Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-MAGAZINE

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikvahethmagazine — TIKVAH-MAGAZINE
ርዕሶች ከሰርጥ:
Silver
Platinum
Golden
Naturaldisaster
Alert
Update
All tags
የሰርጥ አድራሻ: @tikvahethmagazine
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 196.59K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን 251913134524

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 230

2022-06-13 10:17:58
የ4 ቀናት ጉዞ ወደ ውቢቷ ዱባይ በድጋሚ ይዘንልዎ መጣን!

ከ 39,799 ብር ጀምሮ!

ቪዛ እና የደርሶ መልስ ቲኬት
ባለ 4 ወይም 5 ኮከብ ሆቴል የ4 ምሽቶች ቆይታ (ማረፊያ) ከጣፋጭ ቁርስ ጋር

ጥቅሉን ይግዙ እና ለ4 ቀናት አስገራሚ ጊዜ ያሳልፉ!

ለበለጠ መረጃ 0115621010 / 0115583058 / 0111575052 ደውለው ሊያገኙን ይችላሉ!

CLICK HERE TO DOWNLOAD OUR APP AND EASILY BOOK YOUR TICKETS

በየጊዜው የምናዘጋጃቸውን ልዩ እና በቅናሽ የቀረቡ የጉብኝት ጥቅሎችን እና የበረራ ትኬቶችን የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ያግኙ!

@fourwindstravel
20.4K views07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 23:43:58 #የዛሬ (ሰኔ 5/2014)

"እኛ በጤና ሚኒስትር በኩል በኮቪድ ላይ በኮንትራት ተቀጥረን የምንሰራ ባለሙያዎች ነን። ኮቪድ ከጀመረ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ ሆስፒታሎች ስናገለግል ቆይተናል። የጤና ሚኒሰትር እና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቋሚነት እንደተቀጠርን በደብዳቤ ገለፀው ነበር ከአንድ አመት በፊት ፤ አሁን ግን ኮንትራት ጨርሳችዋል ምንም የምናደርገው ነገር የለም ብለው ደብዳቤ ደረሰን። ምንም አንኳን ባንመሰገን ሲያልቅ መወርወር አልነበረብንም'' ፦ በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ወቅት በኮንትራንት ተቀጥረው ሲያገለግሉ የነበሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጤና ባለሞያዎች መልዕክት

ተጨማሪ ያንብቡ [ 1 , 2 ]

"የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር ሽልማት በዛሬው ዕለት ይደረግ የነበረው ወደ ሰኞ 06/10/14 ተቀይሯል። ህዝባችን ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በመምጣት ፕሮግራሙን እንድትታደሙ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ለተፈጠረው ክፍተት ሕዝባችንን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ " ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር

ዛሬ በአዳማ ከተማ የአፋርና የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ የሰላም ውይይት ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል። መድረኩ በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማምጣት አላማ ያደረገ ነው ተብሏል።

በትግርኛ የሙዚቃ ስራዎች በእጅጉ የሚታወቀው አርቲስት ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። አርቲስቱ ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበር ተነግሯል። ከሙዚቃ ስራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ፣ ወዘመይ፣ ቸቸኮላታ፣ ኣጆኺ ትግራይ፣ ቕዱስ ፀባያ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
28.2K viewsedited  20:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 23:48:26 #የዛሬ (ሰኔ 4/2014)

በነገው ዕለት የዓለምዓቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር መዝጊያ ፕሮግራም በስታድየም ይደረጋል ተብሎ የተገለጸ ቢሆንም አንዳንድ ዶክመንቶች በጊዜ ባለማሟላታቸው እንዲሁም አዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የተቆፋፈረና ምቹ ባለመሆኑ የመዝጊያው ፕሮግራም ከስታዲየም ውጪ እንዲደረግ ተወስኗል። ከሀገሪቱ ጫፍ እስከ ጫፍ ወደ አ አበባ እየመጣችሁ ያላችሁ እንግዶች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይህንን በመገንዘብ ሳትለፉ ባላችሁበት እንድትከታታሉ አዘጋጆቹ ጠይቀዋል።

የትምህት ሚኒስቴር ፤ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ከመንግስት ጣልቃ ገብነት ነጻ ሆኖ ራሱን የሚያስተዳድር ዩኒቨርሲቲ እንደሚሆን አስታውቋል፡፡ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ÷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲን ተከትሎ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ከሁለት እስከ አምስት ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ በሂደት ወደ ነጻ ዩኒቨርሰቲነት እንደሚቀየሩ ተናግረዋል።

እስካሁን ድረስ ከፍተኛ ነው የተባለ የሰብዓዊ ድጋፍ ኮንቮይ ትግራይ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) አሳውቋል። ድርጅቱ በዚህ ሳምንት 308 ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ትግራይ መግባታቸውን ያመለከተ ሲሆን 800 ሺህ ለሚደርሱ ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ በቂ ምግብ የያዙ ናቸው ብሏል።

የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ሴካፋ የሴቶች ሲንየር ሻምፒየን ሺፕ በዩጋንዳ ሲካሄድ ኢትዮጵያ ከ ታንዛኒያ ጋር ያደረገችውን ጨዋታ 2 - 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች። የሉሲዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ቱሪስት ለማ እና ብዙአየሁ ታደሰ አስቆጥረዋል።

በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩና ቀሪ ትምህርታቸውን በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ያጠናቀቁ 417 ተማሪዎች ዛሬ ተመርቀዋል። ተመራቂዎቹ በተለያዩ መስኮች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን 164ቱ ሴት ተማሪዎች መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሜዳውን ጨዋታ ለማድረግ በማላዊ ባደረገው ቆይታ ግብፅ ላይ ካስመዘገበው ጣፋጭ ድል በተጨማሪ ከወጪው በላይ ገቢ በማስገባት ትርፍ ማስመዝገብ ችሏል። በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ ጋር ባደረገው ጨዋታ 68 ሺህ ዶላር የተጣራ ገቢ ማግኘቱ ነው የተገለጸው።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
5.2K viewsedited  20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 23:48:18
“ሴቶች የህብረተሰቡ ወሳኝ እና ግማሽ አካል ከመሆናቸው አንፃር ሴቶችን በሰላም ግንባታ እና በግጭት መከላከል ሂደት ውስጥ ማሳተፍ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የማህበረሰብ ክፍል ስለ ሰላም ግንባታ እና ግጭትን መከላከል ላይ ግንዛቤ እና ልምድ እንዲኖረው ማድረግ ማለት ነው።”

በኮምቦልቻ ከተማ በተደረገ የመጀመርያ ዙር የማህበረሰብ ውይይት የተነሳ

For English

° Website ° Facebook ° Twitter ° Telegram
4.9K views20:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 11:23:26
በቀን 600 ቶን ፌሮ ብረት የማምረት አቅም ያለው የብረታ ብረት ፋብሪካ በዱከም ዛሬ ይመረቃል።

በዱከም ከተማ በቀን 450 ቶን ብረት ማቅለጥ የሚችል የብረታ ብረት ፋብሪካ ግንባታው ተጠናቆ ዛሬ እየተመረቀ ነው።

ፋብሪካው በቀን 600 ቶን ፌሮ ብረት የማምረት አቅም ያለው ታዳሽ የብረታ ብረት ማምረቻ ሲሆን 50 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ አርፏል። ግንባታውም 5 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ  ወደ ስራ ሲገባ ለ700 ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል። የውጭ  ምንዛሬን በማስቀረት ረገድም ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል። (FBC)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
22.2K viewsedited  08:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 11:15:22
የገቢዎች ሚኒስቴር ባሳለፍነው ግንቦት ወር ብቻ ከ26 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን ገለፀ።

ሚኒስቴሩ ሊሰበስብ ካቀደው 27 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ውስጥ 26 ቢሊየን 902ሚሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 97 ነጥብ 23 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተነግሯል፡፡

አፈጻፀሙ ከባለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀር የብር 8 ቢሊዮን 960 ሚሊየን ወይም የ28 ነጥብ 46 በመቶ እድገት እንዳለውም ተገልጿል።

አፈፃፀሙ በበርካታ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆኖ የተመዘገበ በመሆኑ ውጤቱ እጅግ በጣም ጥሩ መሆኑን ተናግሯል፡፡

የተሰበሰበው ገቢ ምንጭ ከአገር ውስጥ ታክስ 13 ቢሊዮን 663ሚሊየን ብር የሚሸፍን ሲሆን፥ ከውጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ ደግሞ 13 ቢሊዮን 238ሚሊየን ብር መሆኑ ነው የተመለከተው።

በዚህም መሰረት የአስራ አንድ ወራት 330 ቢሊዮን 980ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 309 ቢሊዮን 448 ሚሊየን ብር የተሰበሰበ ሲሆን፥ የ93.49 በመቶ አፈጻጸም ተመዝግቧል ነው የተባለው።

ይህ የ11 ወራት አፈጻጸም ከ2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ከ50 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
18.6K viewsedited  08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 11:15:08
የ4 ቀናት ጉዞ ወደ ውቢቷ ዱባይ በድጋሚ ይዘንልዎ መጣን!

ከ 39,799 ብር ጀምሮ!

ቪዛ እና የደርሶ መልስ ቲኬት
ባለ 4 ወይም 5 ኮከብ ሆቴል የ4 ምሽቶች ቆይታ (ማረፊያ) ከጣፋጭ ቁርስ ጋር

ጥቅሉን ይግዙ እና ለ4 ቀናት አስገራሚ ጊዜ ያሳልፉ!

ለበለጠ መረጃ 0115621010 / 0115583058 / 0111575052 ደውለው ሊያገኙን ይችላሉ!

CLICK HERE TO DOWNLOAD OUR APP AND EASILY BOOK YOUR TICKETS

በየጊዜው የምናዘጋጃቸውን ልዩ እና በቅናሽ የቀረቡ የጉብኝት ጥቅሎችን እና የበረራ ትኬቶችን የቴሌግራም ቻናላችንን በመቀላቀል ያግኙ!

@fourwindstravel
16.0K views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 11:15:08
ምን ለመግዛት ወይ ለመሸጥ አስበዋል?

ቤት ፡ መኪና ፡ አፓርትመንት ፡ መሬት ፡ የባንክ ሼር እና የመሳሰሉትን ንብረትዎን በፍጥነት እናሻሸጣለን።

ማይደላላን የመጀመርያ ምርጫዎ ያድርጉ!
ለግዢ፣ ለሽያጭ፣ እና ለኪራይ እኛ ጋር ይደውሉ።

አብረውን መስራት ለሚፈልጉ በራችን ክፍት ነው!
Telegram: https://t.me/MyDelala
: 0903429999
17.0K views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 23:39:13 #የዛሬ (ግንቦት 3/2014)

ኢትዮጵያ የሶማሌላንድ መንግስት በበርበራ ወደብ ላይ የባለቤትነት መብትን አስመልክቶ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ባለመቻሏ በበርበራ ወደብ ላይ ያላትን የ19 በመቶ ድርሻዋን ማጣቷን ተሰምቷል። የሶማሌላንድ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደገለጸው ከቅድመ-ሁኔታዎች አንዱ ለወደቡ ግንባታ የገንዘብ መዋጮ ሲሆን ኢትዮጵያ ይህን ማድረግ ሳትችል ቀርታለች። የኢትዮጵያ መንግስት መረጃውን እያጣራ እንደሚገኝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተፈጸሙ በተባሉ ጥሰቶች ላይ ተመድ [UN] ሊያደርገው ያቀደው #ተጨማሪ ምርመራ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። በኢሰማኮ እና በተመድ የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የጋራ ሪፖርት ላይ የተመላከቱ ምክረ ሀሳቦችን ለመተግበር መንግስት ዝግጁ ነው ብለዋል። ነገር ግን በተመድ በኩል ተጨማሪ ምርመራ ለማድረግ የሚደረገው አካሄድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ሰኔ 3/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን የሰጠ ሲሆን በ30,000 /ሰላሳ ሽህ ብር/ ዋስትና #እንዲወጡ አዟል። ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኋላም ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ከእስር መለቀቃቸውን ቤተሰቦቻቸው አሳውቀዋል።

የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት፤ በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲመረምር ያቋቋመውን ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ኮሚሽን በሊቀመንበር ሲመሩ የነበሩት ፋቱዋ ቤንሱዳ በብሪታኒያ እና በጋራ ብልጽግና (ኮመን ዌልዝ) አገራት የጋምቢያ ከፍተኛ ኮሚሽነር ሆነው በሀገራቸው መንግስት በመሾማቸው ምክንያት ከኃላፊነታቸው #መልቀቃቸውን አሳውቀዋል። በምትካቸው ኬንያዊቷ የህግ ባለሙያ #ካሪ_ቤቲ_ሙሩንጊ ተሹመዋል።

ቴሌግራም አሁን #በነፃ እየሰጠ ያለው አገልግሎት #እንደተጠበቀ ሆኖ ተጨማሪ አገልግሎት የሚሰጥበትን እና ድርጅቱም ገቢ የሚያገኝበትን በክፍያ የሚሰጥ " ቴሌግራም ፕሪሚየም " የተሰኘ አገልግሎት በዚህ ወር ያስጀምራል።

በደሴ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ ስልክ አምባ ትምህርት ቤት በተለምዶ ሚካኤል ጀርባ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በነበረ የቆሻሻ ማቃጠያ ቦታ ከቆሻሻ ማቃጠያው የወዳደቁ የቁራሊዬ እቃዎችን እየሰበሰቡ የነበሩ ሶስት #የ7ኛ ክፍል ተማሪዎች የከባድ መሳሪያ ተተኳሽ ፈንድቶ በሶስቱም ላይ ጉዳት አድርሷል። ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎችም በአሁኑ ሰአት የህክምና አገልግሎት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
4.9K viewsedited  20:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 21:33:39
አውሎ ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ከ150 በላይ ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ።

በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር ሰኔ 1/2014 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ገደማ በተከሰተ አውሎ ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ከ150 በላይ ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱን የመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኅላፊ አቶ ሲሳይ ጌትሽ ገልጸዋል።

እንደ ኅላፊው ገለጻ በተከሰተው የዝናብ አደጋ የመንግሥት አገልግሎት ሠጭ ተቋማትን ጨምሮ 105 የመኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ የተጎዱ ሲሆን 45 ቤቶች ደግሞ በከፊል ጉዳት ደርሶባቸዋል። በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ ኅላፊው ተናግረዋል።

በመኖሪያ ቤቶች በመንግሥት እና መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ የደረሰው ውድመት በጥሬ ገንዘብ ሲገመት ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሆነ ነው የተጠቆመው። ጉዳት ከደረሰባቸው የመንግሥት ተቋማት መካከል የመተማ ዮሐንስ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤት አንዱ ነው።

ስምንት የመማሪያ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውንና ስምንት ደግሞ በከፊል ጉዳት እንደደረሰባቸው የትምሕርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አበበ እንዳለው ገልጸዋል።

የመብራት ፖሎች በመውደቃቸው እና የተዘረጉ ገመዶች በመበጣጠሳቸው የመብራት አገልግሎት ተቋርጧል። የወደሙ የመንግሥት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ከመንግሥት ባሻገር ባለሀብቶችና ረጅ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉም አቶ ሲሳይ ጥሪ አቅርበዋል። (አሚኮ)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
13.9K views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ