Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱ ''ጫካ ፕሮጀክት'' ምንድን ነው? የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር አዲስ | TIKVAH-MAGAZINE

አዲሱ ''ጫካ ፕሮጀክት'' ምንድን ነው?

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በ49 ቢሊዮን ብር አዲስ ብሄራዊ ቤተ መንግስት ለመገንባት በሂደት ላይ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል። ይህም 130 ቢሊዮን ብር በላይ ከሚፈጀው ከህዳሴው ግድብ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ ሀገራዊ ፕሮጀክት ይሆናል ተብሏል።

ይህ በመዲናዋ በየካ ክፍለከተማ በየካ ተራራ ላይ የሚገነባው አዲሱ ቤተመንግሥት በ503 ሄክታር መሬት ላይ ያርፋል ተብሏል። አምስት ወረዳዎችንም የሚነካ ሲሆን በውስጡም የአዳራሽ፣ የሰው ሰራሽ ሀይቅ፣ የመኖሪያ ቤት ግንባታ፣ የመንገድ ጨምሮ ሌሎች ግንባታዎችን ያካትታል።

በግንባታው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚፈናቀሉ ሲሆን ሆኖም ነዋሪዎቹ ቤተ መንግሥቱ የሚታነፅበት አካባቢ ካለው ደረጃ ጋር የሚስማማ ከሆነ በመሬታቸው ላይ የራሳቸውን ንብረት እንዲያለሙ ዕድል ይሰጣቸዋል ተብሏል።

እንደ ሪፖርተር ዘገባ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት መንግስት የተወሰነውን ወጪ የሚሸፍን እንደሚሆን ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን በአካባቢው 20 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ መገንባት የጀመረ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ዘጠኝ ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው መንገድ ተሰርቶ ተጠናቋል። የመንገድ ግንባታው ብቻውንም 15 ቢሊዮን ብር ይፈጃል ተብሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዲሱን የቤተመንግሥት ግንባታ “ጫካ ፕሮጀክት” ብለው የሰየመው ሲሆን አዲስ የሚገነባው የብሄራዊ ቤተ መንግስት አካል የሆኑ ሦስት ሰው ሰራሽ ሀይቆች ግንባታን በውስጡ ይዟል።

በአሁኑ ወቅት የጠቅላይ ሚንስትር መኖሪያና ጽ/ቤት ሆኖ እያገለገለ የሚገኘው የምኒልክ ቤተ መንግሥትን በአንድ ቢሊዮን ብር እድሳት ላይ ካለው የኢዮቤልዩ ቤተ-መንግስት ጋር ወደ ብሔራዊ ሙዚየምነት ሊቀየር ታስቧል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot