Get Mystery Box with random crypto!

የአፍሪካ ልማት ባንክ የምግብ እጥረትን ለመከላከል የሚውል 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር አጸደቀ፡፡ | TIKVAH-MAGAZINE

የአፍሪካ ልማት ባንክ የምግብ እጥረትን ለመከላከል የሚውል 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር አጸደቀ፡፡

የአፍሪካ ልማት ባንክ በአኅጉሪቱ በሚገኙ ሀገራት የምግብ እጥረት እንዳይከሰት ለመከላከል ያስችላል ያለውን 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ያጸደቀው ድጋፍ በዩክሬን እና በሩስያ ጦርነት የተከሰተውን የአቅርቦት እጥርት ለመሸፈን ነው ብሏል።

ድጋፉ 30 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እህል እንደሚገዛበት ተገልጿል። ድጋፉ ከሩስያ እና ከዩክሬን ወደ አፍሪካ የሚገቡትን ስንዴ፣ ቦቆሎና አኩሪ አተር አቅርቦትን የሚተካ መሆኑ ተመልክቷል።

በተጨማሪም አሁን የጸደቀው ድጋፍ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በራስ አቅም ለመሸፈን የሚደረግ ጥረትን ለማገዝና ለአርሶ አደሮች ምርጥ ዘር ለማቅረብ የሚያስችል መሆኑን ባንኩ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot