Get Mystery Box with random crypto!

የጎጃም ባህል ማዕከል ግንባታ አፈጻጸም 41 በመቶ መድረሱን የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ገለጸ። | TIKVAH-MAGAZINE

የጎጃም ባህል ማዕከል ግንባታ አፈጻጸም 41 በመቶ መድረሱን የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ገለጸ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ ላይ በመገንባት የሚገኘው የጎጃም ባህል ማዕከል ግንባታ አፈጻጸም 41 በመቶ መድረሱን የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ገልጿል።

የባህል ማዕከሉ ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ፣ ሙዚየም፣ ቤተ መፅሀፍትና ሌሎች ቢሮዎችን ያካተተ መሆኑንና ከተማዋን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ጠቀሜታ እንዳለው የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌው ተናግረዋል።

በአማራ ህንፃ ስራዎች ተቋራጭነት እየተገነባ የሚገኘው ይህ የባህል ማዕከል የግንባታ ጥራቱን በጠበቀና በተገቢው የውል ስምምነት ጊዜ ለማጠናቀቅ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የድርጅቱ የጎጃም በህል ማዕከል አሰሪ መሀንዲስ አቶ ሰለሞን ቸኮል ተናግረዋል።

መረጃው የክልሉ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine