Get Mystery Box with random crypto!

#WeeklyUpdate ባሳለፍነው ሳምንት 102 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እ | TIKVAH-MAGAZINE

#WeeklyUpdate

ባሳለፍነው ሳምንት 102 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና 14 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር የወጭ ፣ በድምሩ 116 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹ መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል።

የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት ሞያሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና ድሬድዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ሲሆኑ በቅደም ተከተላቸው 30 ነጥብ 5 ሚሊዮን፣ 18ነጥብ 7 ሚሊዮን እና 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሀኒት ፣ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ እቃዎች የጦር መሳሪያዎች፣ጫት፣ አደንዛዥ እጾች እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል ተብሏል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot