Get Mystery Box with random crypto!

በዓመት ከ10 ሺ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ኩባንያ ሊቋቋም ነው። ኩ | TIKVAH-MAGAZINE

በዓመት ከ10 ሺ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ መልሶ ጥቅም ላይ የሚያውል ኩባንያ ሊቋቋም ነው።

ኩቢክ ኢትዮጵያ የተሰኘው መቀመጫውን በሀገረ አሜሪካ ያደረገው የፕላስቲክ አምራች የግል ኩባንያ በዓመት ከ10,000 ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ እንደገና ጥቅም ላይ ማዋል የሚችል ፋብሪካ በአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለመስራት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።

ኢንቨስትመንቱ በዓመት 125,000 ሜትሪክ ቶን የካርበን ልቀትን መቀነስ የሚያስችል ሲሆን በኢትዮጵያ ላለውም የግንባታና የሪል ስቴት ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ የግንባታ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ ያስችላል ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከ10,000 በላይ ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የስራ እድሎችን ለዜጎች የሚፈጥር ኩባንያ ነው ተብሎ ይጠበቃል፡፡ (IPDC)

@tikvahethmagazine