Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ (ግንቦት 24/2014) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ 'ምንም ዓይነት | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ (ግንቦት 24/2014)

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ "ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፍቃድ ሳይኖራቸው በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ህዝብን ለመለያየት ሌት ተቀን የሚሰሩ 111 ህገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውን አረጋግጫለሁ" ያለ ሲሆን 10 ተጠርጣሪዎችንም በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል። [ በቁጥጥር ስር ስለዋሉት እንዲሁም የሚዲያዎቹ ዝርዝር በመግለጫው አልተካተተም ]

ከነገ ጀምሮ በአዲስ አበባ 8,588 መምህራን የሞያ ብቃት ምዘና መውሰድ ይጀምራሉ ተብሏል። የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት እና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ስንታየሁ ማሞ በሰጡት ቃል ፥ " በስምንት ክ/ከተሞች ላይ ምዘና ይካሄዳል። እዚህ ምዘና ላይ የግል ትምህርት ቤቶች ተመዝግበው በየትምህርት ቤቶቻቸው ስም ዝርዝራቸው ተለጥፏል " ብለዋል።

በኢትዮጵያ ያለው ድርቅ 1.75 ሚሊየን ህዝብን ከመኖሪያ ቀዬው አፈናቋል። ድርቁ በአራት ክልሎች (ኦሮሚያ፣ ሶማሊ፣ አፋርና ደቡብ) 10 ሚሊየን ህዝብ ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ አሳርፏል። ከዚህ ውስጥ 1.5 ያህሉ ለተመጣጠነ የምግብ እጥረት የተዳረጉ ህጻናት ናቸው፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መካሄዱን የቀጠለ ሲሆን ዛሬ በተካሄደ ምርጫ ጉባኤው ፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ጴጦሮስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በማድረግ ሾሟል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ፤ በአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ምትክ አምባሳደር ማይክ ሀመርን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው እንደሚሾሙ አስታውቀዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot