Get Mystery Box with random crypto!

ከበርካታ ባንኮች ከፍተኛ ብድር የሚወስዱ ተበዳሪዎችን የሚቆጣጠር ሕግ ሊወጣ ነው ተባለ። ከበርካታ | TIKVAH-MAGAZINE

ከበርካታ ባንኮች ከፍተኛ ብድር የሚወስዱ ተበዳሪዎችን የሚቆጣጠር ሕግ ሊወጣ ነው ተባለ።

ከበርካታ ባንኮች ብድር የሚወስዱ ተበዳሪዎችን መቆጣጠርና የብድር ክምችትን ማስተካከል የሚችል ሕግ፣ እየተሻሻለ ባለው የባንክ ሥራ አዋጅ ውስጥ ለማካተት እየተሠራ መሆኑ ተጠቁሟል።

ብሔራዊ ባንክ ሐሙስ ሚያዝያ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የፋይናንስ ስታቢሊቲ ሪፖርት (Financial Stability Report) የባንክ ብድሮች በጥቂት ተበዳሪዎች እጅ ተከማችተው እንደሚገኙ ይጠቅሳል።

በአገሪቱ ያሉት ሁሉም ባንኮች እስካለፈው ዓመት ሰኔ መጨረሻ ድረስ በሥራ ላይ ካዋሉት አጠቃላይ 1.9 ትሪሊዮን ብር ብድር ውስጥ 23.5 በመቶውን ያበደሩት ለአሥር ተበዳሪዎች እንደሆነ በሪፖርቱ ተካቷል።

ከፍተኞቹ አሥር ተበዳሪዎች ከአጠቃላይ የባንክ ብድር መጠን ውስጥ በ2014 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ከነበረው 18.7 በመቶ ነው በ2015 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ ወደ 23.5 ያደገ ነው ተብሏል።

እየተስተካከለ ያለው የባንክ ሥራ አዋጅ በብሔራዊ ባንክ ተጠናቆ ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት አለመላኩን፣ ነገር ግን እንደ የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ዓይነት ተቋማት እያዩት አስተያየታቸውን እየሰጡበት መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ ኃላፊ አረጋግጫለሁ ብሏል።

@TikvahethMagazine