Get Mystery Box with random crypto!

#DireDawa የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ቀናት ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የሆነ | TIKVAH-MAGAZINE

#DireDawa

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባለፉት ጥቂት ቀናት ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ የሆነ የሙቀት መጠን እንየተስተዋለ መሆኑን ጠቁሟል። ይህን አስመልክቶም የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ለነዋሪዎችም የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፏል።

በተለይም አረጋውያን እና የተለያዩ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው (ከፍተኛ ደም ግፊት፣የስኳር ህመም፣ የልብ ህመም፣ የኩላሊት ህመምና ሌሎችም)፣ እራሳቸውን መንከባከብ የማይችሉ የአይምሮ ህሙማን እና ህፃናት በተለየ መልኩ የጥንቃቄ መልእክቶች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ቢሮው አሳስቧል።

በዚህም፦

1. ወቅታዊው ከፍተኛ የሙቀት መጠን እስኪያልፍ መኖሪያ ቤትዎን በተለያዩ መንገዶች ማቀዝቀዝ፣

2. እቤትዎ በሚሆኑበት ግዜና በእንቅልፍ ወቅት የቤትዎን መስኮትና በር ክፍት ማድረግ፣

3. በቤትዎ የአየር መታፈን እና ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ወቅት ከቤትዎ ውጪ/በረንዳዎ ላይ መቆየት፣

4. ጥም ባይኖርቦትም በቂ ፈሳሽ/ውሃ/ መውሰድ፣

5. አመጋገብዎን ማስተካከል(ስብና ቅባት የበዛባቸው ምግቦችን መቀነስ)፣

6. ቀለል ይሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ጥላማ በሆኑ ቦታዎች ላይ መስራት፣

7. የአልኮል መጠጦችን አለመጠቀም/መቀነስ፣

8. ህፃናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን በተዘጉ/አየር በሌላቸው ክፍሎች ለብቻ አለመተው፣

9.የተለያየ ህመም ማለትም እንደ ከፍተኛ ደም ግፊት፣ ስኳርና የልብ ህመም ካለብዎ የህክምና ክትትልዎን በሚገባ ያድርጉ፣ የታዘዘሎትን መድሃኒት በትዕዛዙ መሰረት ይውሰዱ ሲል ከሙቀቱ ጋር ተያይዘው ከሚከሰቱ የጤና ችግሮችና ድንገተኛ ህልፈት ነዋሪዎች ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲጠብቁ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ገልጿል።

@tikvahethmagazine