Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በጌዴኡፋ ቋንቋ ተተርጉሞ በገደብ ከተማ ባሉ ት/ቤቶች እየተዘመረ ነው። | TIKVAH-MAGAZINE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በጌዴኡፋ ቋንቋ ተተርጉሞ በገደብ ከተማ ባሉ ት/ቤቶች እየተዘመረ ነው።

በጌዴኦ ዞን በገደብ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች የራሳቸውን ቋንቋ በመጠቀም ስለ ሀገራቸው እንዲያዉቁ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ተተርጉሞ እየተጠቀሙ መሆኑ ተገልጿል።

የገደብ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የጌዴኡፋ ቋንቋ መምህርት የሆኑት መሠረት ከበደ በትምህርት ቤታችን ብሔራዊ መዝሙሩ በጌዴኡፋ ቋንቋ መተርጎሙ ተማሪዎች የመዝሙሩን ትርጉም በቀላሉ ለመረዳት አስችሏቸዋል ብለዋል።

ትውልዱ የራሱን ባህላዊ እሴቶችን እና ቋንቋውን እንዲያሳድጉ እና እንድያበለፀግ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በትኩረት መሠራት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል ሲል የዘገበው የገደብ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot