2022-06-02 18:07:18
በአንቡላንስ 21 ሰዎችን ጭኖ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳን ለማሻገር የሞከረው ሹፌር ፍርድ ቤት ቀረበ።
ከኦሮሚያ እና ከደቡብ ክልል አንስተው ወደ ሱዳን ለመሻገር በተለያዩ ደላሎች አማካኝነት የመጡ 21 ሰዎችን ጭኖ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳን ለማሻገር ሲያጓጉዝ የነበረ የቋራ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የአንቡላንስ ሹፌር ላይ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና በሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ።
ተከሳሹ ንጉሴ መኮነን ግንቦት 14 ቀን 20214 ዓም ከሌሊቱ 8:00 ሲሆን ኪነቢ ቀበሌ ጋንክ ጎጥ ላይ ከደላሎች በመቀበል በአምቡላንስ መኪና ጭኖ ወደ ሱዳን ለመሸኘት በማጓጓዝ ላይ እያለ ገለጉ ከተማ አለሙ በር ተብሎ ከሚጠራው ቦታ ላይ የፀጥታ አካላትንና ኬላ ጥሶ ማለፉን የክሱ መዝገብ ያስረዳል።
በዚህም የጸጥታ ኃይሎች ጥይት ለመተኮስ የተገደዱ ሲሆን በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል። ተከሳሹ ተዘዋዋሪዎቹን ወደ ጨካ እና ባዶ ቤት ወስዶ የደበቃቸው ቢሆንም ተከሳሹ እና ተዘዋዋሪዎች በፀጥታ ሀይል ክትትል ተይዘዋል ተብሏል።
ዛሬ ግንቦት 25 ቀን 2014 ዓም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ፍ/ቤት ቀርቦ የክሱ ግልባጭ ደርሶት ክሱ ተነቦለት የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ክሱን አልቃወምም የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ ተከራክሯል።
ዐቃቤ ህግም ተከሳሸ የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈፀሙ በሰውና በሰነድ ማስረጃ አረጋግጨ ክስ ሰላቀረብሁ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ይሰሙልኝ በማለት ለፍ/ቤቱ አሳስቦ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ፍ/ቤቱ አድመጧል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ካዳመጠ በሗላ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለ ሰኔ 02 ቀን 2014 ዓም ቀጠሮ ሰጥቷል።
መረጃው የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ ነው
@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
21.1K viewsedited 15:07