ ይገኛል፡፡ ስለ የአንጀት ቁስለት ህመም እና ስለ ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች ማወቅ ህመሞቹ ከመከሰታቸው በፊት ቀድሞ ለመከላከል እንዲሁም ከአንጀት ቁስለት ህመም ጋር የምንኖር ከሆነም ስለ ህመማችን ይበልጥ ለማወቅ እና የጤና ሁኔታችንን ለማሻሻል አስፈላጊውን እርምጃ እንድወስድ ይረዳናል፡፡ 

@tikvahethmagazine
24.8K viewsedited  08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 22:12:12
በደብረ ብርሃን በ150 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚኒሊክ አረንጓዴ ልማት ፓርክ ሊገነባ ነው፡፡

በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በከተማው በቀድሞ 01 ቀበሌ አንኮበር መገንጠያ አካባቢ በ150 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ ያለውን 'የሚኒሊክ አረንጓዴ ልማት ፓርክ' ግንባታ ዲዛይን አስገምግሟል፡፡

ፓርኩ ሙዝየም፣ ኤግዚቪሽን ሴንተር፣ አንፒ ቲያትር፣ እና ሌሎች ለመዝናኛ እና ለጉብኝትአገልግሎት የሚሆኑ ለአዋቂና ለህጻናት በተለያየ መልኩ የሚዋቡ የአረንጓዴ ቦታዎች ጭምር የተካታተበት መሆኑን የአማካሪ ድርጅቱ አርክቴክት ሰይፈሚካኤል የማታ አብራርተዋል፡፡

ከተሳታፊዎች በፓርኩ ከሚቆመው የሚኒሊክ ሀውልት ውጭ ሌሎች ታሪካዊ በግርግዳዎች ላይ የሚቀረፁ ምስሎች ቢኖሩ፣ የመዝናኛ ማሪፊያ ቦታዎች ቢካተቱብትና ሁሉም ነገሮች ታሪክን የሚያስተምሩ ቢሆኑ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል።

@tikvahethmagazine
11.9K viewsedited  19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 17:03:52
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በ10 ወራት ለ29 ሺሕ 942 ገንቢዎች የግንባታ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በበጀት ዓመቱ አስር ወራት፦

- 10 ሺሕ 783 የፕላን ስምምነት፤

- 3 ሺሕ 985 አዲስ ግንባታ ፈቃድ፤

- 968 የማሻሻያ የግንባታ ፈቃድ፤

- 174 ቀደም ብለው ለተገነቡ ህንፃዎች የግንባታ ፈቃድ፤

- 1 ሺሕ 27 ህንፃዎች የማራዘሚያ ፈቃድ፤

- 11 ሺሕ 418 ግንባታዎች የእድሳት ፈቃድ ተሰጥቷል።

@tikvahethmagazine
23.1K viewsedited  14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 17:00:38
በቸኮሌት መጠቅለያ የኮኬን ዕፅ ይዞ ከኢትዮጵያ ለመውጣት የሞከረው ግለሰብ ተፈረደበት።

አርፋን ሀይደር የተባለው የውጭ አገር ዜጋ መስከረም 11 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 2፡00 ሰዓት ሲሆን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ከአዲስ አበባ ወደ ኳታር ሃገር ዶሃ ለመጓዝ ሲል በተደረገበት ፍተሻ በእጁ በያዘው ቦርሳ ውስጥ በቸኮሌት መጠቅለያ የተጠቀለለ 5 ሺህ 200 ግራም የሚመዝን የኮኬን ዕፅ ይዞ መገኘቱ ተመላክቷል፡፡

ተከሳሹ በፈፀመው የናርኮቲክ ሳይኮትሮፒክ መድሐኒቶች ወይም ዕፆችን ይዞ መገኘት ወንጀል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳች ዐቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ክስ ተመስርቶበታል።

ተከሳሽ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ክሱ ደርሶትና ተነቦለት የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ” እኔ ድርጊቱን አልፈፀምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም ”ሲል ቃሉን በመስጠት ክዶ ተከራክሯል ።

ዓቃቤ ህግ በበኩሉ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ለፍርድ ቤቱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር የሰው߹የሰነድና ኢግዚቢትነት አቅርቦ በበቂ ሁኔታ ለችሎቱ በማስረዳቱ ግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፏል ።

በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ከዚህ በፊት የጥፋተኝነት ሪከርድ የሌለበት በመሆኑ አንድ የቅጣት ማቅለያ በመያዝ ተከሳሽ በ12 ዓመት ፅኑ እስራትና በ75 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ መወሰኑን ፍትሕ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

@tikvahethmagazine
18.8K viewsedited  14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 16:59:44
ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ አደገኛ ዕፅ ማስተላለፊያ ዋሻ ተገኘ።

ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ አደገኛ ዕፅ ለማስተላለፊያነት የሚያገለግለውና 531 ሜትር የሚረዝመው ዋሻ መገኘቱ ተገልጿል። ዋሻው ሐዲድ የተዘረጋለት፣ የአየር መቆጣጠሪያ ስርዓት (ቬንትሌሽን) የተገጠመለት ሁሉን ያሟላ ነው ተብሏል።

የሳውዘርን ካሊፎርኒያ አውራጃ የአሜሪካ አቃቢ ሕግ ጽሕፈት ቤት ዋሻው ከመሬት 18 ሜትር ጠልቆ የሚገኝ እና አንድ ሜትር መጠነ ዙርያ (ዲያሜትር) እንዳለው የገለጸ ሲሆን በዚህ ዋሻ ኮኬይን፣ ሜታመፌታሚን እና ሄሮይን የተባሉ ዕፆችን ሊያስተላልፉ የነበሩ ስድስት ሰዎችንም በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ገልጿል።

ወደ ዋሻው የሚጠጉ መኪኖች ላይ በተደረገ ፍተሻ አደገኛ ዕፅ መገኘቱን ተከትሎ በተደረገ ምርመራ አንድ መጋዘን የተገኘ ሲሆን መጋዘኑ ውስጥ ደግሞ ድንበሩን ተከትሎ የተቆፈረ ምሥጢራዊ ዋሻ መግቢያን አግኝተዋል።

የአቃቢ ሕግ ጽሕፈት ቤት እንደሚለው 799 ኪሎ ግራም ኮኬይን፣ 74 ኪሎ ግራም ሜታፌታሚን እና 1.5 ኪሎ ግራም ሄሮይን በቁጥጥር ሥር ውሏል።

ዕድሜያቸው ከ31 እስከ 55 የሚሆኑት እነዚህ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎች ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ዕድሜ ይፍታህ ሊፈረድባቸው ይችላል። ከዚህ በላይ የ1 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ቅጣትም ይጣልባቸዋል።

በካሊፎርኒያ ለመጨረሻ ጊዜ እንዲህ ያለ ምሥጢራዊ ዋሻ የተገኘው ከሁለት ዓመት በፊት ነበር። ያ ዋሻ 1ሺህ 313 ሜትር ርዝመት የነበረው ሲሆን በርዝመቱም ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ነው። እንደ አውሮጳዊያኑ ከ1993 ጀምሮ 90 የሚሆኑ አደገኛ ዕፅ ማስተላለፊያ የምድር ውስጥ ድብቅ ዋሻዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል። (BBC)

@tikvahethmagazine
16.0K viewsedited  13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 16:59:19
#ልባምሕይወት

ልባም ሕይወት የአዕምሮና ራስን የማሳደግ ስልጠና 6ኛ ዙር ኦንላይን ምዝገባ ተጠናቆ ስልጠና ሊጀመር ነው።

ሆኖም ቀሪ ባሉት የተወሰኑ ቦታዎች ሰልጣኞችን መቀበል እንፈልጋለን። ስልጠናው ከግንቦት 23 እስከ ሰኔ 25 ይሰጣል።

ለአምስት ሳምንታት፣ በሳምንት ሦስት ቀናት፣ ምሽት ከ3:00 - 5:00 ሰዓት በሚሰጠው የአዕምሮና ራስን የማሳደግ ስልጠና በመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ወይም ቴሌግራም ቁጥር +251974046870 ይደውሉ ወይም ስምዎን ቴክስት ያድርጉ




https://t.me/libamhiwot
15.2K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 16:59:19
ቻው! ዝቅተኛ ግፊት!

የሆቴሎቻችሁ ደንበኞች ከቧንቧ፣ ከሻወር እና ከመታጠቢያ በሚመጣው ውሃ እየረኩ ነው? ምቾታቸውን ሊመለስ የሚችለውን የውሃ ግፊት መጨመሪያ Scala 2 Booster pump እስከ G+4 ድረስ ላሉ ህንፃዎቻችሁ አሁኑኑ ያስገጥሙ።

Solution matters!
+251970710024 / +251970710017

@SinopiaImpex
15.7K viewsedited  13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 15:28:42
ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ስርዓትን ለማሳለጥ ይረዳል የተባለው COMESA ተግባራዊ ሊደረግ ነው።

ኢትዮጵያ የፈረመችው እና ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ስርዓትን ለማሳለጥ የሚያስችለው የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ(COMESA) ቀጠናዊ የጉምሩክ ዋስትናን ለመተግበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ተገለጸ፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን የትራንዚት እና መጋዘን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወጋየሁ አዳሙ፣ ቀጠናዊ የጉምሩክ ትራንዚት ዋስትና ከዚህ በፊት በየሀገራቱ የሚደረገውን ተደጋጋሚ የእቃ ዋስትና የሚያስቀር እና እቃዎች በአንድ ዋስትና ብቻ እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል አሰራር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

"ኢትዮጵያን ጨምሮ በ13 አባል ሀገራት መካከል የተፈረመው አዲሱ የጉምሩክ ትራንዚት ዋስትና ወጭዎችን የሚቀንስ፣ የትራንዚት ጊዜን የሚያሳጥር፣ የእቃ አወጣጥ ሂደቶችን የሚያፋጥን በአጠቃላይ ፈጣን የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖር የሚያስችል ነው“ ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡

አቶ ወጋየሁ አክለውም፣ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝድ እና ከጉምሩክ የመረጃ ቋት ጋር የሚተሳሰር በመሆኑ ለጉምሩክ አስተላላፊዎች ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ እንደሚሰጥም አስረድተዋል፡፡

ቀጠናዊ የጉምሩክ ዋስትናን ለመተግበር ከኢንሹራንስ፣ ከባንኮች እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተከታታይ የሆኑ ውይይቶች እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚሰጡም መጠቆማቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine
18.7K viewsedited  12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 15:11:58 #Update : በኢድ- አልፈጥር በዓል ላይ የጭስ ቦንብ በማፈንዳት ወንጀል የተጠረጠረው የፖሊስ አባል ፍርድ ቤት ቀረበ። የፌደራል ፖሊስ አድማ ብተና ዘርፍ አባል የሆነው ኮንስታብል አንቡላ ኡቴ ከትናንት በስቲያ ሰኞ በአዲስ አበባ በተከበረው የኢድ- አልፈጥር በዓል ላይ በመስቀል አደባባይ የሰማዓታት መታሰቢያ ሙዚየም አካባቢ ከፈነዳው የአድማ በታጭ የጭስ ቦንብ ጋር ተያይዞ በቁጥጥር ስር ውሎ በፌደራል…
18.8K viewsedited  12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 13:06:49
በሚቀጥሉት ሦስት ወራት 150 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እንዲገባ ተወስኗል።

መንግስት በሰጠው አቅጣጫና የሀገሪቱ ብሄራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ቡድን በወሰነው መሰረት የኑሮ ውድነትን ለማሻሻልና ገበያውን ለማረጋጋ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት 150 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እንዲገባ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአሁኑ ጊዜም 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ነው። ከዚህ ውስጥ 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ለህብረተሰቡ እየተከፋፋለ ሲሆን 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ደግሞ በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ተጠቃሎ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ አስረድተዋል፡፡

ድፍድፍ ዘይት ከውጭ አስመጥተው በሀገር ውስጥ ለሚያመርቱ ሶስት ፋብሪካዎችም ምርቶቻቸውን ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ የውጭ ምንዛሬ የተመቻቻላቸው ሲሆን የምግብ ዘይት እጥረትን ለዘላቂነት ለመፍታትም ለሌሎች አቅራቢዎችም ዘይት ከውጭ አስመጥተው ለመንግስት እንዲሸጡ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑንም ተገልጿል፡፡

መንግስት ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት የምግብ ዘይት ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ በማድረጉ 23 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ያጣ ሲሆን ለነዳጅ የ100 ቢሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

@tikvahethmagazine
21.6K viewsedited  10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ