Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመደ የቲቢ ሕክምናን ወደ 9 ወር ዝቅ የሚያደርግ የምርምር ውጤት ተገኘ። | TIKVAH-MAGAZINE

በኢትዮጵያ መድሃኒት የተላመደ የቲቢ ሕክምናን ወደ 9 ወር ዝቅ የሚያደርግ የምርምር ውጤት ተገኘ።

የአርማወር ሀንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት መድሃኒት የተላመደ የቲቢ ሕክምናን ከ2 ዓመት ወደ 9 ወር ዝቅ የሚያደርግ የምርምር ውጤት ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የምርምር ውጤቱ በዓለም ጤና ድርጅት ዕውቅና ተሰጥቶት ስራ ላይ የዋለ መሆኑ ሲገለፅ፤ ላንሴት በተባለ ዓለም አቀፍ ጆርናል ላይ መውጣቱን ኢዜአ በዘገባው አመልክቷል።

ኢንስቲትዩቱ በወባ፣ ስጋ ደዌ፣ ቲቢ፣ ማጅራት ገትር፣ ኮሌራ፣ የአንጀት ተስቦ እንዲሁም በባክቴሪያ የሚመጡ በሽታዎች ላይ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ሲገለፅ በአሁኑ ወቅት 395 ተመራማሪዎች እንደሉትም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine