Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Cloudbridge
Traininginstitute
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.20K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2024-04-17 10:20:12
በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ባለ የቁጠባ ዘመቻ በርካታ ጥሬ ገንዘብ እየተሰበሰበ ነው።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች ቁጠባን ለማበረታታት በተደረጉ ዘመቻዎች ነዋሪዎች በርካታ ጥሬ ገንዘብ በስንቄ ባንክ በኩል በቁጠባ መልክ ማስቀመጥ መቻላቸው ተገልጿል።

ለአብነትም በጅማ ዞን ሊሙ ወረዳ በነበረ የአንድ ቀን ዘመቻ ብቻ 252 ሚሊዮን ብር በስንቄ ባንክ በኩል ገቢ መሆን ችሏል። የወረዳው አስተዳዳሪ አንደገለጹት በዚህ ዓመት 2.4 ቢሊዮን ብር በቁጠባ መልክ ወደ ባንኩ እንዲገባ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተመሳሳይ በአጋሮ ከተማ በአንድ ቀን በተደረገ የቁጠባ ዘመቻ 21.8 ሚሊየን ብር በስንቄ ባንክ በቁጠባ ሂሳብ ገቢ ሆኗል ተብሏል።

@TikvahethMagazine
28.5K viewsedited  07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 10:19:34
#Update: በጄኔቫ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማሰባሰብ በተደረገው ስነ ስርዓት ሀገራት ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሚሰጡ አስታወቁ

በኢትዮጵያ ለተከሰተው የሰብዓዊ ቀውስ አስቸኳይ 1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማሰባሰብ በስዊትዘርላንድ ጄኔቫ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ሀገራት 630 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለኢትዮጵያ እንደሚሰጡ አስታወቁ።

በዚህም አሜሪካ 253 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰት ቃል ስትገባ ዩናይትድ ኪንግደም 125 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት በድምሩ ከ139 ሚሊየን ዶላር በላይ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

የመንግስታቱ ድርጅት በሚቀጥሉት 3 ወራት ብቻ ለኢትዮጵያ እርዳታ ለማቅረብ 1 ቢሊዮን ዶላር  እንዲሁም በሀገሪቱ በ2024 እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ 3.24 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል ማለቱ ይታወሳል።

@TikvahethMagazine
24.1K viewsedited  07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 10:19:01
MESTURAH STORE

ማንኛውንም አይነት እቃ ከ SHEIN እና ከ ALI EXPRESS ትእዛዝ መቀበል ጀምረናል ከታች ባሉት Website የፈለጋቹትን መርጣቹ በቴሌግራም ሊንካችን ይላኩልን

የቴሌግራም ሊንካችን https://t.me/mesturahstore

የቲክቶክ ገፃችን https://www.tiktok.com/@mesturahstore?_t=8lYRHxeLhfp&_r=1

በተጨማሪም 0911267699

የ SHEIN website: https://www.shein.com/

የ ALI EXPRESS website: https://www.aliexpress.com/
21.7K views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-17 10:18:46
#cloudbridge. #traininginstitute

ክላውድ በሪጂ ማሰልጠኛ ተቋም ፤ለስልጠና ፍላጊዎች በሙሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽ እውቀት አቅም ግንባታ ነፃ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ እናንተን በጉጉት  ይጠብቃል::

ስልጠና ሚሰጥባችው ዘረፎች መካከል፡
1, Digital marketing
2,Web development
3, Interior design
4, Graphic design

የስልጠና ቦታ
ሲቲ ሞል 6ኛ ፎቅ, መገናኛ ድልድይ,wow burger ያለበት፣Megenagna siti Mall 6th, Addis Ababa, Ethiopia

ለተጨማሪ መረጃ
094-228-0000
092-083-8483
ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸው ፈጥነው በአካል መተው ይመዝገቡ።
         ለአንድ ቀን ሚቆይ ነፃ ስልጠና!
Register online
https://cloudbridgeacademy.com/registration
24.8K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-16 20:13:21
#Update: በኢትዮጵያ ለተከሰተው የሰብዓዊ ቀውስ አስቸኳይ 1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ የማሰባሰብ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ

በስዊትዘርላንድ ጄኔቫ ዛሬ ሚያዚያ 8/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ለተከሰተው የሰብዓዊ ቀውስ የ1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ  የማሰባሰብ ሥነ ሥርዓት ተካሄደ። በስርዓትቱም ዩናይትድ ኪንግደም 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ እንደምታደርግ አስታውቃለች።

የገንዘብ ድጋፉን ሥነ ሥርዓት ያዘጋጁት የኢትዮጵያ፣ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተባባሪ አካላት ለቀረበው የገንዘብ ድጋፍ ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ የሚጠብቁ መሆኑን ገልፀዋል።

በሀገቱ በድርቅ፣ ጎርፍ እና ግጭት ሚሊዮኖችን ከቀያቸው ያፈናቀለ ሲሆን፣ በመጪዎቹ ከሐምሌ 2016 እስከ መስከረም 2017 መካከል የምግብ እጥረት የሚገጥማቸው ሰዎች ቁጥር 10.8 ሚሊዮን እንደሚደርስ ተገምቷል።

@TikvahethMagazine
29.6K viewsedited  17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 20:08:00
በቤጂንግ የግማሽ ማራቶን ውድድር የተፈጠረው ምንድን ነው?

በቤጂንግ በተደረገው የግማሽ ማራቶን ውድድር ሦስት አፍሪካዊያን አትሌቶች አንድ ቻይናዊ አትሌት ተባብረው እንዲያሸንፍ አድርገዋል፤ የውድድር ህግ ጥሰዋል በሚል ምርመራ እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

በውድድሩ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊ አትሌት ደጀኔ ኃይሉ ጨምሮ ሁለት ኬኒያዊያን አትሌቶች ሂ ጃይ (He Jie) የተሰኘውን ቻይናዊ አትሌት በውድድሩ ማገባደጃ ላይ በእጃቸው እንዲፈጥን በመጠቆም እንዲሁም ፍጥነታቸውን በመቀነስ አትሌቱ አሸናፊ እንዲሆን አድርገዋል በሚል ነው ምርመራው የተከፈተው።

ይህ ቪዲዮ በቻይና በሚገኙ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከተለቀቀ በኋላ በርካቶች ድርጊቱን የተቃወሙት ሲሆን የዓለም አቀፍ ሚዲያዎችንም ትኩረት ስቧል።

ከኬኒያውያን አትሌቶች አንዱ ለቢቢሲ ስፖርት አፍሪካ እንደገለጸው ሦስታችንም በውድድሩ የተሳተፍነው ቻይናዊውን አትሌት ለማሯሯጥ (pacemaker) ነው ሲል ገልጿል

አትሌቱ እንደገለጸው ቻይናዊው አትሌት የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ውድድርን ሪከርድ የሆነውን 1:02:33 እንዲሰብር ለማገዝ ብንገባም ማሳካት አልተቻለም ብሏል። ቻይናዊው አትሌት ውድድሩን ማጠናቀቅ የቻለው በ1:03:44 ነው።

የቤጂንግ ስፖርት ቢሮ ቃል አቀባይ ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት ጉዳዩን እየመረመሩ መሆኑን ገልጸው “ውጤቱን እንደተገኘ ለህዝብ እናሳውቃለን” ብለዋል።

@TikvahethMagazine
23.5K viewsedited  17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 19:16:51
በቴሌብር ሱፐር አፕ መረጃ መለዋወጥ የሚያስችል ሥርዓት ተዋወቀ።

ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌብር ሱፐር አፕ መተግበሪያው ላይ የሚካተቱ ተጨማሪ አገልግሎቶችን በዛሬው ዕለት አስተዋውቋል።  በዛሬው ዕለት ካስተዋወቀው አገልግሎት አንዱ "ቴሌብር ኢንጌጅ" የተሰኘው አገልግሎት አንዱ ነው።

"ቴሌብር ኢንጌጅ" ሦስት መሰረታዊ ዓላማዎችን ለማሳካት የተጨመረ አገልግሎት መሆኑን የገለጹት የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፥ ገንዘብ ማስተላለፍ፤ ማኅበራዊ ትስስር መፍጠርና ማጋራትን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።

ይህ አዲስ አገልግሎት በግለሰብም ሆነ በቢዝነስ ደንበኞች መካከል የተናጠል ወይም የቡድን የቀጥታ ውይይቶችን (online chat) ለማድረግ የሚያስችል ሲሆን የድምጽ፤ የፎቶ፤ የቪዲዮ፤ የፋይል መልዕክቶችን መላላክ ያስችላል።

በተጨማሪም በውይይት ወቅት ገንዘብ ማስተላለፍ የአየር ሰዓት መግዛትና መላክን ያካትታል። ከዚህም በተጨማሪ የተገልጋይ አካውንት መክፈት(ማስተካከል)፤ የጓደኝነት ጥያቄ ማቅረብ መቀበል በአዲሱ አገልግሎት የተካተቱ ናቸው።

በግሩፕ ውስጥ ሥጦታ መላላክን የሚያበረታታው "ሻሞ" የተሰኘ አገልግሎትም የተካተተ ሲሆን ለሰዎች ቀጥታ መሸልም ወይም እድለኛ ለሆኑ ሰዎች ሽልማት ማቅረብ ያስችላል።

ቴሌብር ኢንጌጅ የማኅበራዊ ሚዲያ ይሆን?

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ አገልግሎቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት "አዲሱ አገልግሎት ከሶሻል ሚዲያ ያልተናነሰ ፊቸር ያለው ነገር ግን ስሻል ሚዲያን ለመተካት ሳይሆን የመጣው ዲጂታል ህይወትን ለማቅለል [ነው] " ሲሉ አስረድተዋል።

ዛሬ የተዋወቀው ሌላኛው አገልግሎት "የዴቨሎፐርስ ፖርታል" ምንድን ነው?

ኩባንያው "የዴቨሎፐርስ ፖርታል" የተሰኘ ሲስተሞችን ከቴሌብር ሱፐርአፕ ጋር ለማስተሳሰር (integrate) ያግዛል የተባለውን ሥርዓት አስተዋውቋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ እንደገለጹት አሁን ላይ ወደ 237 የንግድ ተቋማት እንዲሁም 108 የሚሆኑ የመንግስት አገልግሎቶች የክፍያ ሥርዓታቸውን ከቴሌብር ጋር ማስተሳሰራቸውን ጠቅሰው ይህ ግን በቂ አለመሆኑን አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም ሲስተሞችን ከቴሌብር ጋር ለማገናኘት ከ2 እስከ 3 ወራት ይፈጅ የነበረ ሲሆን አሁን ይፋ በተደረገው ሥርዓት ግን ተቋማት በሁለት እና በሦስት ቀናት ውስጥ ሥርዓታቸውን ከቴሌብር ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር ይችላሉ ተብሏል።

የቴሌብር ሱፐር አፕን ከኢንተርኔት ክፍያ ነጻ (offline) መጠቀም ይቻላል?

የቴሌብር ሱፐር አፕ ከዚህ ቀደም ደንበኞች ሲጠቀሙ የነበሩትን አገልግሎቶች ጨምሮ አዲስ የተዋወቀውን አገልግሎት ያለምንም የኢንተርኔት ክፍያ መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ይህም ኩባንያው ባለፉት ጊዜያት የራሱን የክላውድ መሰረተ ልማት በመዘርጋቱ "የራሳችንን ዳታ ራሳችን እንድንጠቀም አስችሎናል" ሲሉ ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል።

ይህም ሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶች ቢቋረጡ እንኳን አገልግሎት መስጠት ያስችለዋል ተብሏል።

የቴሌብር ቁጥራዊ መረጃዎች ምን ይላሉ?

- በሦስት ዓመት ውስጥ 44.5 ሚሊዮን ደንበኞችን ማፍራት ችሏል።

- በሦስት አመት ውስጥ 775 የገንዘብ ዝውውሮች የተደረጉ ሲሆን ከ2 ትሪሊየን ብር በላይ አንቀሳቅሷል።

- ዛሬ ላይ በቀን 5 ቢሊዮን ትራንዛክሽን ይፈጸምበታል።

@TikvahethMagazine
23.5K viewsedited  16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 19:15:57
ከ7 እስከ 18 ለሆኑ ልጆች የኦንላይን  ኮዲንግ  ስልጠና

ስልጠና April 20 , 2024 ቅዳሜ ይጀምራል።

ከ7 እስከ 13 ለሆኑ ህጻናት የ6 ሳምንታት የscratch ስልጠና( ጌም እና አኒሜሽን እየሰሩ ነው ሚማሩት)።

ከ14 እስከ 18 ለሆኑት የ website ስልጠና ለ 2 ወር።

የምስክር ወረቀት ያገኛሉ

ክፍያ ለ6 ሳምንት ፕሮግራም 2500 ብር ነው።
ክፍያ ለ 2 ወር ፕሮግራም 3500 ብር ነው።

በቴሌግራም መረጃ ለማግኘት ያግኙን
@koderlabtrainingcenter ወይም በ 0940121072 ይደውሉ።

ይህንን ሊንክ በመጠቀም ሬጅስተር ያርጉ።
https://forms.gle/J3CeN5XE4vQW3MF49
21.4K views16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 12:58:03
በሲዳማ ክልል በዚህ ዓመት 113 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል።

በሲዳማ ክልል በበጀት አመቱ 113 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያለፈ ሲሆን አደጋው በ2015 በጀት አመት ከደረሰው የትራፊክ አደጋ ጋር ሲነጻጸር 48 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል።

80 በመቶ የትራፊክ አደጋ የሚደርሰው በሞተር ሳይክሎች እንደሆነ የጠቀሱት የሲዳማ ክልል መንገድ ልማት እና ትራንስፖርት ቢሮ ኋላፊ አቶ ታምሩ ታፌ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ወደ ትላልቅ ከተሞች እንዳይገቡ እገዳ መጣሉን አስረድተዋል።

ይህ የተገለጸው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሐዋሳ ከተማ አስተዳደር መናኸሪያ የትራንስፖርት አገልገሎት አሰጣጡን በተመለከተ የመስክ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ነው።

@TikvahethMagazine
26.1K views09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-15 12:57:03
በአዲስ አበባ በ9 ወራት 286 ሰዎች በመንገድ ትራፊክ ግጭት ህይወታቸውን አልፏል ተባለ

በአዲስ አበባ በ9 ወራት ውስጥ 286 ሰዎች በመንገድ ትራፊክ ግጭት ህይወታቸውን ማጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድ ደኅንነት ምክር ቤት የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አመለከተ፡፡

በተጠቀሰው ጊዜ 716,624 የትራፊክ የደንብ ጥሰቶች መፈጸቸው ሲገለፅ ፣ ምንም እንኳን ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ 9 ሰው ሞት ቢቀንስም በተለይ የትራፊክ አደጋው አምራች የሆነውን ወጣቱን ሀይል እያሳጣ መሆኑ ተጠቁሟል።

@TikvahethMagazine
22.7K views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ