Get Mystery Box with random crypto!

አንዲት እናት እያዋለደች ባለበት ሰዓት በባሏ በጩቤ ተወግታ የተገደለችው የጤና ባለሞያ በጎፋ ዞን | TIKVAH-MAGAZINE

አንዲት እናት እያዋለደች ባለበት ሰዓት በባሏ በጩቤ ተወግታ የተገደለችው የጤና ባለሞያ

በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በዳዳ ሳታላይት ጤና ጣቢያ አዋላጅ ነርስ የነበረችው ሲ/ር ሲ/ር አማረች ዋዳ በምትሰራበት ቦታ በባሏ በጩቤ ተወግታ ህይወቷ አልፏል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ግንቦት 5 ዕለት ከጧቱ 3:00 ሰዓት ላይ አንዲት እናት እያዋለደች እንዳለ ሲሆን ገዳይ በጩቤ 5 ቦታ በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉን ፖሊስ አስታውቋል።

ከወረዳው ኮሚውኒኬሽን ቢሮ በተገኘው መረጃ መሰረት ሲ/ር አማረች ከገዳይ ባሏ ሁለት ልጆች የወለደች ሲሆን የአንድ ወንድና የአንድ ሴት እናት ነበረች።

ገዳይ በሰዓቱ በህግ ቁጥጥር ውሎ ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን መረጃው ተጣርቶ የህግ እርምጃ ሲወሰድ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

@tikvahethmagazine