Get Mystery Box with random crypto!

ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የአለም ዋንጫን እንዲመሩ ከተሾሙ ዳኞች ውስጥ አለመካትቱ ታውቋል። | TIKVAH-MAGAZINE

ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ የአለም ዋንጫን እንዲመሩ ከተሾሙ ዳኞች ውስጥ አለመካትቱ ታውቋል።

በኳታር አዘጋጅነት በ 2022 ለሚካሄደው የአለም ዋንጫ ፊፋ 36 ዋና ዳኞችን 69 ረዳት ዳኞችን እና 24 የቫር ዳኞችን ውድድሩን እንዲመሩ መሾሙን አስታውቋል።

ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ፊፋ የአለም ዋንጫን እንዲመሩ ከሾማቸው ዳኞች ስም መካከል #አለመካትቱ ታውቋል።

ፊፋ ለመጀመሪያ ጊዜ በኳታር አዘጋጅነት በሚካሄደው የአለም ዋንጫን ላይ ሶስት ዋና ሴት ዳኞችን እና ሶስት ረዳት ሴት ዳኞችን ውድድሩን እንዲመሩ መምረጡ ተገልጿል ።

የአለም ዋንጫን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲመሩ ከተመረጡ ሶስት ሴት ዳኞች መካከል አንዷ ሩዋንዷዊቷ ሳሊማ ሙካንሳንጋ መሆኗ ተዘግቧል።

አፍሪካን ወክለው የአለም ዋንጫን እንዲመሩ የተመረጡ ስድስት ዋና ዳኞች ሳሊማ ሙካንሳንጋ ፣ ጃኒ ሲካዝዌ ፣ ባካሪ ጋሳማ ፣ ቪክቶር ጎሜዝ ፣ ማጉዬቴ ኒዳዬ እና ሙስጣፋ ጎርባል መሆናቸው ተነግሯል።

Via @tikvahethsport

@tikvahethmagazine