Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ_2 (ግንቦት 22/2014) የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ በሰኔ ወር 2014 ዓ | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ_2 (ግንቦት 22/2014)

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ #በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል አስታውቋል። የአውሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ የመጣው ልዩነት ሙሉ በሙሉ ወደ #ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሰኑን ገልጿል።

ባለፉት ሁለት ቀናት ከጎረቤት ኤርትራ ሠራዊት ጋር አዲስ ውጊያ መካሄዱን የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀዋል። ቃል አቀባዩ ባለፈው ቅዳሜ እና እሑድ የኤርትራ ሠራዊት #በሽራሮ ጥቃት ከፍቶ ነበር ሲሉ ተናግረዋል። በኤርትራ መንግስት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም። ይህን አስመልክቶ የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ በሰጡት ቃል ተካሄደ ስለተባለው ውጊያ መረጃው እንደሌላቸው ገልጸው፣ ነገር ግን የኤርትራ ኃይሎች ጥቃት ሊፈጽሙ የሚችሉበት ሁኔታ የለም ብለዋል።

በጌዴኦ ዞን በገደብ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች የራሳቸውን ቋንቋ በመጠቀም ስለ ሀገራቸው እንዲያዉቁ፥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ተተርጉሞ እየተጠቀሙ መሆኑ ተገልጿል።

የፍትህ ሚኒስቴር ባለፉት አራት ዓመታት በባንኮች ላይ የ 1.8 ቢሊየን ብር #ምዝበራ መድረሱን አስታውቋል። ከዚህም ውስጥ 50 ነጥብ 7 በመቶ የደረሰው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ነው የተባለ ሲሆን በመቀጠል ከፍተኛ ምዝበራ ያጋጠማቸው አቢሲኒያ ባንክ (328.9 ሚሊየን ብር)፣ ኦሮሚያ ባንክ (161.8 ሚሊየን ብር) እና ወጋገን ባንክ (155.6 ሚሊየን ብር) ናቸው።

በጥሬ ዕቃ ምክንያት ላለፉት 3 ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው አዲስ የተሽከርካሪ ሠሌዳ የመስጠት አገልግሎት #ከ1ሣምንት በኋላ መሥጠት ይጀመራል ተብሏል። አሁን ላይ ግን የውጭ ምንዛሬ ተፈቅዶ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ከጀርመን ሀገር ለማስመጣት ዝግጅት ተጠናቋል ነው የተባለው።

እስካሁን በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች መያዙ የታወቀው #መንኪፖክስ ወይም የዝንጀሮ ፈንጣጣ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ይደርሳል ብለው እንደማይጠብቁ የዓለም የጤና ድርጅት ከፍተኛዋ የበሽታው ኤክስፐርት ተናግረዋል። ዶክተር ሮዛሙንድ ሉዊስ በሰጡት ማብራሪያ ድርጅታቸው መንኪፖክስ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም በአየር በትንፋሽ ይተላለፍ እንደሆን በተጨማሪም የህመም ምልክት የሌላቸው ሰዎች በሽታውን ያስተላልፋሉ ወይ የሚሉትን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎችን ይዞ እየመረመረ መሆኑን አመልክተዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል12 ወረዳዎች በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ ሰሞኑን በሩዝ ምርት ላይ የተከሰተው #ተምች አስጊ መሆኑ ተነግሯል። የዘርፉ ባለሞያዎች አሁን ላይ በሩዝ ሰብል ላይ የተከሰተው ተምች ''የአፍሪካ ፎል አርሚ ዎርም'' እንደሆነና ክስተቱ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ትልቅ ርብርብ እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot