Get Mystery Box with random crypto!

#የዛሬ (ሰኔ 5/2014) 'እኛ በጤና ሚኒስትር በኩል በኮቪድ ላይ በኮንትራት ተቀጥረን የምን | TIKVAH-MAGAZINE

#የዛሬ (ሰኔ 5/2014)

"እኛ በጤና ሚኒስትር በኩል በኮቪድ ላይ በኮንትራት ተቀጥረን የምንሰራ ባለሙያዎች ነን። ኮቪድ ከጀመረ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ ሆስፒታሎች ስናገለግል ቆይተናል። የጤና ሚኒሰትር እና ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በቋሚነት እንደተቀጠርን በደብዳቤ ገለፀው ነበር ከአንድ አመት በፊት ፤ አሁን ግን ኮንትራት ጨርሳችዋል ምንም የምናደርገው ነገር የለም ብለው ደብዳቤ ደረሰን። ምንም አንኳን ባንመሰገን ሲያልቅ መወርወር አልነበረብንም'' ፦ በኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ወቅት በኮንትራንት ተቀጥረው ሲያገለግሉ የነበሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የጤና ባለሞያዎች መልዕክት

ተጨማሪ ያንብቡ [ 1 , 2 ]

"የኢትዮጵያ ዓለም ዓቀፍ የቁርአን ሂፍዝ ውድድር ሽልማት በዛሬው ዕለት ይደረግ የነበረው ወደ ሰኞ 06/10/14 ተቀይሯል። ህዝባችን ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በመምጣት ፕሮግራሙን እንድትታደሙ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ ለተፈጠረው ክፍተት ሕዝባችንን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ " ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር

ዛሬ በአዳማ ከተማ የአፋርና የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ የሰላም ውይይት ማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል። መድረኩ በሁለቱ ማህበረሰብ መካከል ያሉ አለመግባባቶችን በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምን ማምጣት አላማ ያደረገ ነው ተብሏል።

በትግርኛ የሙዚቃ ስራዎች በእጅጉ የሚታወቀው አርቲስት ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። አርቲስቱ ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበር ተነግሯል። ከሙዚቃ ስራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ፣ ወዘመይ፣ ቸቸኮላታ፣ ኣጆኺ ትግራይ፣ ቕዱስ ፀባያ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot