Get Mystery Box with random crypto!

በመዲናዋ በትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ። በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አ | TIKVAH-MAGAZINE

በመዲናዋ በትራፊክ አደጋ የሰዎች ህይወት አለፈ።

በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ11 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

የትራፊክ አደጋው የደረሰው 13 ሰዎችን አሳፍሮ ከእንጦጦ ወደ ቁስቋም ይጓዝ የነበረ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ገደል ውስጥ በመግባቱ ነው፡፡

የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ÷ አሽከርካሪዎች በኃላፊነት ስሜት ፍጥነታቸውን ቀንሰው በማሽከርከር የዜጎችን ህይወትና ንብረት ከአደጋ መጠበቅ አለባቸው ማለታቸውን ከጉለሌ ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot