Get Mystery Box with random crypto!

በግንባታ ላይ ባለው ከባህር ዳር- ወልዲያ - ኮምቦልቻ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ስርቆት ተፈጸመ። | TIKVAH-MAGAZINE

በግንባታ ላይ ባለው ከባህር ዳር- ወልዲያ - ኮምቦልቻ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ስርቆት ተፈጸመ።

ከባህር ዳር-ወልዲያ -ኮምቦልቻ በግንባታ ላይ ባለ 400 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ስርቆት መፈጸሙን ፖሊስ አስታወቀ።

ድርጊቱ የተፈጸመው በአምባሰል ወረዳ 05 ቀበሌ ልዩ ስሙ አባ ይመሬ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን 3 ሺህ ዶላር ግምት ያለው የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ስርቆት ተፈጽሟል ነው የተባለው።

በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በተፈፀመው የስርቆት ወንጀልም የኤክትሪክ ማስተላለፊያ ምሰሶ ብሎኖች በዘራፊዎች ተፈተው መወሰዳቸው ነው ከወረዳው የተገኘው መረጃ የሚያሳየው።

የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታውን እያከናወነ ያለው ታታ ፕሮጀክት የተባለ የህንድ ድርጅት ሲሆን ስርቆቱን የፈፀሙ ተጠርጣሪዎችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግም ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን በወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የታክቲክ ወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር መስፍን ይመር ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot