Get Mystery Box with random crypto!

የድምጽ ብክለትን ለመከላከል አዲስ ህግ ሊወጣ ነው ተባለ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን | TIKVAH-MAGAZINE

የድምጽ ብክለትን ለመከላከል አዲስ ህግ ሊወጣ ነው ተባለ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ያለውን ከመጠን በላይ የድምጽ ብክለት ለመከላከል አዲስ ህግ ሊወጣ መሆኑ ኢትዮ ኤፍ ኤም ዘግቧል፡፡ ከዚህ በፊት በመዲናዋ የድምጽ ብክለት የሚከለክል ህግ ቢኖርም ተግባራዊ ማድረግ ላይ ክፍተቶች እንደነበሩ ነው የተነገረው፡፡

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ እንደተናገሩት፣ ከተማዋ በድምጽ የብጥብጥ እና የረብሻ ከተማ ከሆነች ሰነባብታለች ሲሉ ተናግረዋል ሲል ዘገባው አክሏል፡፡

በየመንገዱ በህገ-ወጥ መንገድ ከፍተኛ ድምጽ በመጠቀም፣ የንግድ ስራ የሚሰሩ ሰዎች የዜጎችን እና የከተማዋን ሰላም እየነሱ እንደሚገኙም ነው ሥራ አስኪያጁ የገለጹት፡፡

በዓለማችን ካሉ ከተሞች አዲስ አበባ ከፍተኛ የድምጽ ብክለት ከሚያስተናግዱ ከተሞች መካከል ከቀዳሚዎቹ ዉስጥ እንደምትጠቀስ፥ ለዚህም ከተማ አስተዳደሩ ውጤታማ እና ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የድምጽ ብክልት የሚከለክል ህግ እያዘጋጀ መሆኑን መግለጻቸውን ዘገባው አንስቷል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot