Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል 136 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች ተበረከተ። የአማራ ክልል ግብርና | TIKVAH-MAGAZINE

በአማራ ክልል 136 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች ተበረከተ።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸውን 136 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች አስረክቧል።

በዚህ ዓመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ ዛሬ ከ324 የሜካናይዜሽን ትራክተር ለአርሶአደሮች መስጠቱንም የክልሉ የግብርና ቢሮ ሀላፊው ዶ/ር ሀይለማርያም ከፍያለው ተናግረዋል።

ሀላፊው አክለውም ግብርናውን በማዘመን በቀጣይ የ2014 መጨረሻዎች 700 ትራክተሮችን እንደሚያቀርቡ በመግለጽ በቀጣይ አምስት አመታት ከ26,000 ትራክተሮች በላይ ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ አቅዶ እየሰራ እንደሆ ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot