Get Mystery Box with random crypto!

የበድር ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው። “እስላማዊ እሴቶች ለሀገር ሰላም እና እድ | TIKVAH-MAGAZINE

የበድር ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው።

“እስላማዊ እሴቶች ለሀገር ሰላም እና እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው የበድር ጉባኤ ለመጀመሪያ ግዜ በኢትዮጵያ ሊካሄድ ነው።

ከ22 አመታት በፊት አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመው ዓለም ዐቀፍ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ማኅበር 22ኛውን ጉባኤ በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

በድር ወደ ማንነት (BADR back to the root) በሚል የተዘጋጀው መርኃ - ግብር በአውሮፓ እና አሜሪካ የተወለዱ ኢትዮጵያዊያን ስለ ሀገራቸው የሚረዱበት እና ኢትዮጵያን የሚያውቁበት መሆኑ ተጠቅሷል።

5 ሺሕ የሚደርሱ አባላትን ያቀፈው በድር ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዳለውም ተጠቅሷል።

በዚህም ማዕድ የማጋራት እና በልማት ማኅበራት ውስጥ የሚሳተፍ ሲሆን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጎ ፈንድ ሚ በመክፈት ከዲያስፖራው ማኅበረሰብ 1 ሚሊዮን 50 ሺሕ ዶላር ድጋፍ ማድረጉም ተገልጿል።

22ኛው ጉባዔ በአዲስ አበባ መካሄዱ በኮሮና ወረርሽኝ እየተቀዛቀዘ የመጣውን የኮንፍረንስ ቱሪዝም ከማነቃቃት ባለፈ የውጭ ምንዛሬን ያስገኛልም ተብሎ ይጠበቃል።

በመርኃ-ግብሩ ላይ ጥናታዊ ፅሁፎች እንደሚቀርቡ እና ማንነትን የማሳወቂያ መድረክ እንደሚዘጋጅ የተጠቀሰ ሲሆን የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችም ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡

እስካሁን ከ1 ሺሕ 500 በላይ የሚሆኑ ታዳሚያን የተመዘገቡበት የበድር ጉባኤ ከሐምሌ 8 እስከ 18 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድም ተገልጿል። (Walta TV)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot