Get Mystery Box with random crypto!

በሚቀጥሉት ሦስት ወራት 150 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እንዲገባ ተወስኗል። መንግስት በ | TIKVAH-MAGAZINE

በሚቀጥሉት ሦስት ወራት 150 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እንዲገባ ተወስኗል።

መንግስት በሰጠው አቅጣጫና የሀገሪቱ ብሄራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ ቡድን በወሰነው መሰረት የኑሮ ውድነትን ለማሻሻልና ገበያውን ለማረጋጋ በሚቀጥሉት ሶስት ወራት 150 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ከውጭ እንዲገባ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአሁኑ ጊዜም 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ እየገባ ነው። ከዚህ ውስጥ 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ ለህብረተሰቡ እየተከፋፋለ ሲሆን 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ደግሞ በሚቀጥሉት ሶስት ሳምንታት ውስጥ ተጠቃሎ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ አስረድተዋል፡፡

ድፍድፍ ዘይት ከውጭ አስመጥተው በሀገር ውስጥ ለሚያመርቱ ሶስት ፋብሪካዎችም ምርቶቻቸውን ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርቡ የውጭ ምንዛሬ የተመቻቻላቸው ሲሆን የምግብ ዘይት እጥረትን ለዘላቂነት ለመፍታትም ለሌሎች አቅራቢዎችም ዘይት ከውጭ አስመጥተው ለመንግስት እንዲሸጡ ፈቃድ የተሰጣቸው መሆኑንም ተገልጿል፡፡

መንግስት ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታት የምግብ ዘይት ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ በማድረጉ 23 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ያጣ ሲሆን ለነዳጅ የ100 ቢሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

@tikvahethmagazine