Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.57K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 255

2022-05-14 13:09:24
በእሳት አደጋ ምክንያት የንብረት ጉዳት ለደረሰባችው በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ ተደረገላቸው።

በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በጅቡቲ ከተማ ፒካዱስ ልዩ ስሙ ፒኬ 12 አካባቢ በቅርቡ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ በንብረታቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ኢትዮጵያዊያንን ማቋቋሚያ የሚውል 3.1 ሚሊዮን በላይ የጅቡቲ ፍራንክ በኤምባሲው እና በህብረተሰቡ አስተባባሪነት ተሰብስቦ ድጋፍ ተደርጓላቸዋል።

@tikvahethmagazine
11.0K viewsedited  10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 12:46:19
#Silte

ዛሬ በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ለዝናብ እጥረት የሚሰገድ ሰላት (ሰላቱ ኢስቲስቃዕ) መሰገዱን የዞኑ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

@tikvahethmagazine
12.4K viewsedited  09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 12:45:45
#Wolkite

የወልቂጤ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ አበበ አሰፋን የከተማው ከንቲባ አድርጎ ሾሟል። አዲሱ ከንቲባም በምክርቤቱ ቀርበው ቃለ መሀላ መፈጸማቸው ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
11.3K viewsedited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 12:45:29
Sejoy Blood pressure

0911284606
    ሀኪሞን በእጆ , ጤናዎትን በየግዜዉ ሳይጨነቁ በፈለጉበት ቦታ ና ግዜ ይወቁ
የደም መጠን ሚለካ 
የልብ ምት መጠንን ሚለካ
ሰለደም ግፊት አጠቃላይ መረጃ ሚሰጥ
ዋጋ- 1900  birr
Bole medanialem
10.3K views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-14 12:45:18
የአንፖል ካሜራ lamp camera

በከፍተኛ ጥራት የሚቀርፅ Full HD ካሜራ የተገጠመለት የአንፖል ከስልኮ ጋ በ app በማገናኘት ማንኛውንም አይነት ክትትል የሚያደርጉበት የአንፖል መሰኪያ ላይ በመግጠም ብቻ ማንኛውንም እንቅስቃሴ የሚቃኙበት ለሱቅ፣ ለቤት፣ የልጆችዎን እንቅስቃሴ ያለሃሳብ የሚቃኙበት እንዲሁም አካባቢዎን ከስርቆት የሚከላከሉበት የራሱ ሳውንድ ሪከርድ እንዲሁም ሚሞሪ የሚቀበል በመሆኑ ተመራጭ ያደርገዋል።

ዋጋውን ዋጋውን እና ሙሉ መረጃውን ከታች ባስቀመጥነው ሊንክ ገብተው ይመልከቱ

https://t.me/joinchat/Um_xfu9NW05k6L77
https://t.me/joinchat/Um_xfu9NW05k6L77

አድራሻ፦ ልደታ ፌዛክ የገበያ ማእከል 1ኛ ፎቅ ላይ
ስልክ:- 0913979989 0900664655

 Inbox @Tebe_mart09    
11.4K views09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 21:59:40
ከቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ መገኘት ከነበረበት 42 MW ኃይል አሁን የሚገኘው ከ10 MW ያልበለጠ ነው ተባለ።

የቆቃ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ከሐይቁ ደለል የማስወገድ ሥራ፤ ላለፉት 20 ዓመታት ያህል የተቋረጠ በመሆኑ፣ ሐይቁ ለከፍተኛ የደለል ክምችት ተጋልጧል ተብሏል። የሐይቁ ጥልቀትም ከ10 ሜትር ወደ አንድ ሜትር አካባቢ የቀነሰ ሲሆን የሚያመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል በእጅጉ መቀነሱ ነው የተነገረው።

ይህ የተገለጸው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውኃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰሞኑን በቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የመስክ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ነው፡፡

በሐይቁ የውኃ ይዘት መቀነስ ምክኒያት፤ ከሦስቱ ተርባይኖች አንዱ ሥራ እንዳቆመ ያረጋገጠው ቋሚ ኮሚቴው፤ ባለፉት ዘመናት 42 ሜጋ ዋት ያመነጭ የነበረው ይህ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ፤ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ከ10 ሜጋ ዋት ያልበለጠ ኃይል እንደሚያመነጭም ተገንዝቧል፡፡

የቆቃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የኦፕሬሽን ኃላፊ አቶ ወልደማርያም ጥላዬ፤ ከሞጆ ቆዳ ፋብሪካዎች የሚወጣው ኬሚካል ፍሳሽ ሐይቁን እንደበከለ፤ የበፈር ዞን ሕግ ባለመኖሩ ሐይቁ ከሰው እና እንሰሳ ንክኪ ነጻ አለመሆኑ እና በደለል መሞላቱ፤ ተጠቃሽ ችግሮች መሆናቸውን ለኮሚቴው አስረድተዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ቡድን አስተባባሪ አቶ መስፍን ዳኜ፤ ኃይል ማመንጫ ጣቢያው የሚጠበቀውን ያህል ኃይል እያመነጨ ባለመሆኑ፣ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴርን ጨምሮ የክልሉ መንግስት እና በተለያዩ ርከኖች የሚገኙት አመራሮች የተቀናጀ እና የጋራ አቋም ሊኖራቸው እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡ (HPR)

@tikvahethmagazine
10.7K viewsedited  18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 21:28:02
#Update

ዛሬ በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺህ 154 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ከእነዚህ ውስጥ 157 ሴቶች ሁለት ህጻናትና 995 ወንዶች መሆናቸው ታውቋል፡፡ እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 22,600 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

በተያያዘ ዜና ዛሬ ከየመን በተደረገ የአንድ ጊዜ በረራ 150 ዜጎችን ወደ አገራቸው ተመልሰዋል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከኢሚግሬሽን ተወክለው የሄዱ ልዑካን ስራውን በኤደን የመን እየሰሩ እንደሚገኙ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine
13.6K viewsedited  18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 21:17:33
#Jimma

በጅማ ዞን ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው በዘመናዊ ግብርና ሥራ ተሰማርተዋል። ለወጣቶቹ በ 111 ሚሊየን ብር የተገዙ 42 ትራክተሮች በረጅም ጊዜ በሚከፈል ብድር ተሰጥቷቸዋል ሲሉ የጅማ ዞን የሙያና የስራ እድል ፈጠራ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ካሳሁን አስታውቀዋል።

ባለፉት 9 ወራት በዞኑ በግብርና እና በሌሎች የሥራ መስኮች 98 ሺህ 500 ሥራ አጦችን ከ8 ሺህ በላይ በሆኑ ማህበራት በማደራጀት እና የ190 ሚሊየን ብር ብድርና የስራ ቦታ በማመቻቸት የስራ እድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡ (FBC)

@tikvahethmagazine
14.6K viewsedited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 16:03:55
''... በዓለም ውስጥ በየትኛውም ቦታ ለዚህ የተዘጋጀ የለም'' ዶ/ር ጉሌይድ አርታን

በኢጋድ ሊቀመንበር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው ጋባዥነት ዛሬ በናይሮቢ በቀጠናው ስላለው የድርቅ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ጉባኤ ተካሂዷል።

ሊቀመንበሩ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ኢጋድ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ በነበሩት 3 ሳምንታት ውስጥ ሰብዓዊ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

''በአባል ሀገራቱ ያሉ ባለሙያዎች ወቅታዊ ግምት እንደሚያሳየው በኢጋድ አካባቢ ወደ 40.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት እየተጋለጡ ነው።'' ሲሉ ገልጸዋል።

ይህም የመጋቢት መጨረሻ ላይ ከተመዘገበው 29 ሚሊዮን የ30 በመቶ እድገት ማሳየቱንም ነው የጠቆሙት።

እንደ ኢጋድ ትንበያ 8.1 ሚሊዮን ሰዎች በኢትዮጵያ፣ 3.5 ሚሊዮን በኬንያ፣ 7.7 ሚሊዮን በሶማሊያ፣ 8.9 ሚሊዮን በደቡብ ሱዳን፣ 10.6 ሚሊዮን በሱዳን፣ እና በኡጋንዳ 1.6 ሚሊዮን ሰዎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ይጠቁሟል።

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው በቀጠናው ያለውን የድርቅ ሁኔታ ለመቅረፍ አጠቃላይ 6.3 ቢሊዮን ዶላር ልዩ ጥሪ በአስቸኳይ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። ቀጣዮቹ 6 ወራት ህይወት ለመታደግ ወሳኝ ናቸውም ነው የተባለው።

የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ ማዕከል ዳ/ተር የሆኑት ዶ/ር ጉሌይድ አርታን እንዳብራሩት ለአርብቶ አደር ማህበረሰቦች፣ ከድርቅ በኋላ ማገገም ሁልጊዜ የሁሉም ሁኔታዎች በጣም ፈታኝ እንደሆነ ይናገራሉ።

''ከአንድ ዙር ድርቅ ወደ በኋላ እንስሳቶችን እደዚህ ቀደሙ ለመመለስ በአማካይ 5 ዓመታት ይወስዳል። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ከአራት ተከታታይ የውድቀት ወቅቶች በኋላ የሚገኙበትን ሁኔታ አስቡት? በዓለም ውስጥ በየትኛውም ቦታ ለዚህ የተዘጋጀ የለም'' ብለዋል።

@tikvahethmagazine
5.7K viewsedited  13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 16:01:20
በመዲናዋ የፓርኪንግ ብቃት ማረጋገጫ ከወሰዱ 214 ህንጻዎች 86ቱ ብቻ ለታለመለት ዓላማ ማዋላቸው ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙና የህንፃ ስር ተሽከርካሪ ማቆሚያ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ስፍራውን ለታለመለት አላማ ማዋለቸውን ለመለየት የፓርኪንግ ብቃት ማረጋገጫ በወሰዱ በ214 ህንጻዎች ላይ ፍተሻ ማድረጉን ከተማው የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።

በኤጀንሲው የፓርኪንግ ልማት እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተካሄደው ፍተሻ ከ214 ህንፃዎች ውስጥ 86 (40.2%) የህንፃ ስር ፓርኪንግ አገልግሎት ስፍራውን ለታለመለት አላማ ማዋላቸው፣ 74 (34.6) ህንፃዎች ከታለመለት ዓለማ ውጭ በከፊል ለሌሎች አገልግሎቶች ማዋላቸው የተረጋገጠ ሲሆን ቀሪዎቹ 54ቱ (25.2%) ህንፃዎች ለምን አላማ እንዳዋሉ ማወቅ አልተቻለም ተብሏል።

የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታውን በከፊል ለሌላ አገልግሎት የቀየሩት ለውኃ ታንከርና ጀነሬተር ማስቀመጫ፣ ለእቃ ማከማቻ፣ ለቢሮ አገልግሎት፣ ለንግድ ስራ፣ ለቆሻሻ ማጠራቀሚያ እና ተረፈ ምርት ማከማቻ እና ለሌሎች ያልታወቁ አገልግሎት የዋሉ መሆናቸው በምልከታው ተረጋግጧል።

በ11ዱም ክፍለ ከተማዎች የህንፃ ስር ፓርኪንግ ብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷቸው ፍተሻ ተደርጎባቸው ለሌላ አገልግሎት ያዋሉ ተቋማት ላይ ተገቢውን እርምጃ ለመውሰድ ኤጀንሲው ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ የሚገኝ መሆኑን አስታውቋል።

በተጨማሪም በከተማዋ የሚገኙ ህንፃዎች የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታዎች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት አግኝተው ወደ ህጋዊ ስርዓት ለማስገባት ከአምስቱ ቅርንጨጫፍ ጽ/ቤቶች ጋር እየተሰራ እንደሚገኝም ገልጿል።

@tikvahethmagazine
5.3K views13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ