Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ (ግንቦት 13/2014) ጤና ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋሮች ጋር በመ | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ (ግንቦት 13/2014)

ጤና ሚኒስቴር እና ገንዘብ ሚኒስቴር ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር 2,898 አዳዲስ ምሩቃን ሀኪሞችን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመቅጠር ማስታወቂያ ቢወጣም አመልካቾች በወጥነት እንዳላመለከቱ በተደረገ ክትትል ታውቋል። በአዲስ አበባ ለ161 ጠቅላላይ ሀኪሞች ቅጥር ወጥቶ ለመቀጠረ ያመለከቱት 2,300 ሲሆኑ በተቃራኒው በሶማሌ እና አፋር ክልል ለጠቅላላ ሀኪሞች የስራ ቅጥር ቢወጣም #ምንም አመልካች ጠቅላላ ሀኪም ለማግኘት አልተቻለም ተብሏል።

የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከሚገባው እርዳታ #ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ክልሉ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል። በዚህ ሣምንት ወደ ትግራይ የገባው 15 ሺህ ቶን ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶች ሲሆን አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ወደ ክልሉ እያመራ መሆኑን WFP ገልጿል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር አዲስ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ይህም 130 ቢሊዮን ብር በላይ ከሚፈጀው ከህዳሴው ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ ሀገራዊ ፕሮጀክት ይሆናል ተብሏል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያልወሰዱ እና ፈተናውን ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በሙሉ በቀጣይ ዓመት ፈተናውን እንደሚወስዱ ተገልጿል። የዞኑ ትምህርት መምሪያ ተማሪዎቹ በቀጣይ ዓመት ለሚሰጠው ፈተና ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ደንብን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ምክር ቤቱ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ በቦርድ እንዲመራም ወስኗል። በዚህም ለባለሥልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሹመዋል። የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የቦርድ ሰብሳቢ ሆነዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot