Get Mystery Box with random crypto!

የከተማ መሬት ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ምዘናና ስልጠና በሶስት ዩኒቨርስቲዎች ተጀመረ | TIKVAH-MAGAZINE

የከተማ መሬት ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ምዘናና ስልጠና በሶስት ዩኒቨርስቲዎች ተጀመረ።

የከተማ መሬት ዘርፍ አመራርና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ምዘናና ስልጠና በባህርዳር፣ በአምቦና ወላይታ ዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኖል።

በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት በአጠቃላይ 5000 የዘርፉ አመራርና ባለሙያዎችን 16 የዘርፉ የሙያ አይነቶችና አራት የሙያ ስትሪሞችን መሰረት በማድረግ ምዘናውና ሥልጠናው ይከናወናል ተብሏል።

በዚህ በጀት ዓመትም 1000 የሚሆኑ አመራሮችና ባለሙያዎች በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች ስልጠናዉን በመውሰድ እንዲመዘኑ የሚያደርገው መርሃ ግብር ዛሬ በይፋ ተጀምሯል፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ በመገኘት የስልጠና ማስጀመሪያውን በንግግር የከፈቱት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ሰልጣኞች የከተማ ነዋሪዎች የሚንገላቱባቸውንና የሚማረሩባቸውን የመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች በዕውቀትና በዘመነ አሰራር አንዲሁም በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲከውኑ ሰልጣኖች አደራ የተጣለባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በከተሞች ገቢ ማሻሻያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪነት በሀገራችን ባሉ አምስት ዩኒቨርስቲዎች የሚካሄደው የስልጠናና የብቃት ምዘና ውጤታማ እንዲሆን ከፍተኛ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጉን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot