Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Samitech
Cloudbridge
Traininginstitute
Silver
Platinum
Golden
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.23K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 242

2022-05-21 21:59:12 #የዛሬ (ግንቦት 13/2014)

ጤና ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር 2,898 አዳዲስ ምሩቃን ሀኪሞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመቅጠር ማስታወቂያ ቢወጣም አመልካቾች በወጥነት እንዳላመለከቱ በተደረገ ክትትል ታውቋል። በአዲስ አበባ ለ161 ጠቅላላይ ሀኪሞች ቅጥር ወጥቶ ለመቀጠረ ያመለከቱት 2,300 ሲሆኑ በተቃራኒው በሶማሌ እና አፋር ክልል ለጠቅላላ ሀኪሞች የስራ ቅጥር ቢወጣም #ምንም አመልካች ጠቅላላ ሀኪም ለማግኘት አልተቻለም ተብሏል።

የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከሚገባው እርዳታ #ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ክልሉ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል። በዚህ ሣምንት ወደ ትግራይ የገባው 15 ሺህ ቶን ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶች ሲሆን አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ወደ ክልሉ እያመራ መሆኑን WFP ገልጿል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር አዲስ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ይህም 130 ቢሊዮን ብር በላይ ከሚፈጀው ከህዳሴው ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ ሀገራዊ ፕሮጀክት ይሆናል ተብሏል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ እና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በሙሉ በቀጣይ ዓመት ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል። የዞኑ ትምህርት መምሪያ ተማሪዎቹ በቀጣይ ዓመት ለሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ምክር ቤቱ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በቦርድ እንዲመራም ወስኗል። በዚህም ለባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል። የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
12.8K viewsedited  18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 20:37:05
#SomaliRegion

የሶማሌ ፖሊስ ኮሚሽን በተለያየ ግዜ የመንግስት አገልግሎት በሚሰጡ የኢትዮ ቴሌኮም እና የመብራት መስመሮችን በመቆራረጥ ፣በመሸጥ፣ በመመሸሸግ እና በመግዛት አባሪ ተባባሪ የነበሩ 16 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
18.1K viewsedited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 18:10:56
#ጥቆማ!

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ከኮሪያ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (KOICA) ጋር በጋራ ተግባራዊ እያደረገው የሚገኝው የኢኖቬሽን ለልማት ፕሮግራም በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ወይም ዲጂታል ዘርፍ ወደ ምርት እና አገልግሎት የሚቀየሩ ኢኖቬቲቭ የቢዝነስ ሀሳቦችን አወዳድሮ ለመሽለም ጥሪ አቅርቧል።

አመልካቾች ከዚህ በታች ያለውን ድህረ ገጽ በመጠቀም ያመልክቱ። http://registration.mint.gov.et/

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.5K viewsedited  15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 16:00:06
አዲሱ ''ጫካ ፕሮጀክት'' ምንድን ነው?

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር አዲስ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ይህም 130 ቢሊዮን ብር በላይ ከሚፈጀው ከህዳሴው ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ ሀገራዊ ፕሮጀክት ይሆናል ተብሏል።

ይህ በመዲናዋ በየካ ክፍለከተማ በየካ ተራራ ላይ የሚገነባው አዲሱ ቤተመንግሥት በ503 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል ተብሏል። አምስት ወረዳዎችንም የሚነካ ሲሆን በውስጡም የአዳራሽ፣ የሰው ሰራሽ ሀይቅ፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የመንገድ ጨምሮ ሌሎች ግንባታዎችን ያካትታል።

በግንባታው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚፈናቀሉ ሲሆን ሆኖም ነዋሪዎቹ ቤተ መንግሥቱ የሚታነፅበት አካባቢ ካለው ደረጃ ጋር የሚስማማ ከሆነ በመሬታቸው ላይ የራሳቸውን ንብረት እንዲያለሙ ዕድል ይሰጣቸዋል ተብሏል።

እንደ ሪፖርተር ዘገባ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት መንግስት የተወሰነውን ወጪ የሚሸፍን እንደሚሆን ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በአካባቢው 20 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ መገንባት የጀመረ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ ተሰርቶ ተጠናቋል። የመንገድ ግንባታው ብቻውንም 15 ቢሊዮን ብር ይፈጃል ተብሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዲሱን የቤተመንግሥት ግንባታ “ጫካ ፕሮጀክት” ብለው የሰየመው ሲሆን አዲስ የሚገነባው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አካል የሆኑ ሦስት ሰው ሰራሽ ሀይቆች ግንባታን በውስጡ ይዟል።

በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚንስትር መኖሪያና ጽ/ቤት ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው የምኒልክ ቤተ መንግሥትን በአንድ ቢሊዮን ብር እድሳት ላይ ካለው የኢዮቤልዩ ቤተ-መንግስት ጋር ወደ ብሔራዊ ሙዚየምነት ሊቀየር ታስቧል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
26.1K viewsedited  13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 15:57:21
ውብ በሆነ መልክ በመረጡት ፎቶ እና ጥቅስ በእንጨት እና ቆዳ ላይ በተለያየ ሳይዝ ለማሰራት ከፈለጉ በዚ 0927840730 ይዘዙ።
ዋጋ እና ለበለጠ መረጃ...
#share
#like
#join
@kiyaengraving
21.8K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 15:57:21
የስራ ማግኛ ኦንላይን ፕላትፎርም /ሊንኮችህ/ ዝርዝር ለማግኘት

Join our telegram

https://t.me/+Zhm6yWqPh7U0N2E0
21.1K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 15:02:06
#Update: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህንፃ ቀለማት ስታንዳርድን (Brand ) አጥንቶ ለውይይት ይፋ አድርጓል። ለከተማዋ የሚስማሙ 13 አይነት ቀለማት ተለይተዋል ሲል ነው ያስታወቀው፡፡

ለከተማዋ በብራንድነት ከተመረጡት ቀለማት መሃከል የህንፃ ባለንብረቶች የሚመርጡትን ወስደው የመጠቀም መብት ያላቸው ሲሆን ይህ አሰራር በሙከራ ደረጃ በተወሰኑ ክ/ከተሞች ተጀምሮ ወደ ትግበራ ገብቷል ብሏል፡፡

ፎቶ: የተመረጡት ቀለማት

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
22.0K viewsedited  12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 13:06:35
#WeeklyUpdate

ባሳለፍነው ሳምንት 102 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 14 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር የወጭ ፣ በድምሩ 116 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹ መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል።

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 30 ነጥብ 5 ሚሊዮን፣ 18ነጥብ 7 ሚሊዮን እና 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.5K viewsedited  10:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 13:02:56
የአፍሪካ ልማት ባንክ የምግብ እጥረትን ለመከላከል የሚውል 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር አጸደቀ፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ በአኅጉሪቱ በሚገኙ ሀገራት የምግብ እጥረት እንዳይከሰት ለመከላከል ያስችላል ያለውን 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ያጸደቀው ድጋፍ በዩክሬን እና በሩስያ ጦርነት የተከሰተውን የአቅርቦት እጥርት ለመሸፈን ነው ብሏል።

ድጋፉ 30 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እህል እንደሚገዛበት ተገልጿል። ድጋፉ ከሩስያ እና ከዩክሬን ወደ አፍሪካ የሚገቡትን ስንዴ፣ ቦቆሎና አኩሪ አተር አቅርቦትን የሚተካ መሆኑ ተመልክቷል።

በተጨማሪም አሁን የጸደቀው ድጋፍ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረግ ጥረትን ለማገዝና ለአርሶ አደሮች ምርጥ ዘር ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ባንኩ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
21.6K viewsedited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 11:08:37
የአዲስ አበባ ፖሊስ 1ሺሕ 196 የፖሊስ አባላት ዛሬ አስመርቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለአራት ወር ከ15 ቀናት ያሰለጠናቸውን 1ሺሕ 196 የፖሊስ አባላት በዛሬው ዕለት አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 789 ወንዶች ሲሆኑ 407 ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.7K viewsedited  08:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ