Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.56K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 241

2022-05-30 12:22:42
የድምጽ ብክለትን ለመከላከል አዲስ ህግ ሊወጣ ነው ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን ከመጠን በላይ የድምጽ ብክለት ለመከላከል አዲስ ህግ ሊወጣ መሆኑ ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡ ከዚህ በፊት በመዲናዋ የድምጽ ብክለት የሚከለክል ህግ ቢኖርም ተግባራዊ ማድረግ ላይ ክፍተቶች እንደነበሩ ነው የተነገረው፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እንደተናገሩት፣ ከተማዋ በድምጽ የብጥብጥ እና የረብሻ ከተማ ከሆነች ሰነባብታለች ሲሉ ተናግረዋል ሲል ዘገባው አክሏል፡፡

በየመንገዱ በህገ-ወጥ መንገድ ከፍተኛ ድምጽ በመጠቀም፣ የንግድ ስራ የሚሰሩ ሰዎች የዜጎችን እና የከተማዋን ሰላም እየነሱ እንደሚገኙም ነው ሥራ አስኪያጁ የገለጹት፡፡

በዓለማችን ካሉ ከተሞች አዲስ አበባ ከፍተኛ የድምጽ ብክለት ከሚያስተናግዱ ከተሞች መካከል ከቀዳሚዎቹ ዉስጥ እንደምትጠቀስ፥ ለዚህም ከተማ አስተዳደሩ ውጤታማ እና ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የድምጽ ብክልት የሚከለክል ህግ እያዘጋጀ መሆኑን መግለጻቸውን ዘገባው አንስቷል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.6K viewsedited  09:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 11:04:09
#Update

የፍትህ ሚኒስቴር ባለፉት አራት ዓመታት በባንኮች ላይ ደረሰ ያለው የ 1.8 ቢሊየን ብር ምዝበራ 50 ነጥብ 7 በመቶ የደረሰው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ነው።

በመቀጠል ከፍተኛ ምዝበራ ያጋጠማቸው አቢሲኒያ ባንክ (328.9 ሚሊየን ብር)፣ ኦሮሚያ ባንክ (161.8 ሚሊየን ብር) እና ወጋገን ባንክ (155.6 ሚሊየን ብር) ናቸው።

የፍትህ ሚኒስቴር ዲኤታ ፍቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት በባንኮች ላይ የሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች የተለያየ መልክ የሚከተሉ በመሆናቸው የሚያደርሱት ቀውስና አደጋ ከፍተኛ ነው። (ሪፖርተር)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
23.1K viewsedited  08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 10:56:51
#Harar

ማዕዶት የኪነ ጥበብ ማህበር ከሐረሪ ክልል ደም ባንክ ጋር በጋራ በመተባበር በነገው ዕለት ሁለተኛ ዙር ልዩ የደም ልገሳ ፕሮግራም #በሐረር_ከተማ ማዘጋጀቱን በ @tikvahmagbot አማካኝነት አሳውቆናል።

በመሆኑም በሐረር የምትገኙ የቲክቫህ ቤተሰቦች ነገ ማክሰኞ ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11 ሰዓት ስላሴ ቤተክርስቲያን አካባቢ በመገኘት ደም እንድትለግሱ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethmagazine
21.5K viewsedited  07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 10:49:10
ከ2009 ጀምሮ በተደረገ ጥናት ከኢትዮጵያ ባንኮች ላይ ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ባላይ መመዝበሩ ይፋ ተደረገ።

ወንጀል ከ1 ቢሊየን 896 ሚሊየን ብር በላይ መመዝበሩን በፍትህ ሚኒስቴር የተደረገ ጥናት ይፋ ሆኗል። ከ2009 ጀምሮ በተካሄደው በዚህ ጥናት ከ370 ቢሊየን ብር በላይ በባንኮች ላይ ማጭበርበር ተሞክሮ እንደነበር ተመላክቷል።

ጥናቱን ተከትሎ የፍትህ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ እና የተለያዩ ባንኮች ፕሬዚዳንቶች፣ የኢትዮ ቴሌኮምና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው። (FBC)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
19.0K viewsedited  07:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 10:39:49
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ73 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት 219 የትራፊክ አደጋዎች ተከስቶ የ73 ሰዎች ህይወት መቅጠፉ ተገልጿል።

በአደጋዎቹ፥ 119 ዜጎች ለከባድ የአካል ጉዳት፤ በ25 ሰዎች ደግሞ ለቀላል የአካል ጉዳት ሲዳረጉ ከስድስት ሚሊዮን ብር ጉዳት በንብረት ላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ካሉ ዞኖች ከፍተኛዉን ቁጥር የያዘዉ ቤንች ሸኮ ዞን ሲሆን 74 አደጋ በዞኑ ሲመዘገብ የ25 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል። በ47 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ተመዝግቧል።

የዳውሮ ዞን 59 አደጋዎች፤ ካፋ ዞን 46 አደጋዎች፤ በኮንታ ዞን 25 አደጋዎች፤ ሸካ ዞን 10 አደጋዎችና በምእራብ ኦሞ ዞን 5 አደጋዎች መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር አደጋ መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር በድሩ ማሞ ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
18.4K viewsedited  07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 10:37:46
#Update : በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ ያሳድገዋል የተባለው በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ዛሬ ተመርቆ አገልግሎት ጀምሯል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
17.3K viewsedited  07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 22:38:51 #የዛሬ ( ግንቦት 21/2014)

ለሰብዓዊነት ሲባል የግጭት ማቆም ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ ከፍተኛ ነው የተባለው የሰብዓዊ እርድታ ወደ ትግራይ ተጓጉዟል። ዓርብ ዕለት ከአፋር ሰመራ ከተማ 215 የምግብ እርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ አቅንተዋል። የግብረ ሰናይ ተቋማት በትግራይ ክልል 5.2 ሚሊዮን ሰዎችን ለመመገብ በየሳምንቱ በ500 ከባድ ተሽከርካሪዎች የተጫነ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ክልሉ ሊደርስ እንደሚገባ እየገለፁ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ በ2015 በጀት ዓመት ወደ 3.8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ያስፈልጋታል፡፡ ከዚህ የነዳጅ ፍላጎት ለዓመቱ ከሚያስፈልገው ነጭ ናፍጣ ግማሽ ያህሉን 1,600 ሜትሪክ ቶንና 860 ሺ ሜትሪክ ቶን ቤንዚን በቪቶል ባህሪን ኩባንያ በኩል ሚቀርብ ነው፡፡ ለዚህ አቅርቦት ኢትዮጵያ 2.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታደርጋለች፡፡ ይህ ወጪ በ2014 ለዓመት ለሚያስፈልጋት ነዳጅ ያወጣችውን ያህል በ2015 ለግማሽ ፍጆታዋ የምትውለው ነው። በባህሪኑ ኩባንያ ከሚገባው ነዳጅ ሌላ ቀሪውን የ2015 የነዳጅ ፍላጎት ቀጥታ ሚሞላው በጨረታ በሚደረግ ግዥ ነው፡፡ ቀሪውን ነዳጅ ወደ አገር ለማስገባት ተጨማሪ 2.8 ቢሊዮን ዶላር ይጠይቃል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸውን 136 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች አስረክቧል። በዚህ ዓመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ ዛሬ ከ324 የሜካናይዜሽን ትራክተር ለአርሶአደሮች መስጠቱን የተነገረ ሲሆን በቀጣይ የ2014 መጨረሻዎች 700 ትራክተሮችን፤ በቀጣይ አምስት ዓመታት ደግሞ ከ26,000 ትራክተሮች በላይ ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ ታቅዷል ተብሏል።

በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ መካከል ሲደረግ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ምዘናን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሳድጋል የተባለው ፕሮጀክት በሦሥቱ አገሮች ተፈርሞ ጸድቋል። በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የሚመረቁ ተማሪዎችና መምህራን በሦሥቱ አገሮች ተንቀሳቅሰው የመስራት ዕድል ይፈጠርላቸዋል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ የጌዲዮ የባህል ማዕከል እንዲገነባ 5ሺህ ካሬ መሬት ቦታ ለዞኑ አስተዳደር አስረክቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
8.5K viewsedited  19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 14:45:06
በአማራ ክልል 136 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች ተበረከተ።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸውን 136 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች አስረክቧል።

በዚህ ዓመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ ዛሬ ከ324 የሜካናይዜሽን ትራክተር ለአርሶአደሮች መስጠቱንም የክልሉ የግብርና ቢሮ ሀላፊው ዶ/ር ሀይለማርያም ከፍያለው ተናግረዋል።

ሀላፊው አክለውም ግብርናውን በማዘመን በቀጣይ የ2014 መጨረሻዎች 700 ትራክተሮችን እንደሚያቀርቡ በመግለጽ በቀጣይ አምስት አመታት ከ26,000 ትራክተሮች በላይ ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ አቅዶ እየሰራ እንደሆ ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
24.0K viewsedited  11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 14:43:55
በመዲናዋ በትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ።

በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

የትራፊክ አደጋው የደረሰው 13 ሰዎችን አሳፍሮ ከእንጦጦ ወደ ቁስቋም ይጓዝ የነበረ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ገደል ውስጥ በመግባቱ ነው፡፡

የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ÷ አሽከርካሪዎች በኃላፊነት ስሜት ፍጥነታቸውን ቀንሰው በማሽከርከር የዜጎችን ህይወትና ንብረት ከአደጋ መጠበቅ አለባቸው ማለታቸውን ከጉለሌ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
21.5K viewsedited  11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 14:43:41
ውብ በሆነ መልክ በመረጡት ፎቶ እና ጥቅስ በእንጨት እና ቆዳ ላይ በተለያየ ሳይዝ ለማሰራት ከፈለጉ በዚ 0927840730 ይዘዙ።
ዋጋ እና ለበለጠ መረጃ...
#share
#like
#join
@kiyaengraving
18.6K views11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ