Get Mystery Box with random crypto!

ሰሞኑን በሩዝ ምርት ላይ የተከሰተው ተምች አስጊ መሆኑ ተጠቆመ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች | TIKVAH-MAGAZINE

ሰሞኑን በሩዝ ምርት ላይ የተከሰተው ተምች አስጊ መሆኑ ተጠቆመ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከባለፈው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ የተከሰተው የተምች ወረርሽኝ በበቆሎና በሩዝ ማሳዎቻቸው ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

በተለይ በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በሩዝ ሰብል ላይ ተምች መከሰቱ ተገልጿል። በወረዳው የተሰተው ተምች በሩዝ ሰብል ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው የተጠቆመው።

የክልሉ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ የተምች ወረርሽኙ በክልሉ 12 ወረዳዎች ውስጥ በ1 ሺህ 219 ሄክታር መሬት ላይ መከሰቱን ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። በአሁኑወቅት ወረርሽኙ በክልሉ 4 ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 12 ወረዳዎች ውስጥ በ 1 ሺህ 219 ሄክታር መሬት ላይ መታየቱን ነው የገለጹት።

በተመሳሳይ በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ ኮይና ከርከን በተባሉ ሁለት ቀበሌዎች ተምች መከሰቱ ሪፖርት ተደርጓል። ተምቹ በ4000 ሄክታር መሬት የሩዝ ማሳ ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው ተብሏል።

በዲማ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት የሰብል ልማት ስራ ሂደት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጫኔ ገመቹ እንደገለፁት ከዚህ በፊት የአሜሪካን ተምች ተብሎ የሚጠራ በበቆሎ ላይ ተከስቶ እንደነበር ገልፀው አሁን የተከሰተው ተምች በዋናነት ሩዝን የሚያጠቃ ከዚህ በፊት ያልተከሰተ መሆኑን ተናግረዋል።

የዘርፉ ባለሞያዎች አሁን ላይ በሩዝ ሰብል ላይ የተከሰተው ተምች ''የአፍሪካ ፎል አርሚ ዎርም'' እንደሆነና ክስተቱ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ትልቅ ርብርብ እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot