Get Mystery Box with random crypto!

''... በዓለም ውስጥ በየትኛውም ቦታ ለዚህ የተዘጋጀ የለም'' ዶ/ር ጉሌይድ አርታን በኢጋድ ሊ | TIKVAH-MAGAZINE

''... በዓለም ውስጥ በየትኛውም ቦታ ለዚህ የተዘጋጀ የለም'' ዶ/ር ጉሌይድ አርታን

በኢጋድ ሊቀመንበር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው ጋባዥነት ዛሬ በናይሮቢ በቀጠናው ስላለው የድርቅ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ጉባኤ ተካሂዷል።

ሊቀመንበሩ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ኢጋድ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ በነበሩት 3 ሳምንታት ውስጥ ሰብዓዊ እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

''በአባል ሀገራቱ ያሉ ባለሙያዎች ወቅታዊ ግምት እንደሚያሳየው በኢጋድ አካባቢ ወደ 40.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ለከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት እየተጋለጡ ነው።'' ሲሉ ገልጸዋል።

ይህም የመጋቢት መጨረሻ ላይ ከተመዘገበው 29 ሚሊዮን የ30 በመቶ እድገት ማሳየቱንም ነው የጠቆሙት።

እንደ ኢጋድ ትንበያ 8.1 ሚሊዮን ሰዎች በኢትዮጵያ፣ 3.5 ሚሊዮን በኬንያ፣ 7.7 ሚሊዮን በሶማሊያ፣ 8.9 ሚሊዮን በደቡብ ሱዳን፣ 10.6 ሚሊዮን በሱዳን፣ እና በኡጋንዳ 1.6 ሚሊዮን ሰዎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን ይጠቁሟል።

ዶ/ር ወርቅነህ ገበየው በቀጠናው ያለውን የድርቅ ሁኔታ ለመቅረፍ አጠቃላይ 6.3 ቢሊዮን ዶላር ልዩ ጥሪ በአስቸኳይ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። ቀጣዮቹ 6 ወራት ህይወት ለመታደግ ወሳኝ ናቸውም ነው የተባለው።

የኢጋድ የአየር ንብረት ትንበያ ማዕከል ዳ/ተር የሆኑት ዶ/ር ጉሌይድ አርታን እንዳብራሩት ለአርብቶ አደር ማህበረሰቦች፣ ከድርቅ በኋላ ማገገም ሁልጊዜ የሁሉም ሁኔታዎች በጣም ፈታኝ እንደሆነ ይናገራሉ።

''ከአንድ ዙር ድርቅ ወደ በኋላ እንስሳቶችን እደዚህ ቀደሙ ለመመለስ በአማካይ 5 ዓመታት ይወስዳል። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ከአራት ተከታታይ የውድቀት ወቅቶች በኋላ የሚገኙበትን ሁኔታ አስቡት? በዓለም ውስጥ በየትኛውም ቦታ ለዚህ የተዘጋጀ የለም'' ብለዋል።

@tikvahethmagazine