Get Mystery Box with random crypto!

#ለጥንቃቄ ' ትላንት ማታ ሚያዚያ 13 ከምሽቱ 2:30 አካባቢ እኔና ባለቤቴ ዘመድ ጥየቃ ቆይተን | TIKVAH-MAGAZINE

#ለጥንቃቄ

" ትላንት ማታ ሚያዚያ 13 ከምሽቱ 2:30 አካባቢ እኔና ባለቤቴ ዘመድ ጥየቃ ቆይተን ጉዞአችንን ከቄራ ወደ ወሎ ሰፈር አድርገን ስንሄድ ድንገት ጎተራ ማሳለጫ መንገድ ላይ አስደንጋጭ ክስተት ተመለከትን።

ጎተራ ማሳለጫ በላይኛው መስመር አንድ ሰው ከሶስት ሰዎች ጋ ሲታገል ተመለከትን። ቦታው እና ሁኔታው እጅግ አደገኛ ነው።

እግረኛ የማይጓዝበት እና መኪኖች በፍጥነት የሚያልፉበት መንገድ ከመሆኑ የተነሳ ለኛ በዚህ ሁኔታ መቆም እጅግ ፈተኝ ነበር።

ነገር ግን ቢያንስ የተጎጂው ሰው ሕይወት ለማትረፍ በቦታው ቀድመን የደረስን እኛ ብቻ መስሎ ስለታየን እና መኪና አስቁሞ በዚህ ልክ ይዘርፋሉ ብለን ስላልገመትን 7 ሜትር በሚሆን ርቀት ላይ ቆምን።

ይህን ሰው አንዱ መሬት ላይ አስተኝቶ አንቆታል ፤ ሌላኛው በተደጋጋሚ ይደበድበዋ አንደኛው በእጁ በያዘው ስለት ያለው መሳርያ ደጋግሞ ሲወጋው ተመለከትን።

ሰውዬው በዚህ መሀል ከፍ ባለ ድምፅ የሰቀቀን ጩኸት ያሰማ ነበር።

ከመኪናችን መውረድ ስለማንችል ያለን አማራጭ ሀዛርድ አብርተን ያለማቋረጥ ክላክስ ማድረግ ብቻ ነበር። ከኋላ ሌሎች መኪኖች ደረሱብን እነሱም ሁኔታው በግልፅ ስለሚታይ ከመኪናቸው ሳይወርዱ ያለማቋረጥ ክላክ ማድረግ ጀመሩ።

ያኔ ነው ከሌቤቹ/ነብሰ በላዎቹ አንዱ ወደ እኛ መቶ ጮኸብን በእግሩ መኪናውን ደበደበ ፊቱ በደንብ ይታያል። ሌሎች 2ቱ ሰውዬውን ይታገሉታል።

ሪስክ ወስጄ መኪናዬን በጣም ሳቀርብባቸው ሰውዬውን ለቀውት ሶስቱም መንገድ ዳር ያስቀመጡትን ድንጋይ አንስተው ሲያስፈራሩኝ መኪናዬ እንዳይጎዳብኝ ፈጣሪን እየተማፀንኩ በፍጥነት አለፍኩ። ነገር ግን በቀላሉ መስታወቱ ላይ ጉዳት ማድረስ ይችሉ ነበር።

ሰውዬውም ከወደቀበት ተነስቶ በተቃራኒ መስመር እየተንገዳገደ ለመሸሽ ሲሞክር በስፖኪዬ ተመለከትኩት።

ክስተቱን መረጃ ለመስጠት ለፌዴራል ፖሊስ ስንደውል አዲስ አበባ ፖሊስ ጋር መረጃ ስጡ ባሉን መሰረት በ +251111110111 ደውለን አሳወቅን። ቤት ደርሰን ሁኔታው በጣም ስለረበሸን በድጋሚ ስንደውል ፖሊሶች ተልከው " በአከባቢው ምንም የተፈጠረ ነገር የለም " ተባልን።

ይህን ከሰማን በኋላ ሁለት ሀሳብ መጣብን ፤
° ምናልባት ተበዳዩ ሰውዬ የነሱ ተባባሪ እና ግርግር ፈጥረው ከመኪና የወረደ አሽከርካሪ ላይ ጉዳት ለማድረስ እና መኪና እና ሌሎች ንብረቶችን ለመስረቅ ታቅዶ የተሰራ ይሆን ?
° ምናልባት ያለምህረት ሲደበድቡት ሱወጉት እውነትም ተበዳይ ይሆን ?

የሚመለከተው የፀጥታ አካል ትኩረት ሰጥቶ ቢሰራበት እንለለን። የደህንነት ካሜራዎችም የህብረተሰቡን ስጋት መከታተል አለባቸው።

ጎተራ አከባቢ እና ሌሎች ተጋላጭ ቦታዎች ላይ በምሽት የምታሽከረክሩት ጥንቃቄ አይለያችሁ!

(አንተነህ ክ.)

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine