2022-05-27 23:50:08
#የዛሬ (ግንቦት 19/2014)
እናት የፓርቲ 4 አመራሮቹ የገቡበትን ማወቅ እንዳልቻለ ገልጿል። ፓርቲው በአማራ ክልል መንግስት እየወሰደ ያለውን የሰሞኑን እርምጃ "አፈና" ሲል ገልጾ በዚህ ሂደት አመራሮቹ እንደታፈኑበት ገልጿል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሩ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በባህር ዳር ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል። ፓርቲው አመራሩ በአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩን ነው ያመለከተው።
የ 'ፍትህ መጽሔት' ማኔጂግ ዳሪክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ " የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በህዝብ ዘንድ አመኔታ ለማሳጣትና ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ወንጀል " መጠርጠሩን መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ለፍ/ቤት ገልጿል። የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ በበኩሉ መከላከያን መተቸት እምነት ማሳጣት አለመሆኑን ጠቅሶ ተከራክሯል። ጉዳዩን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎች የፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንዲቀርብ በማዘዝ መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ለፊታችን ሰኞ ቀጥሯል።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ላይ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። ጋዜጠኛ ያየሰው የተጠረጠረው " ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል " መሆኑን መርማሪ ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።
''
እስካሁን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ስም ብዙ ነገሮች ተችለዋል በአሁን ሰዓት ግን የለየለት የሽብር ስራ ፣ የሽብር ፈጠራ ፣ ሀገርን የማፍረስ ስራ ፣ ህግ የሌለ እስከማስመሰል ፣ የፍትህ ተቋማት እርምጃ መውሰድ አይችሉም የሚያስብል ደረጃ ላይ ደርሶ ሀገርን የማፍረስ ተልዕኮ ላይ እየሰሩ ያሉት አካላት ላይ የህግ የበላይነት ለማስከበር ከምን ጊዜውም በላይ የፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች የፍትህ ተቋማት ጋር በመሆን የምርመራ ስራን እየሰራ ይገኛል።'' አቶ ሙሊሳ አብዲሳ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ "
የሚዲያ ባለሙያዎች መታሰራቸው ከመገናኛ ብዙሃን ህጉ ጋር የሚጻረርና መዘዙ ከመገናኛ ብዙሃን እና ሃሳብን ከመግለጽ የዘለለ በመሆኑ አሳሳቢ ነው" ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ከጥቂት ወራት በፊት ታስሮ ከእስር የተፈታው የቀድሞ የአውሎ ሚዲያ ባልደረባ አሁን ላይ " አልፋ ቲቪ " የተሰኘ የማህበራዊ ሚዲያ መስራች እና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መዋሉን ጠበቃ ታደለ ገብረመድህንን ዋቢ አድርጎ አዲስ ስታንዳር አስነብቧል። የጋዜጠኛውን መታሰር ባለቤቱ ሄለን አባተ አረጋግጠዋል።
የፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አህመድ ትላንት በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን (በለቡ ፖሊስ ጣቢያ ነበረች) ዛሬ ወደ ቢሾፍቱ መወሰዷን የጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ለሚ ታዬ ተናግረዋል።
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ወደ በሰኔ እና ሃምሌ ወር 2022 ወደ ሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ እንደሚጓዙ ታውቋል።
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረችው ፅጌሬዳ ግርማይን በመግደል የተከሰሰው ተማሪ በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤት ወሰነ። ፍርድ ቤቱ ዛሬ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን በወንጀል ህግ ቁጥር 5391-ሀ ጥፋተኛ አድርጎታል።
#ቲክቫህኢትዮጵያ
@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
4.6K viewsedited 20:50