Get Mystery Box with random crypto!

በደብረ ብርሃን በ150 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚኒሊክ አረንጓዴ ልማት ፓርክ ሊገነባ ነው፡፡ | TIKVAH-MAGAZINE

በደብረ ብርሃን በ150 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚኒሊክ አረንጓዴ ልማት ፓርክ ሊገነባ ነው፡፡

በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በከተማው በቀድሞ 01 ቀበሌ አንኮበር መገንጠያ አካባቢ በ150 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ ያለውን 'የሚኒሊክ አረንጓዴ ልማት ፓርክ' ግንባታ ዲዛይን አስገምግሟል፡፡

ፓርኩ ሙዝየም፣ ኤግዚቪሽን ሴንተር፣ አንፒ ቲያትር፣ እና ሌሎች ለመዝናኛ እና ለጉብኝትአገልግሎት የሚሆኑ ለአዋቂና ለህጻናት በተለያየ መልኩ የሚዋቡ የአረንጓዴ ቦታዎች ጭምር የተካታተበት መሆኑን የአማካሪ ድርጅቱ አርክቴክት ሰይፈሚካኤል የማታ አብራርተዋል፡፡

ከተሳታፊዎች በፓርኩ ከሚቆመው የሚኒሊክ ሀውልት ውጭ ሌሎች ታሪካዊ በግርግዳዎች ላይ የሚቀረፁ ምስሎች ቢኖሩ፣ የመዝናኛ ማሪፊያ ቦታዎች ቢካተቱብትና ሁሉም ነገሮች ታሪክን የሚያስተምሩ ቢሆኑ የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል።

@tikvahethmagazine