Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ73 ሰዎች ህይወት አለፈ። በ | TIKVAH-MAGAZINE

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ባለፉት 9 ወራት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ73 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት 219 የትራፊክ አደጋዎች ተከስቶ የ73 ሰዎች ህይወት መቅጠፉ ተገልጿል።

በአደጋዎቹ፥ 119 ዜጎች ለከባድ የአካል ጉዳት፤ በ25 ሰዎች ደግሞ ለቀላል የአካል ጉዳት ሲዳረጉ ከስድስት ሚሊዮን ብር ጉዳት በንብረት ላይ መድረሱን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ካሉ ዞኖች ከፍተኛዉን ቁጥር የያዘዉ ቤንች ሸኮ ዞን ሲሆን 74 አደጋ በዞኑ ሲመዘገብ የ25 ሰዎች ህይወት ደግሞ አልፏል። በ47 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ተመዝግቧል።

የዳውሮ ዞን 59 አደጋዎች፤ ካፋ ዞን 46 አደጋዎች፤ በኮንታ ዞን 25 አደጋዎች፤ ሸካ ዞን 10 አደጋዎችና በምእራብ ኦሞ ዞን 5 አደጋዎች መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር አደጋ መከላከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር በድሩ ማሞ ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot