Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የሚገኙ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የማጽዳትና የመጠገን ሥራ እየተሰራ ነው ተባለ። | TIKVAH-MAGAZINE

በአዲስ አበባ የሚገኙ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የማጽዳትና የመጠገን ሥራ እየተሰራ ነው ተባለ።

በአዲስ አበባ የጎርፍ አደጋ ሥጋት ያለባቸው ሥፍራዎች የሚገኙ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የማጽዳትና የመጠገን ሥራ እየተሰራ መሆኑን የመዲናዋ የመንገዶች ባለሥልጣን አስታውቋል።

ከመንገድ ግንባታና ጥገና በተጨማሪ ተቋሙ ጽዳትና ጥገና ለሚያስፈልጋቸው ከ400 ኪሎ ሜትር በላይ ‘የፍሳሽ መስመር ጽዳትና ጥገና መደረጉን የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እያሱ ሰለሞን ገልጸዋል።

መጪው የክረምት ወቅት ከባድ ዝናብ እንደሚኖር የሚቲዎሮሎጅ ትንበያ እንደሚያመለክት ኃላፊው ገልጸው ይህንንም ተከትሎ የአደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን በለያቸው ሥፍራዎች የሚገኙ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን የማጽዳትና የመጠገን ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ ኅብረተሰቡ ለጽዳት ተብሎ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦይ ክዳኖች በሚከፈቱበት ወቅት ደረቅ ቆሻሻዎችን በማስወገድ መስመሮች እንዲዘጉ በማድረግ ችግሩን ማባባሱን ገልጸዋል። እስካሁን 42 ቦታዎች ላይ ጥገናና ጽዳት እየተደረገ በመሆኑ ኅብረተሰቡ እነዚህን ቦታዎች ህገ-ወጥ ተግባራት ከሚፈጽሙ ሰዎች እንዲከላከል ጠይቀዋል።

@tikvahethmagazine