Get Mystery Box with random crypto!

#EPSA የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እስትራቴጂካዊ የሆኑና በመድኃኒት አቅርቦት ላይ | TIKVAH-MAGAZINE

#EPSA

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት እስትራቴጂካዊ የሆኑና በመድኃኒት አቅርቦት ላይ ያሉ ተግዳሮቶች የዳሰሰበት ውይይት ከአጋር አካላት (partners) ጋር ማድረጉን ገልጿል።

በውይይቱ የሚከተሉት አበይት ተግባራት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው በሚቀጥሉት ሁለት ወራት እንዲተገበሩ ሥምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

1) የተቀናጀ አገራዊ የመድኃኒት አቅርቦት ዳሰሳን ማድረግ፤

2) የአመታዊ የመድኃኒት እና የህክምና መገልገያዎች ቆጠራን በተመለከተ ዝግጅት ማድረግና ቆጠራውን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ፤

3) የተጀመሩና ያልተጠናቀቁ መመሪያዎችን በሚቀጥለው የስራ ዘመን መጀመሪያ ስራ እንዲጀምሩ ማድረግ፤

4) የስራ መገምገሚያና መከታተያ አመልካች (ጠቋሚ) መረጃ አመልካቾች (monitoring indicators) የከለሣ ስራው ተጠናቆ በአዲስ መልክ እንዲዘጋጁ ተወስኗል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot