Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Freeseminar
Cloudbridge
Traininginstitute
Cryptocurrency
Аирдроп
Tikvahtechteam
Techdailly
Attention
Cbdc
Cryptocurrencies
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.37K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 257

2022-05-25 18:29:06
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+Zhm6yWqPh7U0N2E0
17.4K views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 11:14:27
የ8ኛ ክፍል ተማሪ ባከናወነው የፈጠራ ስራ የቀበሌውን ነዋሪዎች የመብራት ሀይል ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ዋጫሌ ወረዳ ዌቢቲ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተማሪ አደን ሁሴን የቱሉ ወቢ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን የከብቶች አዛባ እና የተለያዩ እንሰሶች አይነ ምድርን በማደባለቅ ባዮጋዝ በማዘጋጀት እንዲሁም ሽቦ እና ፕላስቲክን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ሀይል ማንጨት ችሏል፡፡

በዚህም ከራሱ አልፎ ለ16 የቀበሌው አባወራዎች መስመር በመዘርጋት የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ አድርጓቸዋል፡፡ በአካባቢው የሚከናወነውን የባዮ ጋዝ አሰራር መነሻ በማድረግ እና የራሱን የፈጠራ ችሎታ በማከል ውጤታማ ሥራ ማከናወን መቻሉን ተማሪ አደን ገልጿል፡፡

ተማሪው ካናወነው የፈጠራ ስራ በወር 1600 ብር ገቢ እያገኘ እንደሆነም ተናግሯል፡፡ (OBN)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
26.9K viewsedited  08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 10:55:08
የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ሰጪዎች የባንክ አዋጁ ከመሻሻሉ በፊትም ቢሆን በኢትዮጵያ ፈቃድ ያገኛሉ ተባለ።

የዲጂታል ክፍያ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በመዘጋጀት ላይ ሲሆን አዋጁ ሲጠናቀቅ የውጭ ባለሀብቶች የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላቸዋል።

የውጭ የሞባይል ገንዘብ ኦፕሬተሮች ወይም የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ሰጪዎች የባንክ አዋጁ ማሻሻያ ከመደረጉ በፊትም ቢሆን በኢትዮጵያ እንዲሰሩ ይፈቀድላቸዋል ተብሏል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ /ዶር / የባንክ አዋጁን ማሻሻል እና የሞባይል ገንዘብ ኦፕሬተሮችን መፍቀድ የተለያዩ መሆናቸውን ገለፀው የውጭ የሞባይል ገንዘብ ኦፕሬተሮች ሀገር ውስጥ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ህግ ለብቻ አንደሚሠራ ጠቁመዋል።

አሁን በሥራ ላይ ባለው የባንክ አዋጅ መሠረት የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ተቋማት ማለትም ክፍያ፣ ሬሚታንስ እና ኢንሹራንስን በዲጂታል አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን የውጭ ባለሀብቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መያዝ አይችሉም።

ባለፈው አመት የቴሌኮም ጨረታ አሸንፎ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኬንያ በሰፊው አገልግሎት የሚሰጠውን ኤም-ፔሳን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ዝግጅት ላይ መሆኑን ሲገልፅ ቆይቷል። አየተዘጋጀ ያለው ህግ ሲፀድቅ ኤም-ፔሳን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ሀገር የፊንቴክ ኩባንያዎች እንዲሰሩ ይፈቀድላቸዋል ብለዋል ገዢው።

በተጨማሪም መንግስት የባንክ ኢንዱስትሪውን ለውጭ ውድድር ለመክፈት ዝግጅት ላይ መሆኑ ሚታወስ ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የፋይናንሻል ህጉን ለማሻሻል ኮሚቴ አዋቅሮ እየሠራ እንደሚገኝ ገዢው ገልጸዋል።

Credit : Capital

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.2K viewsedited  07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 10:25:36
የበድር ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው።

“እስላማዊ እሴቶች ለሀገር ሰላም እና እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው የበድር ጉባኤ ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው።

ከ22 አመታት በፊት አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመው ዓለም ዐቀፍ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ማኅበር 22ኛውን ጉባኤ በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

በድር ወደ ማንነት (BADR back to the root) በሚል የተዘጋጀው መርኃ - ግብር በአውሮፓ እና አሜሪካ የተወለዱ ኢትዮጵያዊያን ስለ ሀገራቸው የሚረዱበት እና ኢትዮጵያን የሚያውቁበት መሆኑ ተጠቅሷል።

5 ሺሕ የሚደርሱ አባላትን ያቀፈው በድር ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዳለውም ተጠቅሷል።

በዚህም ማዕድ የማጋራት እና በልማት ማኅበራት ውስጥ የሚሳተፍ ሲሆን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጎ ፈንድ ሚ በመክፈት ከዲያስፖራው ማኅበረሰብ 1 ሚሊዮን 50 ሺሕ ዶላር ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል።

22ኛው ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄዱ በኮሮና ወረርሽኝ እየተቀዛቀዘ የመጣውን የኮንፍረንስ ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ የውጭ ምንዛሬን ያስገኛልም ተብሎ ይጠበቃል።

በመርኃ-ግብሩ ላይ ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡ እና ማንነትን የማሳወቂያ መድረክ እንደሚዘጋጅ የተጠቀሰ ሲሆን የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችም ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡

እስካሁን ከ1 ሺሕ 500 በላይ የሚሆኑ ታዳሚያን የተመዘገቡበት የበድር ጉባኤ ከሐምሌ 8 እስከ 18 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድም ተገልጿል። (Walta TV)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
20.4K viewsedited  07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 10:21:52
#ጤናረቡዕ #ዕሮብንለአንጀትጤና

ጤናማ አንጀት በነርቭ እና ሆርሞኖች አማካኝነት ከአንጎል፣ ኩላሊት፣ እና ከሌሎች የሰውነት አካላት ጋር ይገናኛል። ይህም አጠቃላይ የሰውነት ጤናን ለመጠበቅ ይረዳል።

ለመሆኑ....

የአንጀት ጤና ምንድን ነው?

የአንጀት ህመም ምልክቶች ምንድን ናቸው?

ሙሉ ጹሑፉን ለማንበብ https://bit.ly/አንጀትጤና

፨፨፨፨፨፨፨፨

በጉዳዩ ላይ ለሚኖሮት ጥያቄ፣ ምክርና አስተያየት በስልክ +251965662501 ይደውሉልን።

በቴሌግራም @IBDETHIOPIA ላይ ይጻፉልን።

[ ይህ ክሮንስ እና ኮላይተስ ኢትዮጵያ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የሚያቀርብላችሁ ጤና ረቡዕ የተሰኘው መረጃ ዋናው አላማ ስለስር የሰደዱ ህመሞች መረጃን መስጠት እንዲሁም ስለአንጀት ጤና አጠባበቅ በጽሁፍ፣ በቃለመጠይቅ፣ በተንቀሳቃሽ ምስሎች እና በ ሌሎች አዝናኝ እና አስተማሪ መንገዶች ጠቃሚ የሆኑ ትምህርቶችን ወደናንተ ማድረስ ነው።

በዝግጅቶቻችን ስር የሰደደ ህመም እርሶ ወይም ቤተሰብዎ ውስጥ ካለ እንደታካሚ ምን ማወቅ እንዳለቦት አልያም በሙሉ ጤና ላይ ካሉ ምን አይነት የአኗኗር ዘይቤ መከተል እንዳለቦት ለማወቅ ይችላሉ። ]

@tikvahethmagazine @ibdeth
18.4K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 10:21:31
ኢትኤል ዲዛይን ❖ Ethel Design

ለመኖርያ ቤት ለቢሮ ለንግድ ቦታዎ ውብ እና ማራኪ የሆኑ ዲዛይኖችን በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ካለው የፊኒሺንግ ስራ ጋር ሰርተን እናስረክቦታለን። ይደውሉልን።

የምንሰጣቸው አገልግሎት
የዲዛይን እና የፊኒሺንግ ስራ
የእንጨት ፓርቲሽኖችን መስራት
አጠቃላይ የእንጨት ስራ
ብራንዲንግ

Contact us @etheldesign1
0939902740
0919361804

Telegram: t.me/etheldesign
17.8K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 10:21:13
Register at https://www.effsaa.org/short-term-training-program-registration-form/ after the settlement of the training fee.
Venue
At the training hall of Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA) which is located at Kazanchis, Nigist Towers Hotel & Apartments 4th Floor (In front of Elilly International Hotel)
For More Information,
Call us at +251 115 589045 / +251 903 182525
OR
Visit our telegram channel
https://t.me/EFFSAAOfficial
20.8K viewsedited  07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:28:02 #የዛሬ (ግንቦት 16/2014)

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለማችንን ትልቁን የጤና ተቋም የዓለም የጤና ድርጅትን ለሁለተኛ ዙር እንዲመሩ ዳግም ተመረጡ። የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ብቸኛ ዕጩ ሆነው ዳግም መመረጣቸው የተረጋገጠው በጄኔቫ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉብዔ ላይ ነው።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር የሆነት ኮነሌል ገመቹ አያና ከስር እንዲለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሰነ።

በ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ማጠቃለያ ላይ ተማሪዎች ማጠቃለያ ፈተናዎችን ለመውስድ እየተዘጋጁ ይገኛሉ። ነገር ግን ማህበራዊ ኃላፊነት በጎደላቸው አካላት ሆን ተብሎ ተማሪዎችን ለማዘናጋት በዘንድሮ ዓመት ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለም ተብሎ በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች የሚናፈሰው ወሬ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

"ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመኪና ስርቆት እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዳይለየው " - የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት

የኳታሩ ዓለም ዋንጫ ሊጀምር የወራቶች እድሜ ብቻ ሲቀሩት የዓለም ዋንጫው በዛሬው ዕለት አስቀድሞ በተያዘለት ቀን #ኢትዮጵያ ደርሷል። የአለም ዋንጫው በሀገራችን የሁለት ቀናት ቆይታ ሲኖረው በነገው ዕለት ከ ረፋዱ 4:30 ጀምሮ በመስቀል አደባባይ በመገኘት የስፖርት አፍቃሪው አብሮ ፎቶ መንሳት እንደሚችል ተገልጿል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
10.3K viewsedited  19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 19:11:44
የኦሮሞ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲቲዩት 54 መፅሀፍቶችን ማሳተሙን አስታወቀ፡፡

የኦሮሞ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲቲዩት ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ባካሔደው የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ጥናት 54 የተለያዩ ይዘት ያላቸው መፅሀፍቶችን ማሳተሙን አስታውቋል፡፡

የኢንስቲቲዩቱ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ጥናት እና ምርምር ቡድን በስነ-ቃል እና ስነ ፅሁፍ እንዲሁም በመዝገበ ቃላት በመሳሰሉት ዘርፎች ላይ በማተኮር ያዘጋጁትን መፅሀፍቶች በሽያጭ እና በልገሳ ለህብረተሰቡ ማድረስ መቻሉን የኦሮሞ ጥናት እና ምርምር ኢንስቲቲዩት ዳሬክተር አቶ ድሪባ ተረፈ ተናግረዋል፡፡ (OBN)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
21.5K viewsedited  16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 18:55:00
#EPSA

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እስትራቴጂካዊ የሆኑና በመድኃኒት አቅርቦት ላይ ያሉ ተግዳሮቶች የዳሰሰበት ውይይት ከአጋር አካላት (partners) ጋር ማድረጉን ገልጿል።

በውይይቱ የሚከተሉት አበይት ተግባራት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው በሚቀጥሉት ሁለት ወራት እንዲተገበሩ ሥምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

1) የተቀናጀ አገራዊ የመድኃኒት አቅርቦት ዳሰሳን ማድረግ፤

2) የአመታዊ የመድኃኒት እና የህክምና መገልገያዎች ቆጠራን በተመለከተ ዝግጅት ማድረግና ቆጠራውን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ፤

3) የተጀመሩና ያልተጠናቀቁ መመሪያዎችን በሚቀጥለው የስራ ዘመን መጀመሪያ ስራ እንዲጀምሩ ማድረግ፤

4) የስራ መገምገሚያና መከታተያ አመልካች (ጠቋሚ) መረጃ አመልካቾች (monitoring indicators) የከለሣ ስራው ተጠናቆ በአዲስ መልክ እንዲዘጋጁ ተወስኗል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
19.3K viewsedited  15:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ