Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ ( ግንቦት 21/2014) ለሰብዓዊነት ሲባል የግጭት ማቆም ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ ከፍተ | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ ( ግንቦት 21/2014)

ለሰብዓዊነት ሲባል የግጭት ማቆም ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ ከፍተኛ ነው የተባለው የሰብዓዊ እርድታ ወደ ትግራይ ተጓጉዟል። ዓርብ ዕለት ከአፋር ሰመራ ከተማ 215 የምግብ እርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ አቅንተዋል። የግብረ ሰናይ ተቋማት በትግራይ ክልል 5.2 ሚሊዮን ሰዎችን ለመመገብ በየሳምንቱ በ500 ከባድ ተሽከርካሪዎች የተጫነ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ክልሉ ሊደርስ እንደሚገባ እየገለፁ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ በ2015 በጀት ዓመት ወደ 3.8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ ያስፈልጋታል፡፡ ከዚህ የነዳጅ ፍላጎት ለዓመቱ ከሚያስፈልገው ነጭ ናፍጣ ግማሽ ያህሉን 1,600 ሜትሪክ ቶንና 860 ሺ ሜትሪክ ቶን ቤንዚን በቪቶል ባህሪን ኩባንያ በኩል ሚቀርብ ነው፡፡ ለዚህ አቅርቦት ኢትዮጵያ 2.8 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ታደርጋለች፡፡ ይህ ወጪ በ2014 ለዓመት ለሚያስፈልጋት ነዳጅ ያወጣችውን ያህል በ2015 ለግማሽ ፍጆታዋ የምትውለው ነው። በባህሪኑ ኩባንያ ከሚገባው ነዳጅ ሌላ ቀሪውን የ2015 የነዳጅ ፍላጎት ቀጥታ ሚሞላው በጨረታ በሚደረግ ግዥ ነው፡፡ ቀሪውን ነዳጅ ወደ አገር ለማስገባት ተጨማሪ 2.8 ቢሊዮን ዶላር ይጠይቃል።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተለያዩ የፈረስ ጉልበት ያላቸውን 136 ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ለአርሶአደሮች አስረክቧል። በዚህ ዓመት ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ ዛሬ ከ324 የሜካናይዜሽን ትራክተር ለአርሶአደሮች መስጠቱን የተነገረ ሲሆን በቀጣይ የ2014 መጨረሻዎች 700 ትራክተሮችን፤ በቀጣይ አምስት ዓመታት ደግሞ ከ26,000 ትራክተሮች በላይ ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ ታቅዷል ተብሏል።

በኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ መካከል ሲደረግ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ምዘናን ወደ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያሳድጋል የተባለው ፕሮጀክት በሦሥቱ አገሮች ተፈርሞ ጸድቋል። በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የሚመረቁ ተማሪዎችና መምህራን በሦሥቱ አገሮች ተንቀሳቅሰው የመስራት ዕድል ይፈጠርላቸዋል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ የጌዲዮ የባህል ማዕከል እንዲገነባ 5ሺህ ካሬ መሬት ቦታ ለዞኑ አስተዳደር አስረክቧል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot