Get Mystery Box with random crypto!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የቴሌግራም ቻናል አርማ zena24now — ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የሰርጥ አድራሻ: @zena24now
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.23K
የሰርጥ መግለጫ

The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-06 19:58:33 ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት "በኢትዮጵያ ልክ እድገት ያረጋግጣል ተብሎ የተተነበየ ሀገር የለም"? ኢትዮጵያ ፋክት ቼክ ሰፋ ያለ ማጣራትን በዛሬዉ የጠ/ሚ አብይ የምክር ቤት ዉሎ ላይ አደርጓል

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ዛሬ በፓርላማ ተገኝተው ከህዝብ እንደራሴዎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ዳታዎችን ጠቅሰው ነበር።

ጠ/ሚሩ በዚሁ ንግግራቸው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት አምና፣ ማለትም እ.አ.አ በ 2022 6.4% እንደነበር፣ ዘንድሮ ቢያንስ 6.1% እንደሚያድግ እንዲሁም በቀጣዩ አመት ተመልሶ 6.4% ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

ይሁንና ጠ/ሚር አብይ በዚሁ ንግግራቸው ላይ "በ Sub-Sahara (ከሰሀራ በታች ካሉ ሀገራት) በኢትዮጵያ ልክ እድገት ያረጋግጣል ተብሎ የተተነበየ ሀገር የለም፣ በአለምም ፈጣን እድገት እያመጡ ካሉ ጥቂት ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ነች" ብለዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ የ IMF ዳታ ላይ ዳሰሳ አድርጓል።

የ IMF ዳታ እንደሚያመለክተው ዘንድሮ (እ.አ.አ በ2023) ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ያሉት ከሰሀራ በታች ያሉት የአፍሪካ ሀገራት በቅደም ተከተል እነዚህ ናቸው:

1. ሴኔጋል- 8.3%
2. ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ- 6.3%
3. ርዋንዳ እና አይቬሪ ኮስት- 6.2%
4. ኢትዮጵያ እና ኒጀር- 6.1% ናቸው።

በቀጣዩ አመት ከፍ ያለ እድገት ያስመዘግባሉ የተባሉት ሀገራት ደግሞ:

1. ኒጀር- 13%
2. ሴኔጋል- 10.6%
3. ርዋንዳ- 7.5%
4. ሞዛምቢክ- 8.2%
5. አይቬሪ ኮስት- 6.6%
6. ኢትዮጵያ- 6.4% ናቸው።

ሪፖርቱን በዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል: https://www.imf.org/en/Publications/REO/SSA/Issues/2023/04/14/regional-economic-outlook-for-sub-saharan-africa-april-2023

በዚህም መሰረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ "በኢትዮጵያ ልክ እድገት ያረጋግጣል ተብሎ የተተነበየ ሀገር የለም" የሚለው ንግግር የተሳሳተ መሆኑን ማየት ይቻላል።

በተጨማሪም ኢንተርኔት በፈረንሳይ እንዲቋረጥ ተደርጓል ሲሉ ጠ/ሚኒስትሩ ተናግረዉ ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ በፈረንሳይ ኢንተርኔት እንዲቋረጥ ስለመወሱ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚዲያን በተመለከተ ማብራሪያ በሰጡበት ንግግራቸው “በኢትዮጵያ ብቻ አይደለም፤ ሰሞኑን ሰምታችኋል ፈረንሳይ ችግር ነበር፣ በአውሮፓ ምድር በፈረንሳይ አገር ለመጀመሪያ ጊዜ ኢንተርኔት እንዲቋረጥ ተወስኗል። የአፍሪካ የተለመደ ነው…” ሲሉ ተደምጠዋል።

ሆኖም ኢትዮዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንሳይ አገር ለመጀመሪያ ጊዜ ኢንተርኔት እንዲቋረጥ ተወስኗል በማለት የተናገሩት የተሳሳተ መሆኑን አረጋግጧል።

ነገሩ እንዲህ ነበር:
በፈረንሳይ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ስምንና አርማ በመጠቀም የተጻፈ አንድ ደብዳቤ ባሳለፍነው ዕሁድ በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጨ። ደብዳቤው በሀገሪቱ ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በኢንተርኔት ላይ እቀባ መጣሉን የሚገልጽ ነበር።

ሆኖም የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስትር ወዲያኑ ባወጣው መግለጫ የተሰራጨው ደብዳቤም ሆነ በኢንተርኔት ላይ እቀባ እንዲጣል ውሳኔ ተላልፏል የሚለው መረጃ ሀሠተኛ መሆኑን አስታውቋል።

ኤፒን ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ የመረጃ አጣሪ ተቋማትም የመረጃውን ሀሠተኝነት በተመለከተ ዘገባ ሰርተዋል።

በተጨማሪም ፕሬዝደንት ማክሮን ከአንድ ቀን በፊት ከከንቲባዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በኢንተርኔት ላይ እቀባ አለመደረጉን አረጋግጠዋል። ሆኖም ነገሮች ሲረጋጉ ኢንተርኔትን ማቋረጥን የተመለከቱ ደንቦች ሊወጡ ይችላሉ ሲሉ ተናግረዋል።

Via ኢትዮ ፋክት ቼክ
#ዳጉ_ጆርናል
2.1K viewsBeⓒk, edited  16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 19:58:23
2.0K viewsBeⓒk, 16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 16:07:09
በሐመር ወረዳ 65 ከመቶ የሚሆነው የበልግ ሰብል በተከሰተ የዝናብ እጥረት ከጥቅም ውጭ መሆኑ ተነገረ

በሐመር ወረዳ ምርት ለመስጠት ደርሶ የነበረ የበልግ ሰብል በተከሰተ የዝናብ እጥረት 65 ከመቶ የሚሆነው ሰብል በፀሐይ ተቃጥሎ ከጥቅም ውጭ እንደሆነ ተነግሯል ።በወረዳው ከአራት ዓመታት በላይ ዝናብ ሳይጥል መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ከወራት በፊት ዝናብ መጣሉን ተከትሎ ከ7200 ሄክታር መሬት በላይ በበልግ ሰብል መሸፈኑ ተገልጿል ።

ከዚህ ውስጥ በተከሰተው የዝናብ እጥረት በበልግ በሁሉም የሰብል አይነቶች ከተሸፈነው መሬት ውስጥ 65 ከመቶ የሚሆነው ሰብል ምርት እንደማይሰጥ የሐመር ወረዳ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አ/ቶ አወቀ ንጋቱ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

በፀሐይ የተቃጠለው ሰብል ምንም አይነት ምርት እንደማይሰጥ በእርሻ ዘርፍ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት መረጋገጡን ገልጸዋል ። በዚህ ምክንያት አርሶ አደሮች ሰብሉን ለእንስሳት መኖ እንዲውል ማድረጋቸው ተነግሯል ።

በወረዳው ከፊል አርሶ አደር እና አርብቶ አደር የማህበረሰብ ክፍል የሚገኝ ሲሆን ለተከታታይ ዓመታት በሰው እና በእንስሳቱ ላይ ድርቅ መፈራረቁን ተናግረዋል ። በዚህ ዓመት በተገኘው ዝናብ ሰፊ ስራ ቢሰራም በተከሰተው የዝናብ እጥረት ምክንያት ምርት ሊሰጡ የተቃረቡ ሰብሎች በፀሐይ መቃጠላቸው የማህበረሰቡን ቅስም መስበሩን አ/ቶ አወቀ ጨምረው ተናግረዋል ።

በአበረ ስሜነህ
#ዳጉ_ጆርናል
2.9K viewsTrue, 13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 15:11:17
በገዳም ለሚገኙ ሴት መነኮሳት የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ ማሰባሰብ ተጀመረ

የተፈጥሮ ፀጋ ለገዳማዉያን ከራሴዉ ለራሴዉ በሚል መሪ ቃል በጎንደር ለሚገኘዉ በሙት አንሳ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም እና በሌሎል ተመሳሳይ ከፍተኛ ችግር ባለባቸዉ ገዳማት ለሚገኙና በተፈጥሮ ምክንያት ንፅህና መጠበቂያ በማጣት ለተቸገሩ ሴት መነኮሳት የእርዳታ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ተጀምሯል።

ለዓለም ሞተዉ በክርስቶስ ፍቅር ህያዉ የሆኑት ገዳማዉያን መናንያን ከዓለማዊ ፈተና በላይ የተፈጥሮ ፀጋ እንቅፍት እየሆነባቸዉ መሆኑን በማንሳት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮችና መላዉ ኢትዮጵያዉያን ድጋፍ እንዲያድርጉ ጥሪ መቅረቡ ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

በደብረ ቁስቋም የበጎ አድራጎት ተቋም አስተባባሪነት የተዘጋጀዉ ይህ መርሃ ግብር ከ40 በላይ የጤና ባለሙያዎች ለገዳማዉያኑ ህክምና እንዲያደርጉ ለማድረግና በሚቀጥሉት 6 ወራት ለ 2000 ሴቶች 12ሺ የንፅህና መጠበቂያ ምርቶችና 1ሺ ዳይፐሮች ለማቅረብ መታቀዱ በጋዜጣዊ መግለጫዉ ተጠቅሷል።

በዓይነት ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ከየካ ፓሊስ መምርያ ፊት ለፊት እልፍ ፀጋ ማዕከል በአካል በመገኘት ድጋፍ ማድረግ እንደሚችሉ ተገልጿል። በገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ በደብረ ቁስቋም የበጎ አድራጎት ተቋም ይፋዊ የንግድ እና የአቢሲንያ  የባንክ አካዉንቶች እንዲሁም በዉጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ በተዘጋጀዉ ጎ ፈንድ ሚ እጃቸዉን መዘርጋት እንደሚችሉ መገለፁን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

በአብርሃም ፍቅሬ
#ዳጉ_ጆርናል
2.9K viewsTrue, 12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 14:06:24
ለ2016 በጀት ዓመት የተዘጋጀው የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ጸደቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2016 በጀት ዓመት የተዘጋጀውን 801 ነጥብ 65 ቢሊዮን ብር የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።

በጀቱ የጸደቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 28ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት ሲሆን የምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 ዓ.ም የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት ዝግጅትን አስመልክቶ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርቧል።

የ2016 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት ረቂቅ በጀት 801 ነጥብ 65 ቢሊዮን ብር እንዲሆን የተያዘ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 203 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብሩ ለካፒታል በጀት ተመድቧል፡፡

369 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ ወጪ፤ 214 ነጥብ 07 ቢሊዮን ብሩ ደግሞ ለክልል መንግስታት ድጋፍ እንደሚከፋፈል ተገልጿል።

ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ደግሞ 14 ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲሆን የፀደቀው በጀት ከ2015 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ15 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አለው ተብሏል።

#ዳጉ_ጀርናል
3.0K viewsBeⓒk, 11:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 12:27:08
ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ የሰሜኑ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት ጦርነቱ እንዲቆም መግለጫ ባለመስጠቱ እና በወቅቱ በትግራይ ክልል ተገኝቶ ሕዝቡን ባለመጠየቁና ባለማጽናናቱ ይቅርታ ጠየቀ

የተመረጡ ቆሞሳትን ይፋ በማድረግ የፊታችን ሐምሌ ዘጠኝ ሢመታቸዉ ይከናወናል ተብሏል


ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ልዩ ጉባኤ ማጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሚዲያዎች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በሁለት ዐበይት አጀንዳዎች መወያየቱን ገልጾ የኤጲስ ቆጶሳትን ሹመት በተመለከተ የተመረጡ ቆሞሳትን ይፋ በማድረግ የፊታችን ሐምሌ ዘጠኝ ሢመቱ እንደሚፈጸም አስታውቋል።

በሌላ በኩል በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመስጠቷ፣ በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ፣ ሊቃውንተ ቤተ
ክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣ ጦርነቱ ቁሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ መጠየቁን በንባብ ከተሰማው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።

Via ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
#ዳጉ_ጆርናል
3.1K viewsBeⓒk, edited  09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 12:15:45
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተከበሩ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለቀረቡላቸዉ በርከት ያሉ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን ለቅቀዉ የሰቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ ፤ ዳግም ምርጫም እንዲከናወንም ተጠይቀዉ ነበር።

ጠ/ሚኒስትሩ በምላሻቸዉ ምርጫ ለማከናወን ሶስት አመታትን መጠበቅ ግድ እንደሚል ተናግረዋል። በድቅድቅ ጨለማ ዉስጥ ኢትዮጵያ እንዳለች አድርጎ መሳልም ትክልል አለመሆኑን መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

#ዳጉ_ጆርናል
2.9K viewsBeⓒk, 09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 11:54:36
#ሰበር
የቤላሩስ ፕሬዝዳንት ሉካሼንኮ የዋግነር አለቃ ፕሪጎዚን ወደ ሩሲያ መመለሳቸውን ተናገሩ

የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ባለፈው ወር በሩሲያ የተፈጠረዉን ጥቃት ለማስቆም ስምምነት ላይ እንዲደረስ ማድረጋቸዉ የሚታወስ ሲሆን የሩሲያ ቅጥረኛ ቡድን ዋግነር መሪ ዬቭጄኒ ፕሪጎዚን ቤላሩስ አለመሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡ሉካሼንኮ ከቀናት በፊት ፕሪጎዚን በስምምነቱ መሰረት ወደ ቤላሩስ መምጣታቸዉን ተናግረዉ ነበር፡፡

"ፕሪጎዝሂን በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ውስጥ ናቸዉ በቤላሩስ ግዛት ዉስጥ አይደሉም "ሲሉ ሉካሼንኮ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡በሌላ በኩል የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንደተናገሩት ወደ ዩክሬን የሚላኩ የጦር መሳሪያዎች መዘግየት የመልሶ ማጥቃቱን ሂደት እንዳዘገየዉ ገልጸዋል፡፡ይህዉ መዘግየት ሩሲያ በያዘቻቸዉ የዩክሬን ግዛቶች ፈንጂን ጨምሮ መከላከያዋን እንድታጠናክር አስችሏታል ሲሉ አክለዋል።

የዩክሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኢጆር ክላይመንኮ ሩሲያ በምዕራባዊ የዩክሬን ከተማ ሊቪቭ በፈፀመችዉ የሚሳኤል ጥቃት አራት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች 32 ሰዎች ቆስለዋል።የሊቪቭ ከንቲባ አንድሪ ሳዶቪይ በጥቃቱ ወደ 60 የሚጠጉ አፓርትመንቶች እና 50 ተሽከርካሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

ጥቃቱ ባለፈው አመት ከተጀመረዉ ጦርነት በኃላ በሊቪቭ ከተማከፍተኛ የሲቪል መሠረተ ልማት ዉድመት ማስከተሉን ገልጸዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
2.8K viewsTrue, 08:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 11:50:46
ያለቀላቸዉ እና በግንባታ ላይ ያሉ የሪልስቴት እና አፓርታማ ቤቶችን የሚሻሽጠዉ "አለን ለቤቶ" ታማኝ እና የአስተማማኝ ቤቶችን መረጃ ወደ እናንተ ሲያደርስ ቆይቷል።

አሁን ደግሞ ይህ በእንዲህ እንዳለ ማንኛዉንም ቦታ ፣ ቤት እና ንብረት ለመሸጥ ካሰቡ ፤ ህጋዊ ሂደቱን ብቻ ተከትሎ ገዢዉንም ሻጩንም ባስደሰተ መልኩ ማገበያየት ጀምሯል። ለኢንቨስትመንት እና ለሌሎች ስራዎች የሚሆኑና ለመሸጥ ያሰቡት ቤት ፣ ቦታ እና ሌሎች ንብረቶች ካሉ በ 09-29-92-44-49 ላይ ይደዉሉልን።

አለን ለቤቶ ጥሩዉን ለእናንተ!
2.6K viewsBeⓒk, 08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-06 11:32:56
የህዳሴ ግድብ ሙሌት እስከ መስከረም መጀመሪያ እንደማይከናወን ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ

ኢትዮጵያ የሱዳንን እና ግብፅ ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ የህዳሴ ግድብ ሙሌቱ እስከ መስከረም መጀመሪያ እንደማታከናዉን ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም ሀምሌ አጋማሽ የግድቡን የዉሃ ሙሌት ስናከብር ነበር ያሉት ጠ / ሚኒስትሩ ዘንድሮ ግን በቂ የዉሃ መጠን ለሁለቱ ሀገራት ከደረሰ በኋላ ሙሌቱ እንደሚከናወን መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሶስተኛ ዙር ሙሌት የተከናወነ ሲሆን በዘንድሮዉ ክረምት አራተኛዉ ሙሌት ለማከናወን እቅድ ተይዞ ነበር። ሆኖም ኢትዮጵያ የሁለቱ ሀገራትን ጥያቄ በማክበር ይህን እቅድ ማራዘሟን ነዉ ጠ/ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ሱዳን እና ግብፅ በተደጋጋሚ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ዙሪያ አሳሪ ስምምነት እንዲፈጸም ፍላጎት እንዳላቸዉ ሲገለጽ ቆይቷል። በተለይም ግብፅ ለአፍሪካ ኅብረት፣ ለአረብ ሊግ፣ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና ለኃያላኑ ምዕራባውያን በተደጋጋሚ ከግድቡ ጋር በተያያዘ አቤቱታዋን ስታሰማ እንደነበር ይታወቃል።

በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል
2.7K viewsBeⓒk, 08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ