Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Update
Sale
Packingmachine
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.56K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 238

2022-06-02 17:40:55
#FreelanceEthiopia

በትርፍ ሰዓትዎ ከሚሰርዋቸው ሥራዎች ጀምሮ እንደ ትምህርት ደርጃዎ፣ የሥራ ልምድዎ እና ፍላጎትዎ በሁሉም አይነት ዘርፎች ሁሉንም አይነት ሥራዎች በአንድ ቦታ ያገኛሉ።

ለመቀላቀል ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ፦

https://t.me/+HZktkFNrwzg3Y2Fk
13.5K views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 17:15:45
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ''ፋይላችን ጠፋብን'' የሚለውን ቅሬታ ለመፍታት የፋይል ማደራጀት ዘመቻ እየተከናወነ ነው ተብሏል።

በአዲስ አበባ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ መሬት ልማት እና አስተዳደር ጽ/ቤት ከግንቦት 18 ቀን/2014 ጀምሮ እስከ ሰኔ 08/2014 የሚሰጠውን መደበኛ አገልግሎት በጊዜያዊነት በማቆም ፋይሎቹን በተደራጀ እና ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ኮድ ለመስጠት ሁሉንም የጽ/ቤቱን ሰራተኞች በማስተባበር በዘመቻ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ለ15 ቀናት ያህል መደበኛውን አገልግሎት ቆሞ በተሰራው ሥራ ከእቅዱ ቀድነው እቅድ ውስጥ 60 በመቶ የሚሆነውን ማጠናቀቃቸውን የመሬት ልማት አስተዳደር ምክትል ጽ/ቤት ሀላፊ ከሆኑት አቶ ተስፋዬ ግርማ ተናግረዋል።

በዚህም 50 ሺህ የሚያክሉት ኮድ የተሰጣቸው ሲሆን 25 ሺ የሚሆኑ ማህደራትን ደግሞ ወደ ኮምፒዩተር 'in code' ተደርገው መገልበጣቸውን ገልጸዋል፡፡

በክፍለከተማው ከቦሌ እና ከየካ የዞሩ ፋይሎች መኖራቸው የተገለጸ ሲሆን በክፍለ ከተማው በተደጋጋሚ ከሚነሱት ቅሬታዎች ዋናው ''ፋይላችን ጠፋብን'' የሚል ነው። ''ፋይሎቹን አደራጅተን ስንጨርስ ቢያንስ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነውን የህበረተሰቡን ጥያቄ እንመልሳለን'' ሲሉ ምክትል ጽ/ቤት ሀላፊው ተናግረዋል።

ከቦሌ እና ከየካ ከሚመጡ ፋይሎች በተጨማሪ ክ/ከተማው በራሱ እስከ አሁን ከ 300 በላይ አዳዲስ ፋይሎችን ማደራጀቱ የተገለጸ ሲሆን ወደፊትም ከአርሶ አደር መብት ፈጠራ ጋር ተያይዞ የሚሰሩ ሥራዎች መኖራቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
15.1K viewsedited  14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 17:00:57
በባንኮች የደንበኞች የቁጠባ ሂሳብ መጠን 1 ነጥብ 6 ትሪሊየን ብር ደርሷል።

እስከ መጋቢት 2014 ዓ.ም ድረስ በባንኮች የደንበኞች የቁጠባ ሂሳብ መጠን 1 ነጥብ 6 ትሪሊየን ብር መድረሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

የባንኩ የሱፐርቪዥን ዳሬክተር ፍሬዘር አያሌው አጠቃላይ ባንኮች የሰጡት የብድር መጠንም 1.5 ትሪሊየን ብር መሆኑንና የተበዳሪዎች ቁጥርም ከ350 ሺህ ማለፋን ገልጸዋል።

ከቁጠባ ተደራሽነት አንጻር የተሻለ ቢሆንም የብድር ተደራሽነቱ ግን በአብዛኛው ለትልልቅ ተበዳሪዎች የተሰጠ በመሆኑ ውስንነት ያለበት መሆኑን ጠቁመዋል።

በእርሻና ጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም አነስተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የተሰጠው ብድር ዝቅተኛ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ይሻል ብለዋል።

በግል ባንኮች በቂ የገንዘብ ክምችት አለመኖርና የብድር ስጋት መጨመር ለብድር ተደራሽነት ዝቅተኛ መሆን በምክንያትነት ተቀምጠዋል። (ENA)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
15.0K viewsedited  14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 16:48:35
የኮንሶ ዞን አስተዳደር እና የኮንሶ ህዝብ ለጂንካ ዩኒቨርስቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ያደረገው ደማቅ አቀባበል

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
25.5K viewsedited  13:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 16:31:51
#UPDATE

በጋምቤላ ክልል የተምች ወረርሽኝ በአምስት ወረዳዎች ውስጥ በ7 ሺህ 446 ሄክታር መሬት ላይ መከሰቱን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

ወረርሽኙ በክልሉ ወረርሽኙ የተከሰተው በዲማ፣ በላሬ፣ በኢታንግ፣ በጎደሬ እና በጋምቤላ ወረዳ እንደሆነ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ኩዌት ሉል ገልጸዋል።

ተባዩን ለማጥፋት በተደረገ ጥረት በባህላዊ እና ፀረ ተባይ በመርጨት 1376 ሄክታር ሰብልን ለመቆጣጠር መቻሉን ቢሮው ጨምሮ አመልክቷል።

በዲማ ወረዳ የኮይ ቀበሌ ሳሙና ዳገት ንዑስ ነዋሪ የሆኑት አርሶአደር ተኩሴ አበባውና እና አርሶ አደር መሀመድ ኡመር በሰጡት አስተያየት በአካባቢያቸው ከግንቦት ወር መግቢያ ጀምሮ የተከሰተው የተምች ወረርሽኝ በሩዝ ማሳዎቻቸው ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

ወረርሽኙ አሁን ባለው ሁኔታ በባህላዊ መንገድ ለመከላከል አዳጋች እንደሆነ የጠቀሱት አርሶአደሮቹ በዚህም የምርት መቀነስ ሊያጋጥም ይችላል የሚል ሥጋት እንዳደረባቸው ተናግረዋል።

መንግስት ከዚህ ቀደም ፀረ ተባይ ኬሚካል አሰራጭቶ ከማሳቸው የተወሰነ ሰብል ማትረፍ መቻላቸውን ገልፀው በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በ2014/15 ምርት ዘመን በመኸር እርሻ 148 ሺህ 786 ሄክታር በማልማት ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እስካሁን 72 ሺህ 708 ሄክታር በዘር ተሸፍኗል ተብሏል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
15.0K viewsedited  13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 16:31:08
#ELiDAEthiopia

ኢምፓቲ ፎር ላይፍግሬትድ ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን /ኢሊዳ/ የተቀናጀ የልማት ስራን በመስራት ሴቶችን፣ ልጃገረዶችን፣ ወጣቶችን እና ህጻናትን በትምህርት፣ በጤና እና በኢኮኖሚ በመደገፍ እንዲሁም በዲሞክራሲ ባህል ግንባታ እና ሰላም ላይ የሚሰራ እና ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን የሚወጡ ምርታማ እና አርቆ አሳቢ ዜጎች ማፍራትን አላማ አድረጎ በ 2008 (እ.ኤ.አ) በሴቶች የተመሰረት ሀገር በቀል የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅት ነው፡፡

ኢሊዳ በአዲስ አባበ ከተማ መስተዳደር እንዲሁም፣ በአማራ እና አፋር ክልላዊ መንግስታት የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ቢሮዎችን በመክፈት ሰፊ የልማት ስራዎች እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች ላይ ሰላምን መልሶ መገንባት እና ግጭት አፈታት ላይ በማተኮር የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን እንዲሁም በአፋር ክልል በጦርነት ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመሰብሰብ የተለያየ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

For English

° Website ° Facebook ° Twitter ° Telegram
14.1K viewsedited  13:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 23:42:25 #የዛሬ (ግንቦት 24/2014)

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ "ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፍቃድ ሳይኖራቸው በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ህዝብን ለመለያየት ሌት ተቀን የሚሰሩ 111 ህገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውን አረጋግጫለሁ" ያለ ሲሆን 10 ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል። [ በቁጥጥር ስር ስለዋሉት እንዲሁም የሚዲያዎቹ ዝርዝር በመግለጫው አልተካተተም ]

ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ 8,588 መምህራን የሞያ ብቃት ምዘና መውሰድ ይጀምራሉ ተብሏል። የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ስንታየሁ ማሞ በሰጡት ቃል ፥ " በስምንት ክ/ከተሞች ላይ ምዘና ይካሄዳል። እዚህ ምዘና ላይ የግል ትምህርት ቤቶች ተመዝግበው በየትምህርት ቤቶቻቸው ስም ዝርዝራቸው ተለጥፏል " ብለዋል።

በኢትዮጵያ ያለው ድርቅ 1.75 ሚሊየን ህዝብን ከመኖሪያ ቀዬው አፈናቋል። ድርቁ በአራት ክልሎች (ኦሮሚያ፣ ሶማሊ፣ አፋርና ደቡብ) 10 ሚሊየን ህዝብ ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ አሳርፏል። ከዚህ ውስጥ 1.5 ያህሉ ለተመጣጠነ የምግብ እጥረት የተዳረጉ ህጻናት ናቸው፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መካሄዱን የቀጠለ ሲሆን ዛሬ በተካሄደ ምርጫ ጉባኤው ፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ጴጦሮስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በማድረግ ሾሟል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ፤ በአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ምትክ አምባሳደር ማይክ ሀመርን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው እንደሚሾሙ አስታውቀዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
4.4K viewsedited  20:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 18:32:40
#NewsUpdate

በሕገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሲጓዙ በታንዛኒያ መንግስት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩ ኢትዮጵያውያን መካከል 20 ኢትዮያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ዛሬ የተመለሱት ኢትዮጵያዊያኑ ዕድሜያቸው ከ11 እስከ 17 መሆኑ ነው የተገለጸው።

በቀጣይ ሌሎች ዜጎም ከእስር ተፈትተው ወደ ሀገር መመለስ የሚችሉበት ሁኔታ በመንግስት በኩል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ መሆኑን በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ በአጠቃላይ ቁጥራቸው 1ሺህ 38 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው መመለስ የተቻለ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 158 ህጻናትና 880 ወንዶች ናቸው ተብሏል።

እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ 31,236 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን ከሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
18.8K viewsedited  15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 18:17:16
የፌደራል ፖሊስ 111 'ህገ-ወጥ' የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውን አረጋግጫለሁ አለ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ "ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፍቃድ ሳይኖራቸው በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ህዝብን ለመለያየት ሌት ተቀን የሚሰሩ 111 ህገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውን አረጋግጫለሁ" ብሏል ።

ፌደራል ፖሊስ አሰባሰብኩት ባለዉ መረጃ ብሄርን ከብሄር ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱትን በመለየት 10 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል። [ በቁጥጥር ስር ስለዋሉት እንዲሁም የሚዲያዎቹ ዝርዝር በመግለጫው አልተካተተም ]

የተለያዩ ግጭት ቀስቃሽ አጀንዳዎችን በመቅረጽ የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት እንዳይረጋጋ የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት በብሄር እና በሀይማኖት መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ያደረጉ መሆናቸዉን ጨምር አስታዉቋል።

የፌደራል ፖሊስ ከኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አገኘሁት ባለዉ መረጃ ግለሰቦቹ ምንም አይነት ህጋዊ ፍቃድ የሌላቸው መሆናቸዉን የሚዲያ ተከታዮቻቸውን በመጠቀም 'ሀሰተኛና ግጭት ቀስቃሽ' መረጃዎችን የሚያሰራጩት በክፍያ እንደሆነም በምርመራ ደርሼበታለሁ ሲል መግለጫው አስታዉቋል። የጀመረውንም ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
16.5K viewsedited  15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 18:15:40
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቶጎ ሎሜ በኩል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ አዲስ በረራ ዛሬ ጀመረ።

አየር መንገዱ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከፈረንጆቹ 1998 ጀምሮ ወደ ዋሽንግተን መብረር የጀመረ ሲሆን ከዚህ ቀደም በአየርላንድ ደብሊን አድርጎ በረራ ያደርግ ነበር። የዛሬው አዲስ  የበረራ መስመር አፍሪካን ከአሜሪካ ለማገናኘት ይረዳል ተብሏዋል።

በሎሜ በኩል የሚደረገው በረራ በቦይንግ 787 አውሮፕላን እንደሚደረግም ተገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 116 ዓለም አቀፍ እና 23 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች አሉት።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
13.9K viewsedited  15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ