Get Mystery Box with random crypto!

የ8ኛ ክፍል ተማሪ ባከናወነው የፈጠራ ስራ የቀበሌውን ነዋሪዎች የመብራት ሀይል ተጠቃሚ ማድረግ ችሏ | TIKVAH-MAGAZINE

የ8ኛ ክፍል ተማሪ ባከናወነው የፈጠራ ስራ የቀበሌውን ነዋሪዎች የመብራት ሀይል ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ዋጫሌ ወረዳ ዌቢቲ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ተማሪ አደን ሁሴን የቱሉ ወቢ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን የከብቶች አዛባ እና የተለያዩ እንሰሶች አይነ ምድርን በማደባለቅ ባዮጋዝ በማዘጋጀት እንዲሁም ሽቦ እና ፕላስቲክን በመጠቀም የኤሌክትሪክ ሀይል ማንጨት ችሏል፡፡

በዚህም ከራሱ አልፎ ለ16 የቀበሌው አባወራዎች መስመር በመዘርጋት የኤሌክትሪክ ሀይል ተጠቃሚ አድርጓቸዋል፡፡ በአካባቢው የሚከናወነውን የባዮ ጋዝ አሰራር መነሻ በማድረግ እና የራሱን የፈጠራ ችሎታ በማከል ውጤታማ ሥራ ማከናወን መቻሉን ተማሪ አደን ገልጿል፡፡

ተማሪው ካናወነው የፈጠራ ስራ በወር 1600 ብር ገቢ እያገኘ እንደሆነም ተናግሯል፡፡ (OBN)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot