Get Mystery Box with random crypto!

የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ሰጪዎች የባንክ አዋጁ ከመሻሻሉ በፊትም ቢሆን በኢትዮጵያ ፈቃድ ያ | TIKVAH-MAGAZINE

የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ሰጪዎች የባንክ አዋጁ ከመሻሻሉ በፊትም ቢሆን በኢትዮጵያ ፈቃድ ያገኛሉ ተባለ።

የዲጂታል ክፍያ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ በመዘጋጀት ላይ ሲሆን አዋጁ ሲጠናቀቅ የውጭ ባለሀብቶች የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላቸዋል።

የውጭ የሞባይል ገንዘብ ኦፕሬተሮች ወይም የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ሰጪዎች የባንክ አዋጁ ማሻሻያ ከመደረጉ በፊትም ቢሆን በኢትዮጵያ እንዲሰሩ ይፈቀድላቸዋል ተብሏል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ /ዶር / የባንክ አዋጁን ማሻሻል እና የሞባይል ገንዘብ ኦፕሬተሮችን መፍቀድ የተለያዩ መሆናቸውን ገለፀው የውጭ የሞባይል ገንዘብ ኦፕሬተሮች ሀገር ውስጥ እንዲሠሩ የሚፈቅደው ህግ ለብቻ አንደሚሠራ ጠቁመዋል።

አሁን በሥራ ላይ ባለው የባንክ አዋጅ መሠረት የዲጂታል ፋይናንሺያል አገልግሎት ተቋማት ማለትም ክፍያ፣ ሬሚታንስ እና ኢንሹራንስን በዲጂታል አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን የውጭ ባለሀብቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መያዝ አይችሉም።

ባለፈው አመት የቴሌኮም ጨረታ አሸንፎ የገባው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኬንያ በሰፊው አገልግሎት የሚሰጠውን ኤም-ፔሳን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ዝግጅት ላይ መሆኑን ሲገልፅ ቆይቷል። አየተዘጋጀ ያለው ህግ ሲፀድቅ ኤም-ፔሳን ጨምሮ ሌሎች የውጭ ሀገር የፊንቴክ ኩባንያዎች እንዲሰሩ ይፈቀድላቸዋል ብለዋል ገዢው።

በተጨማሪም መንግስት የባንክ ኢንዱስትሪውን ለውጭ ውድድር ለመክፈት ዝግጅት ላይ መሆኑ ሚታወስ ነው። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የፋይናንሻል ህጉን ለማሻሻል ኮሚቴ አዋቅሮ እየሠራ እንደሚገኝ ገዢው ገልጸዋል።

Credit : Capital

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot